የታተመው:
የሚጀምረው፦ ሜይ 1፣ 2018
Microsoft የአገልግሎቶች ስምምነት
ግላዊነትዎግላዊነትዎ1_YourPrivacy
ማጠቃለያ

1. ግላዊነትዎ። ግላዊነትዎ መጠበቁ ለእኛ ጠቃሚ ነው። እባክዎ የMicrosoft የግላዊነት መግለጫን ("የግላዊነት መግለጫ") ከእርስዎ እና ከመሳሪያዎችዎ የምንሰበስባቸውን የውሂብ አይነቶች ("ውሂብ")፣ ውሂብዎን እንዴት እንደምንጠቀምበት፣ እና ውሂብዎን የምናካሂድበትን ሕጋዊ መሰረት የሚያስረዳ በመሆኑ እባክዎ ያንብቡት። የግላዊነት መግለጫው በተጨማሪም Microsoft የእርስዎን ይዘት እንዴት እንደሚጠቀም፣ ይኽም እርስዎ ከሌሎች ጋር የሚያደርጓቸው ግንኙነቶች፣ በእርስዎ በአገልግሎቶቹ በኩል ለ Microsoft የገቡ ልጥፎች፤ እንዲሁም ፋይሎች፣ ፎቶዎች፣ ሰነዶች፣ ኦዲዮ፣ የዲጂታል ሥራዎች፣ የቀጥታ ዥረቶች፣ እና እርስዎ የሚሰቅሏቸው፣ የሚያከማቿቸው፣ የሚያሰራጯቸው፣ ወይም በአገልግሎቶቹ በኩል የሚያጋሯቸው ቪዲዮዎች ናቸው፣("የእርስዎ ይዘት"). በሂደት ውስጥ ማሳለፍ በፈቃድ ላይ የተመሰረተ ከሆና በሕግ እስከተፈቀደው ድረስ ከሆነ፣ በእነዚህ ውሎች መስማማትዎ፣ በMicrosoft የእርስዎን ይዘት እና ውሂብ፣ በግላዊ መግለጫው ውስጥ በተመለከተው መሰረት መሰብሰብ፣ ጥቅም ላይ ማዋል እና መገለጽ እንዲችል ፈቃድ ይሰጣሉ። አንዳንድ ጊዜ፣ የተለየ ማሳወቂያ በማቅረብ በግላዊነት መግለጫው ውስጥ በተገለጸው መሰረት ፈቃድዎን እንጠይቃለን።

ሙሉ ጽሁፍ
የእርስዎ ይዘትየእርስዎ ይዘት2_yourContent
ማጠቃለያ

2. የእርስዎ ይዘት። አብዛኛዎቹ አገልግሎቶቻችን የእርስዎን ይዘት እንዲያከማቹ ወይም እንዲያጋሩ ወይም ከሌሎ ነገሮችን እንዲቀበሉ ይፈቅዱልዎታል። የእርስዎ ይዘቶችን ባለቤትነት አንጠይቅም። የእስዎ ይዘት የእራስዎ ይዘት እንደሆነ የሚቆይ ሲሆን ሃላፊነቱም የራስዎ ነው።።

 • ሀ. ይዘዎን ከሌሎች ጋር በሚያጋሩ ጊዜ፣ እነርሱ በዓለም አቅፍ ደረጃ መጠቀም፣ ማስቀመጥ፣ መቅረጽ፣ ዳግም መስራት፣ ማሰራጨት፣ ማስተላለፍ፣ ማጋራት እና ማሳየት (እና በHealthVault ስረዛ ላይ) እንደሚችሉ ተረድተዋል። ሌሎች ይህ ሃላፊነት እንዲኖርባቸው ካልፈለጉ አገልግሎቱን የእርስዎን የዘቶች ለማጋራት አይጠቀሙበት። ለእነዚህ ውሎች ቆይታ፣ በአገልግሎቶቹ በኩል እና በአገልግሎቶቹ ላይ ለተሰቀሉ፣ ለተከማቹ ወይም ለተጋሩ ይዘቶች ሙሉ የባለቤትነት መብት እንዳለዎ እና፣ እነዚህን ይዘቶች መሰብሰብ፣ መጠቀም፣ ይዞ ማቆየት ማናቸውንም የሌሎች መብቶች እንደማይጥስ ማረጋገጫ እና ዋስትና ሰጥተዋል። Microsoft የእርስዎ ይዘትን ባለቤት አይሆንም፣ አይቆጣጠርም፣ አያረጋግጥም፣ አይከፍልለትም፣ እውቅና አይሰጥም ወይም በማንኛውም ሌላ ሁኔታ ሃላፊነት አይወስድም። በተጨማሪም ለእርስዎ ይዘት ወይም አገልግሎቱን በመጠቀም ሌሎች ለሰቀሏቸው፣ ላከማቿቸው ወይም ላጋሯቸው አገልግሎቶች በሃላፊነት አይጠየቅም።
 • ለ. አገልግሎቱን ለእርስዎና ለሌሎች ሰዎች ለማቅረብ፣ እርስዎንና አገልግሎቶቹን ለመጠበቅ እንዲሁም የ Microsoft ምርቶችንና አገልግሎቶችን ለማሻሻል አስፈላጊ እስከሆነው መጠን ድረስ ለ Microsoft ይዘትዎን እንዲጠቀም አለም አቀፍ የሆነና ከክፍያ ነጻ የሆነ የአእምሮአዊ ንብረት ፈቃድ ሰጥተውታል። ለምሳሌ የእርስዎን ይዘት በአገልግሎቱ ላይ ቅጂ ለማድረግ፣ ለማቆየት፣ ለማስተላለፍ፣ ዳግም ቅርጸቱን ለማስተካከል፣ ለማሳየትና በግንኙነት መሳሪያዎች በኩል ለማሰራጨት። ይዘትዎን አገልግሎቱ በስፋት በመስመር ላይ ያለ ምንም ገደብ የሚገኝባቸው አካባቢዎች ላይ ካተሟቸው የእርስዎ ይዘት በማሳያዎች ላይ ወይም አገልግሎቱን በሚያስተዋውቁ ነገሮች ላይ ሊታይ ይችላል። አንዳንዶቹ አገልግሎቶች በማስተወቂያ የሚሸፈኑ ናቸው። Microsoft ማስታወቂያዎችን ለግል የሚያበጅበትን መንገድ መቆጣጠሪያዎች በMicrosoft የመለያ አስተዳደር ድር ጣቢያ ደህንነትና ግላዊነት ገጽ ላይ ማግኘት ይቻላል። በኢሜይል፣ በውይይትመ በቪዲዮ ጥሪዎች ወይም የድምጽ መልእክቶች ወይም በሰነዶችዎ፣ ፎቶዎችዎ ወይም በሌሎች የግል ፋይሎ ውስጥ የሚሏቸውን ነገሮች ማስታወቂያዎችን ወደ እርስዎ ለማነጣጠር አንጠቀምም። የማስታወቂያ ፖሊሲዎቻችን በዝርዝር በግላዊነት መግለጫው ውስጥ ተሸፍነዋል።
ሙሉ ጽሁፍ
የስነምግባር ደንብየስነምግባር ደንብ3_codeOfConduct
ማጠቃለያ

3. የስነምግባር ደንብ።

 • ሀ. በእነዚህ ውሎች በመስማማት አገልግሎቱን ሲጠቀሙ እነዚህን ደንቦች እንደሚከተሉ እየተስማሙ ነው:
  • i. ማንኛውንም ህገ ወጥ ነገር አያድርጉ።
  • ii. ህጻናትን የሚበዘብዝ፣ የሚጎዳና ጉዳት ለማድረስ የምያስፈራራ ማንኛውም እንቅስቃሴ ላይ አይሳተፉ።
  • iii. አይፈለጌ መልእክቶን አይላኩ። አይፈለጌ መልእክት ማለት የማይፈለግ ወይም ቁጥጥር የማይደረግበት በርካታ ኢሜይሎች፣ ልጥፎች፣ የእውቂያ ጥያቄዎች፣ አጭር የስልክ መልእክቶች (የጽሁፍ መልእክት) ወይም ፈጣን መልእክቶች ናቸው።
  • iv. አግባብነት የሌላቸው ይዘቶችን በይፋ አያሳዩ፣ ወይም አገልግሎቱን ለዚህ ዓላማ (ለምሳሌ ዕርቃን፣ ልቅ ወሲብ፣ አስጸያፊ ቋንቋ፣ አሰቃቂ ምስል፣ ወይም ይወንጀል ድርጊት ለማሳየት) ፣ ወይም አካባቢያዊ ሕጎችም የማያከብሩ ይዘቶችን እና መረጃዎችን ይፋ ለማድረግ አይጠቀሙ።
  • v. የማጭበርበር፣ የሓሰት ወይም አሳሳች (ለምሳሌ በማስመሰል ገንዘብ መጠየቅ፣ ሌላ ሰውን ነንደሆኑ አስመስሎ መቅረብ፣ የጨዋታ ቁጥርን ከፍ አድርጎ ለማሳየት ወይም ደረጃን ወይም አስተያየቶችን ለመለወጥ አገልግሎቶችን ማመቻቸት) ወይም ፈራጅ ወይም ስም የሚያጠፉ እንቅስቃሴ ውስጥ አይሳተፉ።
  • vi. በአገልግሎቶቹ መዳረሻ ወይም ተገኚነት ላይ የተጣሉ ገደቦችን ለመጣስ አይሞከሩ።
  • vii. ለእርስዎ፣ ለአገልግሎቱ ወይም ለሌሎች ጎጂ የሆኑ ተግባራት ላይ (ለምሳሌ፡ ቫይረሶችን ማስተላለፍ፣ ሰው መከታተል፣ የአሸባሪነት ይዘት መለጠፍ፣ የጥላቻ ንግግሮችን ማድረግ ወይም ሌሎች ላይ የሚደርስ ጥቃትን ማበረታታት) የመሳሰሉ ነገሮች ላይ አይሳተፉ።
  • viii. የሌሎችን ሰዎች መብቶች አይጣሱ (ለምሳሌ የቅጂ መብት ከለላ ያለውን ሙዚቃ ወይም ሌላ የቅጂ መብት ከለላ ያለውን ነገር ያለፈቃድ ማጋራት፣ Bing ካርታዎችን ወይም ፎቶግራፎችን ዳግም መሸጥ ወይም በሌላ መልኩ ማሰራጨት)።
  • ix. የሌሎች ሰዎችን ግላዊነት ወይም የውሂብ ጥበቃ የሚነካ ተግባር ላይ አይሰማሩ።
  • x. ሌሎች ሰዎች እነዚህን ውሎች እንዲጥሱ አያግዙ።
 • ለ. አፈጻጸም። እነዚህን ውሎች ባያከብሩ፣ በራሳችን ውሳኔ አገልግሎቶችን ለእርስዎ ማቅረብ ለናቋረጥ እንዲሁም የMicrosoft መለያዎን ልንዘጋ እንችላለን። እንዲሁም እነዚህን ውሎች ለማስከበር የግንኙነት መልዕክትዎን(ለምሳሌ ኢሜይል፣ ፋይል ማጋራት ወይም ፈጣን መልዕክት) ከአገልግሎቱ ወይም ወደ አገልግሎቱ እንዳይደርስ ልናግድ እንችላለን። ወይም ይዘትዎን በማንኛውም ምክንያት ልናስወግድ ወይም እንዳይታተም ልንከለክል እንችላለን። እነዚህ ጥሰቶች መከሰትና አለመከሰት በምንመረምርበት ወቅት Microsoft ችግሩን ለመፍታ የእርስዎን ይዘት የመገምገም መብቱ የተጠበቀ ሲሆን እርስዎም በዚህ ለግምገማው ፈቃድ ይሰጣሉ። ነገር ግን አጠቃላይ አገልግሎቶቹን መቆጣጠር የማንችል ሲሆን እንደዚያም ለማድረግ አንሞክርም።
 • ሐ. ለ Xbox አገልግሎቶች ተፈጻሚነት። ይህ የስነ ምግባር ደንብ እንዴት በMicrosoft በሚቀርቡት Xbox Live፣ Games for Windows Live እና Microsoft Studios ጨዋታዎች፣ መተግበሪያዎች፣ አገልግሎቶች እና ይዘቶች ላይ ተፋጻሚ እንደሚሆን ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ጋር ጠቅ ያድርጉ። በ Xbox አገልግሎቶችን (በክፍል 13(ሀ)(i) የተገለጸው) መጣስ የይዘት ፈቃዶችን፣ Xbox የወርቅ አባልነት ጊዜን ጨምሮ፣ በፈቃድዎ እንደመተው መቆጠርን ጨምሮ፣ ከመለያው ጋር የተያያዙ የ Microsoft መለያ ሂሳቦችን ጨምሮ፣ በ Xbox አገልግሎቶች ውስጥ ከመሳተፍ መከልከል ወይም መታገድን ሊያስከትል ይችላል።
ሙሉ ጽሁፍ
አገልግሎቱን መጠቀምና ድጋፍአገልግሎቱን መጠቀምና ድጋፍ4_usingTheServicesSupport
ማጠቃለያ

4. አገልግሎቱን መጠቀምና ድጋፍ።

 • ሀ. Microsoft መለያ። አብዛኛዎቹነ አገልግሎቶች ለማግኘት የ Microsoft መለያ ያስፈልግዎታል። የ Microsoft መለያዎ በ Microsoft እና በአንዳንድ የ Microsoft አጋሮች ወደሚቀርቡ ምርቶች፣ ድር ጣቢያዎችና አገልግሎቶች በመለያ እንዲገቡ ያስችልዎታል።
  • i. መለያ መፍጠር። የMicrosoft መለያን በመስመር ላይ በመመዝገብ መፍጠር ይችላሉ። ለMicrosoft መለያ በሚመዘገቡ ጊዜ ማናቸውንም አይነት የሐሰት፣ የተዛባ፣ ወይም አሳሳች መረጃ ላለመጠቀም ይስማማሉ። በአንዳንድ ሁኔታዎች እንደ የበይነ መረብ ግንኙነት አቅራቢዎ የመሳሰለ ሶስተኛ ወገን ለእርስዎ የ Microsoft መለያ መድቦልዎ ሊሆን ይችላል። የ Microsoft መለያዎን ከሶስተኛ ወገን ከተቀበሉት ይህ ሶስተኛ ወገን መለያዎ ላይ የ Microsoft መለያዎን መድረስና መሰረዝን የመሳሰሉ ተጨማሪ መብቶች ሊኖሩት ይችላል። Microsoft ስለ ሶስተኛ ወገን ውሎች ምንም ሃላፊነት ስለሌለበት እባክዎ ማናቸውንም ሶስተኛ ወገኑ የሰጠዎትን ተጨማሪ ውሎች ይገምግሙ። እንደ ንግድዎ ወይም ቀጣሪዎ የመሳሰለ አንድ ተቋምን በመወከል የ Microsoft መለያ ከፈጠሩ ያንንን ተቋም በእነዚህ ውሎች ተገዢ እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችል የህግ ስልጣን እንዳለዎ ያረጋግጣሉ። የMicrosoft መለያ ማረጋገጫዎችዎን ለሌላ ተጠቃሚ ወይም አካል አሳልፈው መስጠት አይችሉም። መለያዎን ለመጠበቅ የመለያ ዝርዝሮችዎንና የይለፍ ቃልዎን ሚስጥራዊነቱ እንደተጠበቀ ያቆዩ። በMicrosof መለያዎ ስር ለሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ኃላፊነት ይወስዳሉ።
  • ii. የመለያ አጠቃቀም። እንደነቃ ለማቆየት የ Microsoft መለያዎን መጠቀም አለብዎ። ይህ ማለት የአገልግሎቶቹን የሚከፈልባቸው ክፍሎች የተሰጠ በተለየ ካልተደነገገ መሰረት የ Microsoft መለያዎንና ተዛማጅ አገልግሎቶችን እንደነቁ ለማቆየት ቢያንስ በአምስት አመት ጊዜ ውስጥ ቢያንስ አንድ ጊዜ በመለያ መግባት አለብዎ። በዚህ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በመለያ ካልገቡ የ Microsoft መለያዎ ንቁ እንዳልሆነ እንወስደውና እንዘጋዋለን። የተዘጋ የ Microsoft መለያ ስለሚያስከትላቸው ነገሮች ለማየት ክፍል 4(ሀ)(iv)(2) ይመልከቱ። ወደ Outlook.com የገቢ መልእክት ሳጥንዎና OneDrive (ለየብቻ) ቢያንስ በአመት አንድ ጊዜ በመለያ መግባት አለብዎ። አለበለዚያ የ Outlook.com የገቢ መልእክት ሳጥንዎንና የእርስዎንOneDrive እንዘጋልዎታለን። የጨዋታ መለያ ከMicrosoft መለያዎ ጋር እንደተዛመደ እንድቆይ ወደ Xbox አገልግሎቶች በ አምስት-ዓመት ጊዜ ውስጥ ቢያንስ አንድ ጊዜ በመለያ መግባት አለብዎ። በበቂ ምክንያት የMicrosoft መለያዎ በተጭበረበረ ሁኔታ በሶስተኛ ወገን እጅ እንደወደቀ ካመንን (ለምሳሌ መለያ በመበርበሩ ምክንያት) እርስዎ እንዲመለስልዎ እኪጠይቁ ድረስ Microsoft መለያውን ሊያግድ ይችላል። በተፈጠረው ችግር ላይ በመመስረት ከእርስዎ ይዘት ውስጥ የተወሰነውን ወይም ሁሉንም እንድናግድ ልንጠየቅ እንችላለን። የ Microsoft መለያዎን አጠቃቀም ላይ ችግር እያጋጠመዎ ከሆነ እባክዎ ይህንን ድሕረ ገፅ ይጎብኙ: https://go.microsoft.com/fwlink/?LinkId=238656
  • iii. ህጻናትና መለያዎች። አገልግሎቱን በመጠቀም በሚኖሩበት አካባቢ "አዋቂነት" ወይም "በህግ ፊት ሃላፊ የመሆን" እድሜ ላይ እንደደረሱ ወይም በእነዚህ ውሎች ለመገዛት ልክ የሆነ የወላጅ ወይም ያሳዳጊ ፈቃድ እንዳለዎት ያረጋግጣሉ። በሚኖሩበት ቦታ ለአካለ መጠን ወይም ለ “ሕጋዊ ኃላፊነት” ስለመድረስዎ እርግጠኛ ካልሆኑ፣ ወይም ይህን ክፍል የማይረዱ ከሆነ፣ እባክዎ የMicrosoft መለያ ከመፍጠርዎ በፊት ወላጆችዎን ወይም ሕጋዊ አሳዳጊዎን ይጠይቁ። የMicrosoft መለያ የሚፈጥር ለአካለ መጠን ያልደረሰ ወጣት ወላጅ ወይም ሕጋዊ አሳዳጊ ከሆኑ፣ እርስዎም ሆነ ልጁ እነዚህን ውሎች ይቀበላሉ ይስማማሉም፣ እንዲሁም የወጣቱ መለያ አሁን ተከፍቶ እንደሆነም ወይም በኋላ ተፈጥሮ እንደሆነ በMicrosoft መለያ ወይም አገልግሎቶች አጠቃቀም ላይ፣ ግዥዎችን ጨምሮ፣ ኃላፊነት አለብዎ።
  • iv. መለያዎን መዝጋት።
   • 1. የታወቁ አገልግሎቶችን ወይም የበMicrosoft መለያዎን በማንኛውም ጊዜ እና በማንኛውም ምክንያት መሰረዝ ይችላሉ። የ Microsoft መለያዎን ለመዝጋት እባክዎ https://go.microsoft.com/fwlink/p/?linkid=618278 ይጎብኙ። የ Microsoft መለያዎን እንድንዘጋ ሲጠይቁን ምናልባት ሃሳብዎን ከለወጡ በሚል ለ 60 ቀናት በታገደ ሁኔታ ውስጥ እናቆየዋለን። ከ 60 ቀን ጊዜው ካለፈ በኋላ የ Microsoft መለያዎ ይዘጋል። የMicrosoft መለያዎ በሚዘጋ ጊዜ ምን እንደሚከሰት ማብራሪያ ለማግኘት እባክዎ ከዚህ በታች ክፍል 4(ሀ)(iv)(2)ን ይመልከቱ። በ60 ቀን ጊዜው ውስጥ መልሰው ወደ መለያዎ መግባት የ Microsoft መለያዎን ዳግም ያነቃዋል።
   • 2. የMicrosoft መለያዎ ከተዘጋ (በእርስዎ ወይም በእኛ)፣ የተወሰኑ ነገሮች ይከሰታሉ። በመጀመሪያ፣ አገልግሎቶች ዘንድ ለመድረስ የMicrosoft መለያዎን የመተቀም መብትዎ ወዲያውኑ ያበቃል። ሁለተኛ፣ ውሂብ ወይም ከMicrosoft መለያዎ ጋር ተያያዥ የሆነ ይዘትዎን እንሰርዛለን፣ ወይም ከእርስዎ የMicrosoft መለያ እንነጥለዋለን (እንድናቆየው ፣ እንድንመልሰው፣ ወይም ወደ እርስዎ ወይም በእርስዎ ወደተለየ ሶስተኛ ወገን እንድናስተላልፍ በሕግ ካልተገደድን በስተቀር)። አንድ ጊዜ መለያዎ ከተዘጋ በኋላ Microsoft የእርስዎን ይዘት መልሶ ለማግኘት ስለማይችል መደበኛ የሆነ ምትኬ የማስቀመጥ ልምድ ሊኖርዎ ይገባል። ሦስተኛ፣ ወደገዟቸው ምርቶች መዳረሻዎን ሊያጡ ይችላሉ።
 • ለ. የሥራ ወይም የትምህርት ቤት መለያዎች። ወደተወሰኑ የMicrosoft አገልግሎቶች በሥራ ወይም በትምህርት ቤት ኢሜይል አድራሻዎ መግባት ይችላሉ። ያ ከሆነ፣ ከእርስዎ ኢሜይል ጋር ተያያዥ የሆነው ሆራ ባለቤት የእርስዎን መለያ እንዲቆጣጠር እና ውሂብዎ ዘንድ እንዲደርስ እንዲሁም እንዲሠራ፣ የግንኙነቶችዎን እና ፋይሎችዎን ይዘት ጨምሮ፣ እንዲሁም መለያው ወይም ውሂብ ደህንነቱን አጥቶ ከሆነ Microsoft ለጎራው ባለቤት እንዲያሳውቅ ይስማማሉ። በተጨማሪም የMicrosoft አገልግሎቶችን መጠቀምዎ Microsoft ከእርስዎ ወይም ከድርጅትዎ ጋር ላለው ውሎች ተገዥ ሊሆኑ እንደሚችሉና እነዚህ ውሎች ተፈጻሚ ላይሆኑ እንደሚችሉ ይስማማሉ፡ ቀድሞም የMicrosoft መለያ ካለዎና በእነዚህ ውሎች የሚሸፈኑ አገልግግሎቶችን ለማግኘት የተለየ የሥራ ወይም የትምህርት ቤት ኢሜይል አድራሻ የሚጠቀሙ ከሆነ እነዚህን አገልግሎቶች ማግኘትዎን እንዲቀጥሉ ከMicrosoft መለያዎ ጋር የተዛመደውን ኢሜይል እንዲያዘምኑ ሊጠየቁ ይችላሉ።
 • ሐ. ተጨማሪ መሳሪያ/ውሂብ ዕቅዶች አብዛኛዎቹን አገልግሎቶች ለመጠቀም የበይነመረብ ግንኙነት እና/ወይም የውሂብ.ሞባይል እቅድ ሊኖርዎ ይገባል። በተጨማሪም እንደ የጆሮ ማዳመጫ፣ ካሜራ ወይም ማይክሮፎን የመሳሰሉ ተጨማሪ መሳሪዎችን ሊፈልጉ ይችላሉ። አገልግሎቱን ለመጠቀም የሚያስፈልጉትን ሁሉንም ግንኙነቶች፣ ዕቅዶች፣ እና መሳሪያዎች የማቅረብ እንዲሁም በግንኙነት፣ ዕቅድ እና መሳሪያ አቅራቢዎቹ የሚጠየቁ ክፍያዎችን የመክፈል ኃላፊነት አለብዎ። እነዚያ ክፍያዎች ለእኛ ከሚከፍሉን ማናቸውም ክፍያዎች ሌላ ሲሆኑ የትኛዎቹንም ክፍያዎች እኛ አንከፍልልዎትም። ለእርስዎ ተፈጻሚ ሊሆኑ የሚችሉ ማናቸውም አይነት ክፍያዎች ካሉ አቅራቢዎችዎ ጋር ይፈትሹ።
 • መ. የአገልግሎት ማሳወቂያዎች። ስለሚጠቀሙት አገልግሎት ልንነግርዎ የምንፈልገው ነገር በሚኖር ጊዜ የአገልግሎት ማሳወቂያዎችን እንልክልዎታለን። ከMicrosoft መለያዎ ጋር በተያያዘ የኢሜይል አድራሻዎን ወይም ስልክ ቁጥርዎን ሰጥተውን ከሆነ፣ የአገልግሎት ማሳወቂያዎች ወደ እርስዎ በኢሜይል ወይም በSMS (የጽሁፍ መልዕክት) ልንልክልዎ እንችላለን፣ የሞባይል ስልክ ቁጥርዎን ከማስመዝገብዎ በፊት መላረጋገጥም ጭምር። በተጨማሪም የአገልግሎት ማሳወቂያዎችን በሌላ መንገድም ልንልክ እንችላለን (ለምሳሌ በምርት-ውስጥ መልዕክት)። በአጭር የስልክ መልእክት ማሳወቂያዎችን ሲቀበሉ የውሂብ ወይም የመልእክት መላኪያ ተመኖች ተፈጻሚ ሊሆኑ ይችላሉ።
 • ሠ. ድጋፍ። ለአንዳንድ አገልግሎቶች የደንበኛ አገልግሎት በsupport.microsoft.comላይ ይገኛል። አንዳንድ አገልግሎቶች፣ ከዚህ በተቃራኒው ካልተገለጸ በስተቀር፣ በ www.microsoft.com/support-service-agreement ላይ በተቀመጡ ውሎች መሰረት፣ የተለየ ወይም ተጨማሪ የደንበኛ አገልግሎት ሊሰጡ ይችላሉ። ለባህሪዎች ወይም አገልግሎቶች የቅድመ ዕይታ ወይም ቤታ ስሪቶች ድጋፍ ላይገኝ ይችላል። አገልግሎቱ በሶስተኛ ወገኖች ከቀረበ ሶፍትዌር ወይም አገልግሎት ጋር ተኳኋኝ ላይሆን የሚችል ሲሆን እርስዎ ለተኳኋኝነት መስፈርቶች ጋር እራስዎን የማስተዋወቅ ሃላፊነት አለብዎ።
 • ረ. አገልግሎቶዎን ማቆም። አገልግሎቶችዎ ከተሰረዙ (በእርስዎ ወይም በእኛ)፣ በመጀመሪያ ወደ አገልግሎቶቹ ያለዎት መዳረሻ ወዲያውኑ ይቆማል፣ ከዚያም ከአገልግሎቶቹ ጋር ተያያዥ በሆኑ ሶፍትዌሮች ያሉዎት ፈቃዶች ወዲያው ያበቃሉ። ሁለተኛ፣ ውሂብ ወይም ከMicrosoft መለያዎ ጋር ተያያዥ የሆነ ይዘትዎን እንሰርዛለን፣ ወይም ከእርስዎ የMicrosoft መለያ እንነጥለዋለን (እንድናቆየው ፣ እንድንመልሰው፣ ወይም ወደ እርስዎ ወይም በእርስዎ ወደተለየ ሶስተኛ ወገን እንድናስተላልፍ በሕግ ካልተገደድን በስተቀር)። በዚህም ምክንያት ማናቸውም አገልግሎቶች ዘንድ (ወይም በነዚያ አገልግሎቶች ውስጥ ያቆዩአቸውን ውሂቦች) ማግኘት አይችሉም። መደበኛ ምትኬ የማስቀመጥ ዕቅድ ሊኖርዎ ይገባል። ሦስተኛ፣ ወደገዟቸው ምርቶች መዳረሻዎን ሊያጡ ይችላሉ። የMicrosoft መለያዎን ከሰረዙ እና ሌሎች አገልግሎትዎ ዘንድ መድረሻ መለያዎች ከሌሉዎ፣ አገልግሎቶቾዎ ወዲያው ይሰረዛሉ።
ሙሉ ጽሁፍ
የሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎችንና አገልግሎቶችን መጠቀምየሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎችንና አገልግሎቶችን መጠቀም5_usingThird-PartyAppsAndServices
ማጠቃለያ

5. የሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎችንና አገልግሎቶችን መጠቀም። አገልግሎቶቹ ፣ ምርቶችን፣ አገልግሎቶችን፣ ድር ጣቢያዎችን፣ አገናኞችን፣ ይዘት፣ ቁሳቁስ፣ ጨዋታዎችን፣ ክህሎቶችን፣ ውህደቶችን፣ ቦቶችን ወይም ከገለልተኛ ሶስተኛ ወገኖች (Microsoft ያልሆኑ ኩባንያዎች ወይም ሰዎች ወይም መተግበሪያዎችን እንዲያገኙ ሊያስችሉዎ ይችላሉ። ("የሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎች እና አገልግሎቶች")። ከአገልግሎቶቻችን ብዙዎቹ በተጨማሪ የሶስተኛ-ወገን መተግበሪያዎችን እና አገልግሎቶችን ጥያቄዎች እንዲያቀርቡ፣ ወይም የድርጊት ልውውጥ እንዲያደርጉ፣ ይዘት ወይም ውሂብ እንዲያጋሩ ይረዱዎታል፣ በዚህም አገልግሎቶቻችንን ለእርስዎ የሶስተኛ-ወገን መተግበሪያዎችን እና አገልግሎቶችን ለእርስዎ እንዲያቀርቡ አቅጣጫ ሰጥተዋል። ሶስተኛ- ወገን መተግበሪያዎቹ እና አገልግሎቶቹ ይዘትዎን ወይም ውሂብዎን አታሚው፣ አቅራቢው ወይም አከናዋኙ ዘንድ እንዲያስቀምጡ ሊያስችልዎ ይችላሉ። የሶስተኛ-ወገን መተግበሪያዎች እና አገልግሎቶች የሶስተኛ-ወገን መተግበሪያዎን ወይም አገልግሎቱን ከማግኘትዎ በፊት የግላዊነት መመሪያ ሊያቀርቡልዎ ወይም ተጨማሪ ውሎችን እንዲቀበሉ ሊያስገድዱዎ ይችላሉ። በ Office ማከማቻ፣ የ Xbox ማከማቻ ወይም Windows ማከማቻ በኩል ለተገኙ መተግበሪያዎች ተጨማሪ ውሎችን ለማግኘት ክፍል 13(ለ)ን ይመልከቱ። የMicrosoft መለያዎን ከማግኘትዎ፣ ከመጠቀምዎ፣ ከመጠየቅዎ፣ ወይም ከማገናኘትዎ በፊት፣ ማናቸውንም ተጨማሪ ውሎች እና የግላዊነት ፖሊሲዎች መመልከት አለብዎ። ማናቸውም ተጨማሪ ደንቦች እነዚህን ደንቦች አይቀይሯቸውም። Microsoft እንደ የማንኛውም የሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎች ወይም አገልግሎቶች አካ የአእምሮአዊ ንብረት ጥበቃ ፈቃድ አይሰጥም። እነዚህን የሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎችና አገልግሎቶች ሲጠቀሙ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋቶችንና ሃላፊነቶችን ሙሉ ለሙሉ ለመቀበል የተስማሙ ሲሆን Microsoft እርስዎ ሲጠቀሟቸው ለሚነሱ ማናቸውም ችግሮች ሃላፊነት የለበትም። በማንኛውም የሶስተኛ-ወገን መተግበሪያ ወይም አገልግሎቶች በኩል በሚመታ መረጃ Microsoft ኃላፊነት የለበትም ተጠያቂም አይደለም።

ሙሉ ጽሁፍ
የአገልግሎት ተገኚነትየአገልግሎት ተገኚነት6_serviceAvailability
ማጠቃለያ

6. የአገልግሎት ተገኚነት።

 • ሀ. አገልግሎቶቹ፣ የሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎች እና አገልግሎቶች፣ ወይም በአገልግሎቶቹ በኩል የቀረቡ ነገሮች ወይም ምርቶች ከጊዜ ወደጊዜ ላይገኙ፣ በተገደበ ሁኔታ ሊቀርቡ ወይም በክልልዎ ወይም በመሳሪያዎ ላይ በመመስረት ሊለያዩ ይችላሉ። ከ Microsoft መለያዎ ጋር የተዛመደውን አካባቢ ከቀየሩ ከአሁን ቀደም በነበረው ክልል ውስጥ እርስዎ ያገኟቸው የነበሩና የከፈሉባቸውን ነገሮች ውይም መተግበሪያዎች መልሰው መያዝ ሊኖርብዎ ይችላል። አንድ ነገርን ወይም አገልግሎትን ለማግኘት ወይም ለመጠቀም በሚጠይቁበት አገር ላይ ያንን ነገር ማግኘት ወይም መጠቀም ህገ ወጥ ወይም ፈቃድ ያልተሰጠው ከሆነ ነገሩን ወይም አገልግሎቱን ከመጠቀም ለመቆጠብ ወይም ነገሩን ወይም አገልግሎቱን ለመድረስ ወይም ለመጠቀም ብለው አካባቢዎን ወይም ማንነትዎን ላለመደበቅ ወይም የተሳሳተ መረጃ ላለመስጠት ተስማምተዋል።
 • ለ. አገልግሎቱ እንዲቀጥል እንጥራለን ነገር ግን ሁሉም የመስመር ላይ አገልግሎቶች አልፎ አልፎ የሚያጋጥሙ መቋረጦችና ብልሽቶች ያጋጥሟቸዋል። በዚህም ምክንያት ለሚያጋጥሙ ብልሽቶች ወይም ኪራዎች Microsoft ሀላፊነት የለበትም። ብልሽት በሚያጋጥምበት ወቅት ያከማቹትን የእርስዎን ይዘት ወይም ውሂብ መልሰው ማግኘት አይችሉ ይሆናል። በየጊዜው በአገልግሎቶቹ ውስጥና በሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎች እና አገልግሎቶች ለሚያስቀምጧቸው ይዘትዎ እና ውሂብ በመደበኛነት ምትኬ እንዲያስቀምጡ እንመክራለን
ሙሉ ጽሁፍ
አገልግሎቱ ወይም ሶፍትዌሩ ላይ የተደረጉ ማዘመኛዎችና በእነዚህ ደንቦች ላይ የተደረጉ ለወጦችአገልግሎቱ ወይም ሶፍትዌሩ ላይ የተደረጉ ማዘመኛዎችና በእነዚህ ደንቦች ላይ የተደረጉ ለወጦች7_updatesToTheServicesOrSoftwareAndChangesToTheseTerms
ማጠቃለያ

7. አገልግሎቱ ወይም ሶፍትዌሩ ላይ የተደረጉ ማዘመኛዎችና በእነዚህ ደንቦች ላይ የተደረጉ ለወጦች።

 • ሀ. እነዚህን ደንቦች በማንኛውም ጊዜ ልንለውጣቸው የምንችል ሲሆን እነደዚያ ስናደርግ እንነግርዎታለን። ለውጦቹ ተፈጻሚ ከተደረጉ በኋላ አገልግሎቱን መጠቀም ማለት በእነዚህ አዲስ ደንቦች ተስማምተዋል ማለት ነው። ከአዲሶቹ ውሎች ጋር የማይስማሙ ከሆነ፣ አገልግሎቶቹን መጠቅም ማቆም፣ የMicrosoft መለያዎን መዝጋት እና፣ ወላጅ ወይም አሳዳጊ ከሆኑ፣ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅዎን የMicrosoft መለያውን(ዋን) እንዲዘጋ/እንድትዘጋ ያግዙት(ዟት)
 • ለ. አንዳንድ ጊዜ አገልግሎቱን መጠቀምዎን ለመቀጠል የሶፍትዌር ማዘመኛዎች ያስፈልጉዎታል። በራስ ሰር የሶፍትዌርዎን ስሪት ልንፈትሽና የሶፍትዌር ማዘመኛዎችን ወይም የማዋቀር ለውጦችን ልንጭን እንችላለን። አገልግሎቱን መጠቀምዎን ለመቀጠል ሶፍትዌሩን ማዘመን ሊጠየቁም ይችላሉ። እንደዚህ አይነት ማዘመኛዎች በሌሎች ተፈጻሚ በሚሆኑ ውሎች እስካልታጀቡ ድረስ በእነዚህ ውሎች ተገዢ ይሆናሉ። Microsoft ማናቸውንም ዝማኔዎች የማቅረብ ግዴታ የለበትም፣ እንዲሁም እርስዎ የገዙትን ወይም ፈቃድ የወሰዱበትን ሶፍትዌር፣ መተግበሪያዎች፣ ይዘት ወይም ሌሎች ምርቶች ስሪት ድጋፍ እንደምንሰጥ መተማመኛ አይሰጥም። እነዚህ ማዘመኛዎች በሶስተኛ ወገኖች ከተሰጡ ሶፍትዌሮች ወይም አገልግሎቶች ጋር ተኳኋኝ ላይሆኑ ይችላሉ። በማንኛውም ጊዜ ሶፍትዌሩን በማራገፍ ለማዘመኛዎች የሰጡትን ፈቃደኝነት ማንሳት ይችላሉ።
 • ሐ. በተጨማሪም፣ ባህሪያትን ወይም ክንውንን ለማስወገድ ወይም ለመቀየር የምንገደድበት ወይም አገልግሎቱን መስጠት ማቆም ወይም የሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎችንና አገልግሎቶችን መዳረሻ በአንድ ላይ መስጠት ማቆማችን አስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜ ሊኖር ይችላል። ተፈጻሚነት ባለው ሕግ ካልሆነ በስተቀር፣ የማናቸውም ቁሳቁሶችን፣ አኃዛዊ ሸቀጦችን (በ ክፍል 13(ቨ) እንደተበየነው) ምትክ መስጠት፣ ወይም ከዚህ ቀድሞ ለተገዙ መተግበሪያዎች የዳግም-ማውረድ ወይም ወይም ምትክ የመስጠት ግዴታ የለብንም። በትክክል ላይሰሩ የሚችሉ ወይም የመጨረሻው ስሪት በሚሰራበት መንገድ ላይሰሩ በሚችል መልኩ ግምገማዊ ወይም ቤታ መልክ አገልግሎቶችን ልንለቅ እንችላለን፣
 • መ. በዚህም እንደ ሙዚቃ፣ ጨዋታዎች፣ ፊልሞች፣ መጽሐፎች እና ሌሎችም ያሉ በአኃዛዊ መብቶች አስተዳደር (DRM) የተጠበቁ ቁሳቁሶችን መጠቀም እዲችሉ DRM ሶፍትዌር በራስ ሰር የመስመር ላይ የመብቶች አገልጋይን ሊያገኝ እና የDRM ዝማኔዎችን ሊያወርድ ይችላል።
ሙሉ ጽሁፍ
የሶፍትዌር ፈቃድየሶፍትዌር ፈቃድ8_softwareLicense
ማጠቃለያ

8. የሶፍትዌር ፈቃድ። በተለየ የMicrosoft የፈቃድ ስምምነት አብሮት ካልመጣ በስተቀር (ለምሳሌ፣ እንደ Windows አካል የተካተተ የMicrosoft መተግበሪያ የሚጠቀሙ ከሆነ፣ ለWindows ስርዓተ ክንውን ተፈጻሚ የሚሆኑት የMicrosoft ሶፍትዌር ፈቃድ ውሎች እንዲህ አይነት ሶፍትዌሮች ላይም ይተገበራሉ። በOffice መደብር፣ Windows መደብር እና Xbox መደብር ማካኝነት የተገዙ መተግበሪያዎች ላይ ከዚህ በታች ያለው ክፍል 13(ለ)(i) ተፈጻሚ ይሆናል።

 • ሀ. እነዚህን ደንቦች ካከበሩ እንደ አገልግሎቱ ተጠቃሚነትዎ በአንድ ጊዜ በአንድ ሰው ብቻ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ በመላው አለም በአንድ መሳሪያ ላይ አንድ ሶፍተትዌር የማውረድና የመጫን መብት እንሰጥዎታለም። ለአንዳንድ መሳሪያዎች፣ እንዲህ አይነቱ መሳሪያ ምናልባት ለእርስዎ ለንግድ ያልሆነ ግላዊ አጠቃቀም ቀድሞ የተጫነ ሊሆን ይችላል። የአገልግሎቱ አካል የሆነው ሶፍትዌር ወይም ድር ጣቢያ የሶስተኛ ወገን ኮድ ሊያካትት ይችላል። ከሶፍትዌሩ ወይም ድር ጣቢያው ጋር የተገናኑ ወይም ማጣቀሻ የተደረገባቸው ማናቸውም የሶስተኛ ወገን ስክሪፕቶች ወይም ኮዶች ፈቃድ የሚሰጥዎ በ Microsoft ሳይሆን የኮዶቹ ባለቤቶች በሆኑ ሶስተኛ ወገኖች ነው። የሶስተኛ ወገን ኮዱ ማሳወቂያዎች ካሉ የሚካተቱት ለመረጃ ብቻ ነው።
 • ለ. ሶፍትዌሩ ፈቃድ ተሰጠበት እንጂ አልተሸጠም። ስለዚህ Microsoft በማመልከትም፣ በዝምታም ይሁን በሌላ መንገድ በግልጽ አሳልፎ ያልሰጣቸውን ሶፍትዌሩ ላይ ያሉ መብቶች ለ Microsoft የተጠበቁ ናቸው። ይህ ፈቃድ ምንም መብት የማይሰጥዎ ሲሆን የሚከተሉትን ማድረግ አይችሉም:
  • i. በሶፍትዌሩ ወይም አገልግሎቱ ውስጥ ያሉ ወይም ከሱ ጋር የተዛመዱ የቴክኖሎጂ ጥበቃ እርምጃዎችን መጣስ፤
  • ii. ተፈጻሚ የሚሆነው የቅጂ መብት ህግ በግልጽ እስከሚፈቅደው ድረስ ካልሆነ በስተቀር ማንኛውንም ሶፍትዌር ወይም በአገልግሎቱ ውስጥ የተካተተ ወይም በአገልግሎቱ በኩል ሊደስበት የሚችል ሌላ የአገልግሎቱ ክፍልን መበተን፣ መልሶ መገጣጠም፣ ሚስጥራዊነትን መፍታት፣ መጥለፍ፣ አስመስሎ መስራት፣ መበዝበዝ ወይም ገልብጦ መስራት አይቻልም፤
  • iii. የሶፍትዌሩን ወይም የአገልግሎቱን በተለያዩ መሳሪያዎች ላይ ለመጠቀም መለያየት፤
  • iv. Microsoft በግልጽ እስካልፈቀደ ድረስ ሶፍትዌሩን ወይም አገልግሎቱን ማተም፣ መቅዳት፣ ማከራየት፣ በሊዝ መስጠት፣ መሸጥ፣ ወደ ውጪ መላክ፣ ማስመጣት፣ ማሰራጨት ወይም ማበደር፤
  • v. ሶፍትዌሩን፣ ማናቸውንም የሶፍትዌር ፈቃዶች ወይም አገልግሎቶቹ ላይ የመድረስ ወይም የመጠቀም መብቶችን ማስተላለፍ፤
  • vi. አገልግሎቶቹን የሌላ ሰውን የመጠቀም ነጻነት በሚያውክ መልኩ ያለፈቃድ መጠቀም ወይም ማንኛውንም አገልግሎት፣ ውሂብ፣ መለያ ወይም አውታረ መረብ መጠቀም፤
  • vii. ፈቃድ ያልተሰጣቸው የሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎች ወደ መለያው መዳረሻ እንዲኖራቸው ማድረግ ወይም ማናቸውንም የ Microsoft ፈቃድ ያለው መሳሪያ (ለምሳሌ Xbox One፣ Xbox 360፣ Microsoft Surface ወዘተ) መቀየር
ሙሉ ጽሁፍ
የክፍያ ሁኔታዎችየክፍያ ሁኔታዎች9_paymentTerms
ማጠቃለያ

9. የክፍያ ሁኔታዎች። አንድ አገልግሎት ከገዙ እነዚህ የክፍ ውሎች ግዢዎ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ ሲሆን በእነሱ ይስማማሉ።

 • ሀ. ለውጦች። የአገልግሎቶቹ የተወሰነ ክፍልን የሚመለከት ክፍያ ካለ ያንን ክፍያ በተጠቀሰው የመገበያያ ገንዘብ የመክፈል ይስማማሉ። ተቃራኒው ካልተደነገገ በስተቀር ለአገልግሎቶቹ የተጠቀሰው ዋጋ ሁሉንም ተፈጻሚ የሚሆኑ ግብሮችና የመገበያያ ገንዘብ ልወጣዎች አያካትትም። ተቃራኒው ካልተደነገገ በስተቀር በ Skype ለሚከፈልባቸው ምርቶች ሁሉም ዋጋዎች ተፈጻሚ የሚሆኑትን ግብሮች ያጠቃልላሉ። እነዚህን ግብሮች ወይም ሌሎች ክፍያዎች የመክፈል ሙሉ ግዴታ አለብዎ። Skype የክፍያ መጠየቂያ መረጃዎ ባለበት የመኖሪያ አድራሻ መሰረት ግብርዎን ያሰላል። ይህ አድራሻ የዘመነ እና ትክክለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ ኃላፊነት ይወስዳሉ። ከSkype ምርቶች ውጭ፣ አካባቢያዊ ሕግ ለስሌቱ የተለየ መሰረት መጠቀምን ያሚያስገድድ ካልሆነ በስተቀር ግብሮች የሚሰሉት የMicrosoft መለያ በሚከፍቱ ጊዜ በነበሩበት ቦታ መሰረት ነው። ከእርስዎ በጊዜው የቀረበ ሙሉ ክፍያ ካልተደረሰን አገልግሎቶቹን ልናግድ ወይም ልንተው እንችላለን። ክፍያ ባለመክፈልዎ ምክንያት የአገልግሎቱ መታገድ ወይም መሰረዝ ወደ መለያዎና ይዘትዎ መዳረሻ እንዳይኖርዎ ወይም መጠቀም እንዳይችሉ ሊያደርግ ይችላል። ከበይነመረብ ጋር በኮርፖሬት ወይም ሊላ የግል አውታረመረብ በኩል መገናኘት አካባቢዎን የሚሸፍን በመሆኑ ክፍያዎች ለትክክለኛው አካባቢዎ ከሚታየው ክፍያ የተለዩ እንዲሆኑ ሊያደርግ ይችላል። አካባቢዎን በሚደብቅ በድርጅት ወይም በሌላ የግል አውታረ መረብ ከበይነመረብ ጋር መገናኘት ለትክክለኛው አካባቢዎ ከሚከፈለው ክፍያ የተለየ ክፍያ ሊያስከፍልዎ ይችላል። በመገኛው ላይ በመመስረት አንዳንድ ግብይቶች የውጪ ምንዛሬ ቅየራ ወይም በሌላ አገር መካሄድን ሊጠይቁ ይችላሉ። ክሬዲት ወይም ዴቢት ካርድ ሲጠቀሙ ባንክዎ ለእነዚህ አገልግሎቶች ተጨማሪ ክፍያዎችን ሊጠይቅዎ ይችላል። እባክዎ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ባንክዎን ያነጋግሩ።
 • ለ. የክፍያ መክፈያ ሂሳብዎ። ለአንድ አገልግሎት ክፍያዎን ለመክፈል ለአገልግሎቱ በሚመዘገቡበት ወቅት የክፍያ መንገድ እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ። የክፍያ መረጃዎን እና የክፍያ ዜዴዎን በ Microsoft የመለያ ማስተዳደሪያ ድር ጣቢያ ላይ እንዲሁም ለSkype ወደ መለያዎ ኆህት በ https://skype.com/go/myaccountላይ በመግባት ማግኘት ይችላሉ። በተጨማሪም Microsoft ባንክዎ የቀረበውን የተመረጠው የክፍያ መንገድ ወይም ተፈጻሚ የሚሆነው የክፍያ አውታረ መረብ በተመለከተ ማናቸውንም የተዘመኑ የመለያ መረጃዎች እንዲጠቀም ለመፍቀድ ተስማምተዋል። ግብይትዎን ማጠናቀቅ እንድንችልና ከግብይቶችዎ ጋር በተያያዘ እንደአስፈላጊነቱ እንድናገኝዎ መለያዎን እንዲሁም የኢሜይል አድራሻንና የክፍያ መንገድዎን ጨምሮ ሌሎች መለያዎችን ቶሎ ቶሎ ለማዘመን ተስማምተዋል። የክፍያ መክፈያ መለያዎ ላይ የተደረጉ ለውጦች በመለያው ላይ የተደረጉ ለውጦች ላይ በምክንያታዊነት እርምጃ እስክንወስድ ድረስ ወደ ክፍያ መክፈያ መለያዎ የምናስገባቸው ክፍያዎች ላይ ምንም ተጽእኖ አያደርሱም።
 • ሐ. የሂሳብ አከፋፈል። ለMicrosoft የክፍያ ዘዴ በማቅረብዎ (i) የክፍያ ዘዴውን የመጠቀም ስልጣን ያለዎ እንደሆነና የሚያቀርቡት ሁሉም የክፍያ መረጃ እውነተኛ እና ትክክለኛ መሆኑን ያረጋግጣሉ። (ii) Microsoft ለአገልግሎቶች ወይም ለቀረቡ ይዘቶች የክፍያ ዘዴዎን ተጠቅሞ ክፍያ እንዲቀበል ፈቃድ ይሰጣሉ፤ እና (iii) Microsoft ለማናቸውም እርስዎ የተመዘገቡባቸው ወይም እነዚህ ውሎች በስራ ላይ እያሉ ለተጠቀሙባቸው የሚከፈልባቸው ባህሪዎች ወይም አገልግሎቶች ክፍያ እንዲቀበል ፈቃድ ይሰጣሉ። ለደንበኝነት ምዝገባ አገልግሎቶች (ሀ) በቅድሚያ (ለ) በገዙበት ወቅት (ሐ) ልክ ከግዢ በኋላ ወይም (መ) በተደጋጋሚ በሚመጣ አከፋፈል እናስከፍልዎታለን። በተጨማሪም እስከፈቀዱት ድረስ ክፍያ ልናስከፍልዎ የምንችል ሲሆን በተደጋጋሚ ለሚከሰቱ የደንበኝነት ምዝገባ አገልግሎቶች በቅድሚያ ማሳወቂያ እንልክልዎታለን። ከአሁን በፊት ላልተጠናቀቁ መጠኖች ከአንድ በላይ ለሆኑ የክፍያ መክፈያ ክፍያዎች በተመሳሳይ ጊዜ ልናስከፍልዎ እንችላለን።
 • መ. በተደጋጋሚ የሚመጡ ክፍያዎች። አገልግሎትን በምዝገባ መሰረት በሚገዙ ጊዜ (ለምሳሌ፣ ወርሃዊ፣ በየሶስት ወሩ ወይም በዓመት)፣ በየጊዜው የሚከፈሉ ክፍያዎች ፈቃድ እየሰጡ መሆኑን ተስማምተዋል፣ በመሆኑም ክፍያዎች በተስማሙበት ክፍለ ጊዜ፣ የዚያ አገልግሎት ምዝገባ ጊዜ በእርስዎ ወይም በMicrosoft እስከሚያበቃ ድረስ ለMicrosoft በዚያ ዘዴ ይከፈላሉ። ተደጋጋሚ ክፍያዎችን በመፍቀድ፣ Microsoft ክፍያዎችን እንደ ኬሌክትሮኒክ ዕዳዎች ወይም የገንዘብ ትልልፍ፣ ወይም ከተጠቀሰው ሂሳቦ ተቀናሽ የሚደረግ ኤሌክትሮኒክ ድራፍት (ለክሊሪንግ ሃውስወይም ተመሳሳይ ክፍያዎች) ወይም ከተጠቀሰው ሂሳብዎ የሚወሰድ ክፍያ (ለክሬዲት ካርድ እና ተመሳሳይ ክፍያዎች) (በአጠቃላይ፣ "ኤሌክትሮኒክ ክፍያዎች")። የምዝገባ ክፍያዎች በአጠቃላይ ከምዝገባው ክፍለ ጊዜ ቀድመው ይከፈላሉ። ማንኛውም ክፍያ ሳይፈጸም ቢመለስ፣ ወይም ማንኛውም ክሬዲት ካርድ ወይም ተመሳሳይ ትራንዛክሽን ቢመለስ ወይም መፈጸም ባይቻል፣ Microsoft ወይም የአገልግሎት አቅራቢዎቹ የተመላሽ ነገሮች፣ ያለመቀበል ወይም በቂ ያልሆነ ገንዘብ መቀጮዎችን የመሰብሰብ መብታቸውን ይጠብቃሉ፣ ይህንንም እንደ ኤሌክትሮኒክ ክፍያ ያከናውናሉ።
 • ሠ. የራስ ሰር እድሳት። የራስ ሰር ዕድሳት የተፈቀደ ከሆነ፣ አገልግሎቶች በትወሰነው የአገልግሎት ጊዜ መጨረሻ በራስ ሰር እንዲታደሱ መምረጥ ይችላሉ። ማናቸውም አገልግሎቶች ለአዲስ ክፍለ ጊዜ ከመታደሳቸው በፊት በኢሜይል ወይም በሌላ ምክንያታዊ የሆነ ዘዴ እናስታውስዎታለን፣ እንዲሁም ማናቸውም አይነት የዋጋ ለውጦች ካሉ በክፍል 9(ቨ) መሰረት እናሳውቅዎታለን። አገልግሎቱን ከዚህ በታች በተገለጸው መሰረት ያልሰረዙት ከሆነ አገልግሎቱን በራስ ሰር ለማዘመን ካስታወስንዎ በኋላ አገልግሎትዎን ከአሁኑ የአገልግሎት ጊዜ በሚያበቃት ወቅት በራስ ሰር የምናድሰው ሲሆን ለታደሰው ጊዜ የወቅቱን ዋጋ እናስከፍልዎታለን። በተጨማሪም ለአገልግሎት እድሳቱ በወቅቱ በእድሳቱ ቀን በፋይል ውስጥ ቢሆንም ወይም ቆይቶ ቢቀርብ ከመረጡትን የክፍያ መንገድ ክፍያውን እንቆርጣለን። በተጨማሪም እንዴት አገልግሎቱን መሰረዝ እንደሚችሉ የሚያሳዩ መመሪያዎችን እንልክልዎታለን። ለእድሳቱ ክፍያ መክፈልን ለማስቀረት አገልግሎቱን ከእድሳት ቀኑ በፊት መሰረዝ አለብዎ።
 • ረ. የመስመር ላይ መግለጫና ስህተቶች። Microsoft መግለጫዎን ለያዩበትና ሊያትሙበት የሚችሉት የመስመር ላይ የሂሳብ መጠየቂያ መግለጫ በ Microsoft የመረያ አስተዳደር ድር ጣቢያ ላይ ያቀርብልዎታል። ለSkype፣ የመስመር ላይ መግለጫዎን ወደ መለያዎ በ www.skype.com ላይ በመግባት ማግኘት ይችላሉ። እኛ የምናቀርበው ብቸኛው የሂሳብ መቀበያ መግለጫ ይሄ ብቻ ነው። በሂሳብዎ ላይ ስህተት ከሰራን ስህተቱ በሂሳብ መጠየቂያው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ከታየበት ቀን ጀምሮ ባሉ 90 ቀናት ውስጥ ለእኛ መንገር አለብዎ። ክፍያውኑ ወዲያውኑ እንመረምረዋለን። በዚያ ጊዜ ውስጥ ካላሳወቁን፣ በህግ ካልተጠየቅን በስተቀር በስህተት ምክንያት ከሚከሰቱ ከሁሉም ሃላፊነቶችና የኪሳራ ክሶች ነጻ ያደረጉን ሲሆን ስህተቱን ለማረም ወይም ገንዘቡን ለመመለስ በህግ አንጠየቅም። Microsoft የሂሳብ መጠየቂያ ስህተት ካገኘ ስህተቱን በ 90-ቀናት ውስጥ እናስተካክለዋለን። ይህ ፖሊሲ ተፈጻሚ ሊሆኑ የሚችሉ ማናቸውም በህግ የተደነገጉ መብቶችን አይነካም።
 • ሰ. ተመላሽ የማድረግ ፖሊሲ። በህግ ወይም በአንድ የተወሰነ የአገልግሎት ጥያቄ ተቃራኒው ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም ግዢዎች የመጨረሻና ተመላሽ የማይደረጉ ናቸው። Microsoft በስህተት ሂሳብ እንዳስከፈልዎ ካመኑ ይህ ክፍያ በተፈጸመበ በ90 ቀናት ውስጥ ለእኛ ማሳወቅ አለብዎ። ህግ ተቃራኒው ካልተጠየቀ በስተቀር 90-ቀን በላይ ለሆናቸው ክፍያዎች ምንም አይነት የክፍያ ተመላሽ አይፈጸምም። በፈቃዳችን ላይ የተመስርተን ተመላሽ ማድረግን ወይም ክሬዲት የመስጠትን መብታችን የተጠበቀ ነው። አንድ ተመላሽ ክፍያ ወይም ክሬዲት ከሰጠን ወደፊት እራሱን ወይም ተመሳሳይ ተመላሽ ክፍያን የመክፈል ግዴታ የለብንም። የተመላሽ መመሪያው ማንኛውንም ተፈጻሚ ሊሆን የሚችሉ በህግ የተደነገጉ መብቶች አይነካም። ለተጨማሪ የተመላሽ ክፍያ መረጃ እባክዎ የእኛን የእገዛ ርዕስ ይጎብኙ። የሚኖሩት በታይዋን ከሆነ እባክዎ በታይዋን የሸማቾች ጥበቃ ህግ እና በተያያዥ ደንቦቹ መሰረት ግዑዝ ባልሆነ ቅጽ እና/ወይም የመስመር ላይ አገልግሎቶች የተገዙ ዲጂታል እቃዎችን የሚመለከቱ ማናቸውም ግዢዎች የመጨረሻ ሲሆኑ ይህ ይዘት ወይም አገልግሎት የተሰጠው በመስመር ላይ ሲሆን ክፍያ ተመላሽ አይደረግባቸውም። ማንኛውንም አይነት የማረጋጊያ ጊዜ ወይም ተመላሽ ክፍያ መጠየቅ አይችሉም።
 • ሸ. አገልግሎቱን መሰረዝ። አንድ አገልግሎትን በማንኛውም ጊዜ በምክንያትም ሆነ ያለምክንያት መሰረዝ ይችላሉ። አገልግሎቱን ለመሰረዝና የሚገባዎ ከሆነ ተመላሽ ክፍያ ለመጠየቅ Microsoft የመለያ አስተዳደር ድሕረ ገፅን ይጎብኙ። እባክዎ ለ Skype እዚህ ጋር የቀረበውን መረጃ በመጠቀም የመውጫ ቅጹን ይሙሉ። አግልግሎቱን ወደሚያብራራው ግብዣ ተመልሰው መመልከት አለብዎ፦ (i) በሚሰርዙበት ጊዜ ተመላሽ አያገኙም፣ (ii) የስረዛ ክፍያዎችን መክፈል ሊጠበቅብዎ ይችላል፣ (iii) ከሰረዙበት ቀን በፊት ወደ ክፍያ ሂሳብዎ የመጡ የክፍያ ጥያቄዎችን የመክፈል ግዴታ ሊኖርብዎ ይችላል፣ እንዲሁም (iv) አገልግሎቱን በሚሰርዙ ጊዜ ወደ መለያዎ ያለዎን መዳረሻ ሊያጡ ይችላሉ፣ ወይም ታይዋን ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ (v) ከሰረዙበት ጊዜ ጀምሮ የሚሰላ ጥቅም ላይ ካልዋለው ክፍያ ጋር እኩል የሆነ ተመላሽ ሊያገኙ ይችላሉ። ውሂብዎን ከዚህ በላይ በክፍል 4 በተቀመጠው መሰረት በሂደት ውስጥ እናሳልፋለን። ከሰረዙ፣ ወደ አገልግሎቱ ያለዎ መዳረሻ በአሁኑ የአገልግሎት ክፍለ ጊዜ ማብቂያ ወይም፣ መለያዎን በክፍለ ጊዜ የምናስከፍል ከሆነ፣ በሰረበት ክፍለ ጊዜ ማብቂያ ላይ ወደ አገልግሎቶቹ ያለዎት መዳረሻ ያበቃል።
 • ቀ. የሙከራ ጊዜ ጥያቄዎች። ተቃራኒውን ካላሳወቅንዎ በስተቀር በማንኛውም የሙከራ ጊዜ ላይ እየተሳተፉ ከሆነ አዳዲስ ክፍያዎችን ለማስወገድ የሙከራ አገልሎቱን(ቶቹን) በሙከራ ጊዜው ማብቂያ ላይ መሰረዝ አለብዎ። የሙከራ አገልግሎቱ(ቶቹ)ን በሙከራ ጊዜው ማብቂያ ድረስ ካልሰረዙት ለአገልግሎቱ(ቶቹ) ክፍያ ልናስከፍልዎ እንችላለን።
 • በ. የማስተዋወቂያ ጥያቄዎች። ከጊዜ ወደ ጊዜ Microsoft አገልግሎቶችን ለሙከራ ጊዜ በነጻ ሊያቀርብ ይችላል። Microsoft (በራሱ ምክንያታዊ ፈቃድ) የግብዣውን ውሎች ያላግባብ እየተጠቅሙበት እንደሆነ ካመነ Microsoft ለእነዚህ አገልግሎቶች (በመደበኛው ተመን) ክፍያ የመጠየቅ መብቱን ይጠብቃል።
 • ቨ. የዋጋ ለውጦች። የአገልግሎቶቹን ዋጋዎች በማንኛውም ጊዜ ልንቀይር እንችላለን፣ ተደጋጋሚ ግዥ ካለዎ፣ በኢሜይል ወይም በሌላ ምክንያታዊ ዘዴ የዋጋ ለውጡ ከመተግበሩ ቢያንስ ከ 15 ቀናት በፊት እናሳውቅዎታለን። በተደረገው የዋጋ ለውጥ የማይስማሙ ከሆነ የዋጋ ለውጡ ተፈጻሚ ከመሆኑ በፊት አገልግሎቱን መጠቀም መተውና ማቆም አለብዎ። ለአገልግሎት ጥያቄዎ ቀድሞ የተወሰነ ውልና ቦታ ካለ ዋጋው ቀድሞ እስከተወሰነው ቀን ድረስ ይቆያል።
 • ተ. ለእርስዎ የሚደረጉ ክፍያዎች። ለእርስዎ መክፈል ያለብን ክፍያዎች ካሉ ያንን ክፍያ ለእርስዎ ለማድረስ ማግኘት ያለንን መረጃ በጊዜና በትክክል እንዲሰጡ ተስማምተዋል። ይህ ክፍያ ለእርስዎ በሚከፈልበት ወቅት ለሚኖሩ ማናቸውም ግብሮችና ክፍያዎች ሃላፊነት ይወስዳሉ። በተጨማሪም ማንኛውንም ክፍያ ለመክፈል እርስዎ ላይ ያደረግናቸውን ማናቸውም ሌሎች ሁኔታዎች ማክበር አለብዎ። በስህተት ክፍያ ከደረስዎ ክፍያውን እንዲመለስልን እንጠይቃለን። ይህንን ለማድረግ በምናደርገው ጥረት ውስጥ ከእኛ ጋር ለመተባበር ይስማማሉ። በተጨማሪም ከአሁን በፊት የተደረገ ትርፍ ክፍያን ለማካካስ ለእርሰዎ የሚደረገውን ክፍያ ያለ ምንም ማሳወቂያ ልናሳንሰው እንችላለን።
 • ቸ. የስጦታ ካርዶች። የስጦታ ካርዶችን (ከ Skype የስጦታ ካርዶች በስተቀር) ክፍያ መጠየቅና መጠቀም በ Microsoft የስጦታ ካርድ ደንቦችና ሁኔታዎች መሰረት ተገዢ ይሆናሉ። የ Skype የስጦታ ካርዶችን የተመለከቱ መረጃዎች በ Skype የእገዛ ገጽ ላይ ማግኘት ይቻላል።
 • ኀ. የባንክ ሂሳብ ክፍያ ዘዴ። ብቁ የሆነ የባንክ ሂሳብን ከMicrosoft መለያዎ ጋር እንደ ክፍያ ዘዴ ማስመዝገብ ይችላሉ። ብቁ የባንክ ሂሳቦች ቀጥተኛ ዴቢት ግቤቶችን መቀበል በሚችሉ የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ ያሉ ሂሳቦችን ያካትታል(ለምሳሌ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ያሉ የራስ ሰር ክሊሪንግ ሃውስ ("ACH")ግቤቶችን የሚደግፉ የፋይናንስ ተቋማት፣ ነጠላ የዩሮ ክፍያ አካባቢ (Single Euro Payments Area)ን የሚደግፉ የአውሮፓ የፋይናንስ ተቋማት ) ("SEPA") ወይም "iDEAL" በኔዘርላንድ ውስጥ)። የብንክ ሂሳብዎን በMicrosoft መለያዎ ውስጥ እንደ ክፍያ ዘዴ በሚያክሉ ጊዜ የተስማሙባቸው ውሎች (ለምሳሌ "ስልጣን" በSEPA ሁኔታ) ተፈጻሚ ይሆናሉ። የተመዘገበው የባንክ ሂሳብዎ በእርስዎ ስም የተያዘ ስለመሆኑና ይህን ባንክ ሂሳብ ለማስመዝገብ እና ለመጠቀም ስልጣን ያለዎ መሆኑን አረጋግጠዋል፣ ዋስትናም ሰጥተዋል። የባንክ ሂሳብዎን በማስመዝገብዎ እና የባንክ ሂሳብዎን እንደ ክፍያ ዘዴ በመምረጥዎ፣ Microsoft (ወይም ወኪሎቹ) ለግዥዎ ወይም ለደንበኝነት ምዝገባ ድምር ክፍያን (በምዝገባዎ አገልግሎት ውሎች መሰረት) አንድ ወይም ከዚያ በላይ ዴቢቶችን ከባንክ ሂሳብዎ (እንዲሁም አስፈላጊ ከሆነ፣ ስህተቶችን ለማረም፣ ተመላሾችን ለመክፈል ወይም ለተመሳሳይ ምክንያት አንድ ወይም ከዚያ በላይ ክሬዲቶችን) እንዲፈጽም ፈቅደዋል፣ እንዲሁም ሂሳብዎን የሚይዘው የፋይናንስ ተቋም እነዚህን ዴቢቶች እንዲቀንስ ወይም ክሬዲቶችን እንዲቀበል ፈቅደዋል። ይህ ፈቃድ የባንክ ሂሳብ መረጃዎን ከMicrosoft መለያ እስከሚያስወግዱ ድረስ ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ የሚሆን ተረድተዋል። በስህተት ክፍያ እንደተጠየቁ ካመኑ ከዚህ በላይ በክፍል 4(መ) በተቀመጠው መሰረት የደበኞች ድጋፍን በተቻለ ፍጥነት ያነጋግሩ። በሃገርዎ ውስጥ ተፈጻሚነት ያላቸው ሕጎች ከባንክ ሂሳብዎ በሚደረጉ የተጭበረበሩ፣ የተሳሳቱ ወይም ፈቃድ የሌላቸውን ግብይቶች ላይ ያለዎትን ተጠያቂነት ሊገድቡ ይችላሉ። በመመዝገብ ወይም የባንክ ሂሳብን እንደክፍያ ዘዴዎ በመምረጥዎ፣ እነዚህን ውሎች አንብበው ተረድተው መስማማትዎን ያረጋግጣሉ።
ሙሉ ጽሁፍ
ተዋዋይ አካል፣ የህግ ምርጫና ችግሮችን የመቅረፊያ አካባቢ ቦታተዋዋይ አካል፣ የህግ ምርጫና ችግሮችን የመቅረፊያ አካባቢ ቦታ10_11_contractingEntityChoiceOfLaw
ማጠቃለያ

10. ተዋዋይ አካል፣ የህግ ምርጫና ችግሮችን የመቅረፊያ አካባቢ ቦታ። ለነጻ እና የክፍያ የተጠቃሚ የSkype ብራንድ ላላቸው አገልግሎቶች፣ እርስዎ ውል የሚገቡት፣ እንዲሁም በእነዚህ ውሎች ውስጥ “Microsoft” ተብሎ የሚጠቀሰው ሁሉ፣ Skype Communications S.à.r.l, 23 – 29 Rives de Clausen, L-2165 Luxembourg. ማለት ነው ለነጻ ወይም ለሚከፈልባቸው የተጠቃሚ የ Skype-የንግድ ምልክት ላለባቸው አገልግሎቶች፣ የህግ መርሆች አለመጣጣም ቢኖርም ባይኖርም፣ የአለም አቀፍ የግለሰቦች ህግ ድንጋጌ ምንም ይሆን ምን የሉክሰምበርግ ህግ የእነዚህን የአገልግሎት ውሎች ይተረጉማል።አተረጓጎምና ተጥሰው ሲገኙ የይገባኛል ጥያቄዎች ላይ ገዢ ህግ ይሆናል። እርስዎ የሚኖሩበት አገር ወይም ክልል ህጎች ሌሎች የይገባኛል ጥያቄዎች ላይ በጠቅላላ ገዢ ህግ ይሆናል (የተጠቃሚዎች ጥበቃ፣ ተገቢ ያልሆነ ውድድርና ከውል ውጪ የሚነሱ ሃላፊነቶች ክሶች)። እነዚህን የአገልግሎት ውሎች የ Skype መለያ በመፍጠር ወይም Skype በመጠቀም ከተቀበሉ እርስዎና እኛ መልሰን መቀልበስ በማንችለው መልኩ በእነዚህ የአገልግሎት ውሎች ወይም ከተጠቃሚ የSkype ንግድ ምልክት ያለባቸው አገልግሎቶች ውስጥ ለሚመነጩ ማናቸውም ግጭቶች የሉክሰምበርግ ፍርድ ቤቶች ባላቸው ጠቅላይ የፍርድ ስልጣንና ቦታ ተስማምተናል። ለሁሉም ሌሎች አገልግሎቶች እነዚህን የአገልግሎት ውሎች የ Microsoft መለያ በመፍጠር ወይም ሌሎች ማናቸውንም አገልግሎቶች በመጠቀም ከተስማሙ እየተዋዋሉ ያሉት ተቋም፣ ገዢው ህግ እንዲሁም ግጭቶች የሚፈቱበት ቦታ ከዚህ በታች ይታያሉ:

 • ሀ. ካናዳ። መኖሪያዎ (ወይም ድርጅት ከሆነ የድርጅቱ ዋና የንግድ ቦታ) ካናዳ ውስጥ ከሆነ የሚዋዋሉት ከ Microsoft Corporation, One Microsoft Way, Redmond, WA 98052, U.S.A ጋር ነው። የሚኖሩበት ክልል ህጎች (ወይም ድርጅት ከሆነ የድርጅቱ ዋና የንግድ ቦታ)፣ የህግ መርሆች አለመጣጣም ቢኖርም ባይኖርም፣ የአለም አቀፍ የግለሰብ ህግ መርሆች ምንም ይሉ ምን የእነዚህን የአገልግሎት ውሎች አተረጓጎም፣ ተጥሰው ሲገኙ እነሱን የተመለከቱ ክሶች፣ እንዲሁም ሁሉም ሌሎች ክሶች (የተጠቃሚዎች ጥበቃ፣ ተገቢ ያልሆነ ውድድርና ከውል ውጪ የሚነሱ ሃላፊነቶች ክሶች)ላይ ገዢ ህግ ይሆናሉ። እርስዎና እኛ መልሰን መቀልበስ በማንችለው መልኩ በእነዚህ የአገልግሎት ውሎች ወይም ከአገልግሎቶቹ ውስጥ ለሚመነጩ ማናቸውም ግጭቶች የኦንታሪዮ ፍርድ ቤቶች ባላቸው ጠቅላይ የፍርድ ስልጣንና ቦታ ተስማምተናል።
 • ለ. ከዩናይትድ ስቴትስና ከካናዳ ውጪ የሆኑ ሰሜን ወይም ደቡብ አሜሪካ። መኖሪያዎ (ወይም ድርጅት ከሆነ የድርጅቱ ዋና የንግድ ቦታ) ከዩናይትድ ስቴትስና ከካናዳ ውጪ የሆኑ ሰሜን ወይም ደቡብ አሜሪካ ውስጥ ከሆነ የሚዋዋሉት ከ Microsoft Corporation, One Microsoft Way, Redmond, WA 98052, U.S.A ጋር ነው። የዋሺንግተን ግዛት ህጎች የህግ ምርጫ መርሆች ምንም ይሉ ምን የእነዚህን የአገልግሎት ውሎች አተረጓጎም፣ ተጥሰው ሲገኙ እነሱን የተመለከቱ ክሶች ላይ ገዢ ህግ ይሆናሉ። አገልግሎቶችዎን የምንልክበት አገር ህጎች ሌሎች ክሶች (የተጠቃሚዎች ጥበቃ፣ ተገቢ ያልሆነ ውድድርና ከውል ውጪ የሚነሱ ሃላፊነቶች ክሶች) ላይ ገዢ ህግ ይሆናሉ ።
 • ሐ. መካከለኛው ምስራቅ ወይም አፍሪካ። መኖሪያዎ (ወይም ድርጅት ከሆነ የድርጅቱ ዋና የንግድ ቦታ) መካከለኛው ምስራቅ ወይም አፍሪካ ከሆነና የአገልግሎቶቹን ነጻ የሆኑ ክፍሎች (እንደ Bing እና MSN) እየተጠቀሙ ከሆነ የሚዋዋሉት ከ Microsoft Corporation, One Microsoft Way, Redmond, WA 98052, U.S.A ጋር ነው። የአገልግሎቱን አንድ ክፍል ለመጠቀም ከከፈሉ እየተዋዋሉ ያሉት ከ Microsoft Ireland Operations Limited, One Microsoft Place, South County Business Park, Leopardstown, Dublin 18, Ireland ጋር ነው። ለነጻና ለሚከፈልባቸው አገልግሎቶች፣ የህግ መርሆች አለመጣጣም ቢኖርም ባይኖርም፣ የአየርላንድ ህጎች የአለም አቀፍ የግለሰብ ህግ መርሆች ምንም ይሉ ምን የእነዚህ የአገልግሎት ውሎች አተረጓጎም፣ ተጥሰው ሲገኙ እነሱን የተመለከቱ ክሶች ላይ ገዢ ህግ ይሆናሉ። አገልግሎቶችዎን የምንልክበት አገር ህጎች ሌሎች ክሶች (የተጠቃሚዎች ጥበቃ፣ ተገቢ ያልሆነ ውድድርና ከውል ውጪ የሚነሱ ሃላፊነቶች ክሶች) ላይ ገዢ ህግ ይሆናሉ ። እርስዎና እኛ መልሰን መቀልበስ በማንችለው መልኩ በእነዚህ የአገልግሎት ውሎች ወይም ከአገልግሎቶቹ ውስጥ ለሚመነጩ ማናቸውም ግጭቶች የአየርላንድ ፍርድ ቤቶች ባላቸው ጠቅላይ የፍርድ ስልጣንና ቦታ ተስማምተናል።
 • መ. አገርዎ ከዚህ በታች በግልጽ ካልተጠቀሰ በስተቀር እስያ ወይም ደቡብ ፓሲፊክ። እርስዎ በእስያ (ከቻይና፣ ጃፓን፣ የኮሪያ ሪፑብሊክ፣ ወይም ታይዋን በስተቀር) ወይም ደቡባዊ ፓሲፊክ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ (ወይም መቀመጫውን በዚያው ያደረገ የንግድ ሥራ) እና የአገልግሎቶቹን ክፍሎች የሚጠቀሙ ከሆነ (ለምሳሌ Bing እና MSN)፣ እርስዎ ውል የሚገቡት ከMicrosoft Corporation, One Microsoft Way, Redmond, WA 98052, U.S.A. ጋር ይሆናል። የአገልግሎቶቹን አካል ለመጠቀም ክፍያ ከፈጸሙ፣ ወይም ነጻውን የOutlook.com አገልግሎት በSingapore ወይም Hong Kong የሚጠቀሙ ከሆነ፣ እርስዎ ውል የሚገቡት ከMicrosoft Regional Sales Corp. ጋር ነው፤ ይኽም በኔቫዳ፣ ዩ ኤስ ኤ ግዛት ሕጎች መሰረት የተቋቋመ፣ ቅርንጫፎቹ በHong Kong እና Singapore ያደረገና መቀመጫውም በ438B Alexandra Road, #04-09/12, Block B, Alexandra Technopark, Singapore, 119968 የሆነ ነው። ይኽ የሚሆነው ግን በ አውስትራሊያ የሚኖሩ ከሆነ (ወይም መቀመጫው በዚያ የሆነ የንግድ ሥራ ከሆኑ) ውል የሚገቡት ከMicrosoft Pty Ltd, 1 Epping Road, North Ryde, NSW 2113, Australia ጋር ነው። ወይም በኒውዚላንድ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ (ወይም መቀመጫው በዚያ የሆነ የግንድ ሥራ ከሆኑ) ውል የሚገቡት ከ Microsoft New Zealand Limited, Level 5, 22 Viaduct Harbour Avenue, PO Box 8070 Symonds Street, Auckland, 1150 New Zealand. ጋር ይሆናል። ለነጻ እና የክፍያ አገልግሎቶች፣ የሕጎችና መርኆች መጣረስ ቢኖርም ባይኖርም፣ የእነዚህን ውሎች ትርጉም በዋሽንግተን ግዛት ሕግ ይገዛል፣ እንዲሁም ሲጣሱም ይጠይቃል። አገልግሎቶችዎን የምንልክበት አገር ህጎች ሌሎች ክሶች (የተጠቃሚዎች ጥበቃ፣ ተገቢ ያልሆነ ውድድርና ከውል ውጪ የሚነሱ ሃላፊነቶች ክሶች) ላይ ገዢ ህግ ይሆናሉ። ከእነዚህ የአገልግሎት ውሎች ወይም ከSkype ባሻገር ካሉት አገልግሎቶች ውስጥ ወይም ከእነርሱ ጋር በተያያዘ ለሚነሱ ማንኛቸውም አለመግባባቶች፣ የአገልግሎቶቹን መኖር፣ ትክክለኝነት ወይም መቋረጥ ጨምሮ፣ ወደ ሲንጋፖር ይመራና ደንቦቹ በዚህ አንቀጽ መሰረት ከነዚህ ደንቦች ጋር እንደተካተተ በሚቆጠረው በሲንጋፖር አለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ማዕከል (SIAC) የግልግም ህጎች መሰረት የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጥባቸዋል። ችሎቱ በ SIAC ፕሬዚደንት የሚመረጥ አንድ የግልግል ዳኛ ይኖረዋል። የግልግል ዳኝነት ችሎቱ ቋንቋ እንግሊዘኛ ይሆናል። የግልግል ዳኛው ውሳኔ የመጨረሻ፣ አስገዳጅና ይግባኝ ሊቀርብበት የማይችል ሲሆን በማንኛውም አገር ወይም ክልል ውስጥ የውሳኔ መሰረት ሊሆን የሚችል ነው።
 • ሠ. ጃፓን። መኖሪያዎ (ወይም ድርጅት ከሆነ የድርጅቱ ዋና የንግድ ቦታ) በጃፓን ከሆነና የአገልግሎቶቹን ነጻ የሆኑ ክፍሎች (እንደ Bing እና MSN) እየተጠቀሙ ከሆነ የሚዋዋሉት ከ Microsoft Corporation, One Microsoft Way, Redmond, WA 98052, U.S.A ጋር ነው። የአገልግሎቱን አንድ ክፍል ለመጠቀም ከከፈሉ እየተዋዋሉ ያሉት ከ Microsoft Japan Co., Ltd (MSKK), Shinagawa Grand Central Tower, 2-16-3 Konan Minato-ku, Tokyo 108-0075 ጋር ነው። ለነጻና ለሚከፈልባቸው አገልግሎቶች የእነዚህን የአገልግሎት ውሎች እንዲሁም ከውሎቹ ወይም ከአገልገሎቶቹ የሚመነጩ ማናቸውን ጉዳዮች የጃፓን ህጎች ገዢ ህግ ይሆናሉ። እርስዎና እኛ መልሰን መቀልበስ በማንችለው መልኩ በእነዚህ የአገልግሎት ውሎች ወይም ከአገልግሎቶቹ ውስጥ ለሚመነጩ ማናቸውም ግጭቶች የቶኪዮ ዲስትሪክት ፍርድ ቤቶች ባላቸው ጠቅላይ የፍርድ ስልጣንና ቦታ ተስማምተናል።
 • ረ. የኮሪያ ሪፐብሊክ። መኖሪያዎ (ወይም ድርጅት ከሆነ የድርጅቱ ዋና የንግድ ቦታ) በኮሪያ ሪፐብሊክ ከሆነና የአገልግሎቶቹን ነጻ የሆኑ ክፍሎች (እንደ Bing እና MSN) እየተጠቀሙ ከሆነ የሚዋዋሉት ከ Microsoft Corporation, One Microsoft Way, Redmond, WA 98052, U.S.A ጋር ነው። የአገልግሎቱን አንድ ክፍል ለመጠቀም ከከፈሉ እየተዋዋሉ ያሉት ከ Microsoft Korea, Inc., 11th Floor, Tower A, K-Twin Tower, Jongro 1 gil 50, Jongro-gu, Seoul, Republic of Korea, 110-150 ጋር ነው። ለነጻና ለሚከፈልባቸው አገልግሎቶች የእነዚህን የአገልግሎት ውሎች እንዲሁም ከውሎቹ ወይም ከአገልገሎቶቹ የሚመነጩ ማናቸውን ጉዳዮች የኮሪያ ህጎች ገዢ ህግ ይሆናሉ። እርስዎና እኛ መልሰን መቀልበስ በማንችለው መልኩ በእነዚህ የአገልግሎት ውሎች ወይም ከአገልግሎቶቹ ውስጥ ለሚመነጩ ማናቸውም ግጭቶች የሲኦል ሴንትራል ዲስትሪክት ፍርድ ቤቶች ባላቸው ጠቅላይ የፍርድ ስልጣንና ቦታ ተስማምተናል።
 • ሰ. ታይዋን። መኖሪያዎ (ወይም ድርጅት ከሆነ የድርጅቱ ዋና የንግድ ቦታ) በታይዋን ከሆነና የአገልግሎቶቹን ነጻ የሆኑ ክፍሎች (እንደ Bing እና MSN) እየተጠቀሙ ከሆነ የሚዋዋሉት ከ Microsoft Corporation, One Microsoft Way, Redmond, WA 98052, U.S.A ጋር ነው። የአገልግሎቱን አንድ ክፍል ለመጠቀም ከከፈሉ እየተዋዋሉ ያሉት ከ Microsoft Taiwan Corp., 18F, No. 68, Sec. 5, Zhongxiao E. Rd., Xinyi District, Taipei 11065, Taiwan ጋር ነው። ለነጻና ለሚከፈልባቸው አገልግሎቶች የእነዚህን የአገልግሎት ውሎች እንዲሁም ከውሎቹ ወይም ከአገልገሎቶቹ የሚመነጩ ማናቸውን ጉዳዮች የታይዋን ህጎች ገዢ ህግ ይሆናሉ። ስለ Microsoft Taiwan Corp. ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እባክዎ በ Ministry of Economic Affairs R.O.C. የቀረበውን ድረ ገጽ ይመልከቱ። እርስዎና እኛ መልሰን መቀልበስ በማንችለው መልኩ በእነዚህ የአገልግሎት ውሎች ወይም ከአገልግሎቶቹ ውስጥ ለሚመነጩ ማናቸውም ግጭቶች የታይዋን ህግ እስከሚፈቅደው ከፍተኛ ድረስ የታፔይ ዲስትሪክት ፍርድ ቤት እንደ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስልጣን እንዲኖረው ተስማምተናል።

በአካባቢዎ ያለው ደንበኛዎ እነዚህ ደንቦች ቢኖሩም እንኳን የተወሰኑ የአካባቢው ህጎች ለመዳኘት ሊጠይቅ ወይም አለመግባባቱን በሌላ ቦታ እንዲፈቱ መብት ሊሰጥዎ ይችላል። ይህ በሚሆንበት ጊዜ የካባቢዎ የተጠቃሚዎች ህግ እስከሚፈቅደው ድረስ በክፍል 10 ውስጥ የተደነገጉት የህግና የቦታ ምርጫ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ።

ሙሉ ጽሁፍ
ዋስትናዎችዋስትናዎች12_Warranties
ማጠቃለያ

11. ዋስትናዎች።

 • ሀ. MICROSOFT እና አጋሮቻችን፣ ሻጮቻችን፣ አከፋፋዮቻችን እና ቸርቻሪዎቻችን የአገልግሎቱን አጠቃቀምዎን በተመለከተ በግልጽም ይሁን በምልከታ ምንም አይነት ዋስትናዎቻንና ሁኔታዎችን አይሰጡም። አገልግሎቱን የሚጠቀሙት በራስዎ ሃላፊነት እንደሆነና እኛ አገልግሎቱን የምናቀርበው "እንዳለ" "ከነ እንከኖቹ" እና "እንደቀረበው" መሆኑን ይረዳሉ። Microsoft ለአገልግሎቶቹ በጊዜ መድረስ እና ትክክለኝነት ዋስትና አይሰጥም። በአካባቢዎ ህግ ስር የተወሰኑ መብቶች ሊኖርዎት ይችላል። በእነዚህ ደንቦች ውስጥ ያለ ማንኛውም ነገር ተፈጻሚ የሆኑትን መብቶዎን ለመንካት የታቀደ አይደለም። ኮምፒውተርና የቴሌኮሙኒኬሽን ስርዓቶች ከእንከን ነጻ እንዳልሆኑና አልፎ አልፎ የአገልግሎት በቋረጦች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ይገነዘባሉ። አገልግሎቶቹ የማይቆረረጡ፣ በሚፈለጉበት ጊዜ የማይደርሱ፣ አስተማማኝ ወይም ስህተት አልባ እንደሚሆኑ ዋስትና አንሰጥም። በተጨማሪም ከኮምፒውተር አውታ መረቦች ጋር ማንኛውንም ግንኙነት ወይም ስርጭት እንደሚኖር ዋስትና አንሰጥም።
 • ለ. በአካባቢዎ ህግ እስከሚፈቀደው ድረስ ማንኛውንም አይነት በተዘዋዋሪ የተመለከቱ ዋስትናዎችን አናካትትም። ይህም የመልሶ መሸጥ መቻል፣ የአመርቂ ጥራት፣ ለአንድ የተወሰነ አገልግሎት ብቁነት፣ በሚጠበቅበት የመስራት ብቃት ማገልገል መቻሉን እና የሌሎችን መብት እንደማይጥስ ዋስትና አለመስጠትን ያካትታል።
 • ሐ. በአውስትራሊያ ለሚኖሩ ተጠቃሚዎች: ሸቀጦቻችን በአውስትራሊያ የተጠቃሚዎች ህግ ከሽፋን ውጪ ከማይሆኑ ዋስትናዎች ጋር ይመጣሉ። ከበድ ያለ ብልሽት ካጋጠመዎት ምትክ እቃ የሚሰጥዎ ወይም ገንዘብዎ ተመላሽ የሚደረግልዎት ሲሆን ለሌሎች ምክንያታቂ ሊገመቱ የሚችሉ ጉዳቶች ወይም ብልሽቶች ደግሞ ካሳ ይሰጥዎታል። የገዙት እቃ ተቀባይነት ያለው የጥራት ደረጃ ከሌለውና ብልሽቱ ከባድ ብልሽት ሊባል የማይችል ከሆነ እቃው እቃው ይጠገንልዎታል ወይም ይለወጥልዎታል።
 • መ. በኒውዚላንድ ለሚኖሩ ደንበኞች በኒውዚላንድ የተጠቃሚዎች ዋስትና ህግ መሰረት የተደነገጉ መብቶች ሊኖርዎ የሚችለስ ሲሆን በነዚህ ደንቦች ውስጥ ያለ ማንኛውም ነገር እነሱን መብቶችዎን ለመንካት የታቀደ አይደለም።
ሙሉ ጽሁፍ
የሃላፊነት ገደብየሃላፊነት ገደብ13_limitationOfLiability
ማጠቃለያ

12. የሃላፊነት ገደብ።

 • ሀ. ጥፋቶችን ለመመለስ ማንኛውም አይነት መሰረት ካለዎ (እነዚህን ውሎች መጣስን ጨምሮ)፣ ተፈጻሚነት ባለው ሕግ እስከሚፈቀደው ድረስ፣ ብቸኛው መድህን ከMicrosoft ወይም ከማናቸውም አጋሮች፣ አከፋፋዮች፣ አሰራጮች፣ ሶስተኛ ወገን መተግበሪያ እና አገልግሎት አቅራቢዎች እና ሻጮች፣ ቀጥተኛ ጥፋቶች ጥፋቱ ለደረሰበት ወር አገልግሎት ከከፈሉት ዋጋ ጋር እኩል የሆነ መጠን (ወይም አገልግሎቱ ነሳ ከሆነ እስከ የአሜሪካ$10) መመለስ ብቻ እንደሆነ ይረዳሉ።
 • ለ. በህግ እስከሚፈቀደው ድረስ የሚከተሉትን መጠየቅ አይችሉም (i) ተከትለው የሚመጡ ኪሳራዎችን ወይም ጉዳቶችን፤ (ii) የደረሰ ወይም የሚጠበቅ ትርፍ ማጣት (ቀጥተኛም ይሁን ተዘዋዋሪ)፤ (iii) የደረሰ ወይም የሚጠበቅ ገቢ ማጣት (ቀጥተኛም ይሁን ተዘዋዋሪ)፤ (iv) አገልግሎቱን የግል ባልሆነ አቅም በመጠቀምዎ የተከሰተ የውል ወይም የንግድ ስራ ወይም ሌላ ኪሳራ ወይም ጉዳት ፤ (v) ልዩ፣ ተዘዋዋሪ፣ ድንገተኛ የሆነ ወይም የቅጣ ኪሳራዎች ወይም ጉዳቶች፤ እና (vi) በህግ በሚፈቀደው መጠን ከዚህ በላይ በቁጥር 12(ሀ) ላይ ከተቀመጠው ገደብ በላይ የሆነ ቀጥተኛ ኪሳራዎችና ጉዳቶች። እነዚህ ገደቦችና ከሽፋን ክልል ውጪ ማድረጊያዎች ተፈጻሚ የሚሆኑት ይህ ካሳ ለማንኛውም ጉዳት ሙሉ በሙሉ የማይክስዎ ከሆነ ወይም ወሳኝ የሆነ አላማውን ካላሳካ ወይም ጉዳቱ ሊደርስ እንደሚችል ስናውቅ ወይም ማወቅ ሲኖርብን ነው። በህግ እስከሚፈቀደው ከፍተኛው መጠን ድረስ እነዚህ ገደቦችና አለማካተቶች ከእነዚህ ደንቦች፣ አገልግሎቶች ወይም ከአገልግሎቱ ጋር ተዛማጅ ሶፍትዌሮች ጋር ለሚገናኙ ማናቸውን ነገሮች ወይም ክሶች ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ።
 • ሐ. የመስራት ችግር ወይም መዘግየት የተከሰተው ከ Microsoft ምክንያታዊ ቁጥጥር በላይ በሆኑ ሁኔታዎች ምክንያት ከሆነ (እንደ የአሰሪና ሰራተኛ አለመግባባቶች፣ የእግዚያብሄር ስራዎች፣ ጦርነት ወይም የሽብርተኝነት እንቅስቃሴ፣ ተንኮል አዘል ጉዳት፣ ድንገተኛ አደጋዎች ወይም ከማንኛውም ተፈጻሚ የሆነ ህግ ወይም የመንግስት ትእዛዝን ማክበር የመሳሰሉ) Microsoft ለእነዚህ የመስራት ችግሮች ወይም መዘግየቶች ተጠያቂ አይሆንም። Microsoft የእነዚህን ክስተቶች አሉታዊ ውጤት ለመቀነስና ተጽእኖ ያልተደረገባቸውን ሃላፊነቶች ለመወጣት የተቻለውን ጥረት ሁሉ ያደርጋል።
ሙሉ ጽሁፍ
ለአገልግሎት የተወሰኑ ደንቦችለአገልግሎት የተወሰኑ ደንቦች14_service-SpecificTerms
ማጠቃለያ

13. ለአገልግሎት የተወሰኑ ደንቦች። ከክፍል 13 በፊትና በኋላ ያሉት ደንቦች በአጠቃላይ ለሁሉም አገልግሎቶች ተፈጻሚ ይሆናሉ። ይህ ክፍል ከአጠቃላይ ደንቦቹ ተጨማሪ የሆኑ ለአንድ አገልግሎት የተወሰኑ ደንቦችን ያካትታል። እነዚህ አገልግሎት-አቀፍ ውሎች ከአጠቃላይ ውሎቹ ጋር ግጭት በሚፈጠር ጊዜ ገዥዎች ይሆናሉ።

ሙሉ ጽሁፍ
Xbox Live እና Microsoft Studios ጨዋታዎችና መተግበሪያዎችXbox Live እና Microsoft Studios ጨዋታዎችና መተግበሪያዎች14a_XboxLive
ማጠቃለያ
 • ሀ. Xbox Live እና Microsoft Studios ጨዋታዎችና መተግበሪያዎች።
  • i. የግል ንግድ ያልሆነ አገልግሎት። Xbox Live፣ የ Windows Live ጨዋታዎች እና Microsoft Studios ጨዋታዎች፣ መተግበሪያዎች፣ አገልግሎቶችና በ Microsoft የቀረቡ ይዘቶች (በአጠቃላይ የ"Xbox አገልግሎቶች" ተብለው የሚጠሩት) ለግልዎና ለንግድ አላማ ላልሆኑ አገልግሎቶች ብቻ የሚውሉ ናቸው።
  • ii. Xbox አገልግሎቶች። ለ Xbox Live ሲመዘገቡ እና/ወይም Xbox አገልግሎቶችን ሲቀበሉ፣ Microsoft እና ሶስተኛ ወገን የጨዋታ አልሚዎች ጨዋታቸውን እንዲያከናውኑ እና የXbox አገልግሎቶችን መስጠት እንዲችሉ የእርስዎን የጨዋታ አጨዋወት፣ እንቅስቃሴዎች እና የXbox ጨዋታ አጠቃቀምዎ ክትትል ይደረግበታል እንዲሁም አግባብነት ላላቸው የሶስተኛ ወገን የጨዋታ አልሚዎች ይጋራል። የ Microsoft Xbox አገልግሎቶች መለያዎን የ Microsoft ያልሆነ አገልግሎት ላይ ካለ መለያዎ ጋር (ለምሳሌ የሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎች እና አገልግሎቶች የ Microsoft ያልሆነ ጨዋታ አዘጋጅ) በሚከተለው ይስማማሉ: (ሀ) Microsoft የተገደበ የመለያ መረጃን (የተጫዋች መለያን፣ የተጫዋች ውጤትን፣ የጨዋታ መለያን፣ የጨዋታ ታሪክን እና የጓደኞች ዝርዝርን ጨምሮ) በ Microsoft የግላዊነት መግለጫ ላይ በመመስረት የ Microsoft ካልሆነው አካል ጋር ሊያጋራ ይችላል፤ እንዲሁም (ለ) በ Xbox የግላዊነት ቅንብርዎ የሚፈቀድለት ከሆነ የ Microsoft ያልሆነው ወገን በዚያ የMicrosoft ያልሆነ መለያ በሚገቡበት ወቅት ከጨዋታ ውስጥ ግንኙነቶችዎ ወደ እርስዎ ይዘት መዳረሻ ሊኖረው ይችላል። በተጨማሪም፣ በእርስዎ የXbox ግላዊነት ቅንብሮች የሚፈቀድ ከሆነ፣ Microsoft የእርስዎን ስም፣ የጨዋታ መለያ፣ የተጫዋች ምስል፣ መፈክር፣ አምሳያ፣ የጨዋታ ቅንጥቦች እና እርስዎ የተጫወቷቸውን ጨዋታዎች በግንኙነት ውስጥ እርስዎ ለሚፈቅዱላቸው ሰዎች ሊያትም ይችላል።
  • iii. የእርስዎ ይዘት። የXbox አገግሎቶች ማኀብረሰብን የመፍጠሩ ሂደት አንድ አካል እንደመሆኑ፣ ለMicrosoft እና አጋሮቹ ይዘትዎን የመጠቀም፣ የማሻሻል፣ ዳግም የመስራት፣ የማሰራጨት፣ የማጋራት እና ይዘትዎን ወይም ስምዎን፣ የተጫዋች መሰየሚያ፣ መፈክር፣ ወይም አምሳያ የማሳየት ነጻ እና ዓለምአቀፋዊ መብት ይሰጣሉ።
  • iv. የጨዋታ አስተዳዳሪዎች። አንዳንድ ጨዋታዎች የጨዋታ አስተዳዳሪዎችንና አስተናጋጆችን ሊጠቀሙ ይችላሉ። የጨዋታ አስተዳዳሪዎችና አስተናጋጆች ስልጣን የተሰጣቸው የ Microsoft ወኪሎች አይደሉም። የእነሱ አስተያየቶች የ Microsoft አስተያየት ላይሆን ይችላል።
  • v. ህጻናት በ Xbox ላይ። Xbox Live የሚጠቀሙ እድሜዎ 18 ያልሆነ ወጣት ከሆኑ ወላጅዎ ወይም አሳዳጊዎ የመለያዎ በርካታ ክፍሎች ላይ ቁጥጥር ሊኖራቸው የሚችል ሲሆን የ Xbox Live አጠቃቀምዎን በተመለከተ ሪፐርቶች ይደርሷቸው ይሆናል።
  • vi. የጨዋታ መገበያያ ወይም ምናባዊ እቃዎች። አገልግሎቶቸቹ ምናባዊ የሆኑ የጨዋታ የመገበያያ ገንዘብ (እንደ ወርቅ፣ ሳንቲም ወይም ነጥቦች የመሳሰሉ) በሚኖሩበት አካባቢ "አዋቂ" የመሆን እድሜን ያለፉ ከሆነ በእውነተኛ ገንዘቦች ከ Microsoft ሊገዟቸው የሚችሉ ነገሮች አሏቸው። አገልግሎቱ በተጨማሪም ከMicrosoft እውነተኛ ገንዘብን ወይም የጨዋታ መገበያያ ገንዘብን በመጠቀም ሊገዟቸው የሚችሉ ምናባዊ ዲጂታል ነገሮችን ወይም እቃዎችን ሊያካትት ይችላል። የጨወዋታ መገበያያ ገንዘቦችና ምናባዊ እቃዎች ከMicrosoft ወይም ከማንኛውም ሌላ ወገን በእውነተኛ መገበያያ ገንዘብ፣ እቃዎች ወይም ሌሎች የገንዘብ ዋጋ ያላቸው ነገሮች ሊለወጡ አይችሉም። የጨዋታ መገበያያውንና ምናባዊ እቃዎቹን በአገልግሎቶቹ ውስጥ ብቻ ከመጠቀም የተገደበ፣ የግል ከሆነ፣ ሊነጠቅ ከሚችል፣ ሊተላለፍ ከማይችልና ለሌላ አካል በንኡስ ፈቃድ ሊሰጥ ከማይችል መብት በስተቀር በእነዚህ በአገልግሎቱ ውስጥ በሚታዩ ወይም በሚመነጩ ወይም ከአገልግሎቱ አጠቃቀም ጋር ከሚዛመዱ ወይም በአገልግሎቱ ውስጥ ለተከማቹ የጨዋታ መገበያያ ገንዘቦች ወይም ምናባዊ እቃዎች ላይ ምን አይነት መብት ወይም ባለቤትነት የልዎትም። Microsoft በማንኛውም ጊዜ የጨዋታ መገበያያ ገንዘቡን እና/ወይም ምናባዊ እቃዎቹን እንደአስፈላጊ ነው ብሎ እንዳሰበው ሊቆጣጠራቸው፣ ሊያስተካክላቸው ይችላል።
  • vii. የሶፍትዌር ማዘመኛዎች። ከXbox አገልግሎቶች ጋር መገናኘት ለሚችሉ ማንኛውም መሳሪያ፣ የእርስዎን የXbox ኮንሶል ሶፍትዌር ስሪት ወይም Xbox መተግበሪያ ሶፍትዌርን በራስ ሰር ልንፈትሽ፣ እንዲሁም የXbox ኮንሶል ወይም የXbox ሶፍትዌር ማዘመኛዎችን ወይም የቅወቃቀር ለውጦችን፣ እርስዎ Xbox ዘንድ እንዳይደርሱ፣ ፈቃድ ያልተሰጣቸው የXbox ጨዋታዎችን ወይም መተግበሪያዎችን፣ ፈቃድ ያልተሰጣቸው ሃርድዌሮች እና በXbox ላይ ተሰኪዎችን ሊከለክሉ የሚችሉትን ጨምሮ ልናወርድ እንችላለን።
  • viii. የተጫዋች ስያሜ ጊዜ ማብቂያ። በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ቢያንስ አንድ ጊዜ ወደ Xbox አገልግሎቶች መግባት አለብዎ፣ ያ ካልሆነ ከመለያዎ ጋር ተዛማጅ የሆነውን የተጫዋች ስያሜ ሊያጡ ይችላሉ፣ እንዲሁም ያ ስያሜ ለሌሎች ተጠቃሚዎች እንዲጠቀሙበት ሊፈቀድ ይችላል።
  • ix. መድረክ። መድረክ የXbox Microsoft ወይም ሶስተኛ ወገን መሳተፍ ወይም አንዳንድ ጊዜም ሽልማት የሚያሰጡ የቪዲዮ ጨዋታ ውድድሮችን መፍጠር እንዲችሉ የሚያደርጉበት አገልግሎት ነው። ("ውድድር")። የእርስዎ መድረክ ለእነዚህ ውሎች ተገዥ ነው፣ በተጨማሪም በሚመዘገቡ ጊዜ በውድድር አዘጋጁ የተቀመጡ የውድድር ውሎችን፣ ሁኔታዎችን እና ደንቦችን እንዲቀበሉ ሊጠበቅብዎት ይችላል።("የውድድር ውሎች")። የብቁነት ደንቦች ተፈጻሚነት ሊኖራቸው ይችላል፣ እንደ አካባቢው ሁኔታም ሊለያዩ ይችላሉ። የሕግ ክልከላ ባለበት አካባቢ ውድድሮች ዋጋ አይኖራቸውም። እነዚህን ውሎች (የስነምግባር ደንብን ጨምሮ) ወይም የውድድር ውሎችን አለማክበር ቅጣትን ወይም ከውድድር ውጭ መሆንን ሊያስከትል ይችላል። ውድድር ከፈጠሩ፣ Microsoft (በራሱ ፈቃድ) ከእነዚህ ውሎች ጋር የሚጣረሱ እንደሆኑ የወሰናቸው ሌሎች ውሎች አያስፈልጉዎትም። Microsoft ማናቸውንም ውድድሮች በማንኛውም ጊዜ የመሰረዝ መብቱን ይጠብቃል።
  • x. ማታለል እና ሶፍትዌሩን ማመሳቀል። ለማንኛውም ከXbox አገልግልሎቶች ጋር የተገናኘ አገልግሎት፣ የስነምግባር ደንቡን ወይም እነዚህን ውሎች በሚጥስ መልኩ ለማታለል ወይም ሶፍትዌርን ለማመሳቀል የሚያገለግል ያልተፈቀደ ሃርድዌር ወይም ሶፍትዌር መኖሩን ለማረጋገጥ መሳሪያዎትን ወዲያው እንፈትሻለን። ከዚያም የXbox መተግበሪያ ሶፍትዌር ዝማኔዎችን ወይም የአወቃቀር ለውጦችን፣ የXbox አገልግሎቶችን እንዳያገኙ ወይም ያልተፈቀዱና ለማታለል እና ለማመሳቀል የሚያስችሉ ሶፍትዌርን የሚከለክሉትን ጨምሮ እናወርዳለን።
  • xi. Mixer።
   • 1. Mixer መለያዎች እና Microsoft መለያዎች። Mixer አገልግሎት በMixer መለያ የሚጠቀሙ ከሆነ፣ አጠቃቀምዎ በMixer የአገግሎት ውሎች የሚሸፈን ሲሆን ይህም በhttps://mixer.com/about/tosላይ ይገኛል። Mixer አገልግሎት በMicrosoft መለያ የሚጠቀሙ ከሆነ፣ አጠቃቀምዎ በእነዚህ ውሎች የሚሸፈን ይሆናል። እነዚህ ውሎች ግጭት በሚኖርበት ቦታ ተፈጻሚ ይሆናሉ።
   • 2. በMixer ላይ ያለ ይዘትዎ። "በMixer ላይ ያለ ይዘትዎ።" ማለት እርስዎ ወይም ሌላ ሰው ስለ እርስዎ በMixer አገልግሎት ላይ የሚፈጥረው ይዘት ሁሉ ማለት ነው። ይኽም የሚከተሉትን የሚያካትት ሲሆን በእነሱ የተገደበ አይደለም፦ የቀጥታ ወይም የተቀረጹ ስርጭቶች፣ (እና ማንኛውም ይዘት ለምሳሌ ሊይዟቸው የሚችሏቸው የኦዲዮቪዥዋል ይዘት )፣ የምርት ስሞች፣ የንግድ ምልክቶች፣ የአገልግሎት ምልክቶች፣ የንግድ ስሞች፣ አርማዎች፣ የፖስታ ማህተሞች፣ አስተያየትዎ፣ ስሜት ገላጭ ምስሎች፣ እና በMixer ጣቢያዎች ላይ የተፈጸሙ እንቅስቃሴዎች ( ከቦት የመነጩ ይዘቶችን ጨምሮ)፤ እና ሁሉም ተያያዥ ዲበ ውሂብ። ማንኛውም ሰው፣ Microsoftን እና ተጥቃሚዎችን ጨምሮ፣ በMixer ላይ ያለ ይዘትዎን አሁን በሚታወቅ ወይም ወደፊት በሚለማ በማንኛውም ቅርጽ፣ ቅርጸት፣ ሚዲያ፣ ወይም ጣቢያ ማየት፣ መጠቀም፣ ማስተናገድ፣ ዳግም መስራት፣ ማሻሻል፣ ማሰራጨት፣ ማተም፣ በይፋ ወይም ዲጂታዊ በሆነ መልክ መተግበር እና ማሳየት፣ መተርጎም፣ እንደሚመች ማበጀት እና በሌላ መንገድ ጥቅም ላይ ማዋል ይችላል።
   • 3. በMixer ላይ ተፈጻሚ የሆኑ የስነምግባር ደንቦች። የMicrosoft’s የስነምግባር ደንቦች በMixer ላይ ስላላቸው ተፈጻሚነት የበለጠ ለመረዳት።እዚህጠቅ ያድርጉ።
   • 4. የMixer አገልግሎትን መጠቀም።
    • a. ዝቅተኛው ዕድሜ. የMixer አገልግሎትን በመጠቀም፣ ቢያንስ 13 ዓመት ዕድሜ ያለዎ መሆኑን ያረጋግጣሉ፣ እንዲሁም በሚኖሩበት አካባቢ ከሕጻንነት የዕድሜ ጣሪያ በታች ከሆኑ፣ አጠቃቀምዎ በአዋቂ ሰው ቁጥጥር የሚፈጸም እንደሆነ ያረጋግጣሉ።
    • b. በመታወቅ እና ባለመታወቅ መጥቀም። ይዘትን መመልከት ብቻ የሚፈልጉ ከሆነ Mixerን ባለመታወቅ መጠቅም ይችላሉ። ያ ካልሆነ፣ መለያ መፍጠር፣ በመለያዎ መግባት፣ እና ለሌሎች ተጠቃሚዎች በMixer ስምዎ መታወቅ አለብዎ።
    • c. መለያዎች በመታወቅ ለመጠቀም የMixer አገልግሎት በመታወቅ ለመጠቀም የMicrosoft መለያ እና/ወይም የMixer መለያ መፍጠር ይችላሉ። የMixer መለያን በመስመር ላይ በመመዝገብ መፍጠር ይችላሉ። ንቁ እንደሆነ እንዲቆይ የMixer መለያዎን መጠቀም አለብዎ። ከእርስዎ የMicrosoft መለያ ጋር የተያያዘውን የMixer ተለዋጭ ስም የእርስዎ አድርገው ለማቆየት ወደ Mixer አገልግሎት በአምስት ዓመት ቢያንስ አንድ ጊዜ መግባት አለብዎ።
   • 5. የአገልግሎት ማሳወቂያዎች። ስለ Mixer አገልግሎት ልንነግርዎ የምንፈልገው ነገር በሚኖር ጊዜ፣ ከMixer/Microsoft መለያ ጋር በተያያዘው ኢሜይል የአገልግሎት ማሳወቂያዎችን እንልክልዎታለን።
   • 6. ድጋፍ። ለMixer አገልግሎት የሚሰጥ አገልግሎት በ mixer.com/contactላይ ይገኛል።
ሙሉ ጽሁፍ
ማከማቻማከማቻ14b_Store
ማጠቃለያ
 • ለ. ማከማቻ። "ማከማቻ" ማለት መተግበሪያዎችን ("መተግበሪያ" የሚለው ቃል ጨዋታዎችን ይጨምራል) እና ሌላ ዲጂታል ይዘትን እንዲያስሱ፣ እንዲያወርዱ፣ እንዲገዙ እንዲሁማ ደረጃ እንዲሰጡና እንዲገመግሙ የሚያስችል አገልግሎት ማለት ነው። እነዚህ ደንቦች የ Office ማከማቻ፣ Windows ማከማቻና Xbox ማከማቻ አጠቃቀምን ይሸፍናሉ። "Office መደብር" ማለት የOffice ምርቶች እና ለOffice፣ Office 365፣ SharePoint፣ Exchange፣ Access እና Project (2013 ስሪቶች እና ከዚያ በላይ)፣ ወይም ማንኛውም ሌላ Office Store ተብሎ የተሰየመ ተሞክሮ መደብር ነው። "Windows ማከማቻ" ማለት እንደ ስልክ፣ ፒሲ እና ታብሌት ለመሳሰሉ የ Windows መሳሪያዎች ማከማቻ ወይም ለማንኛውም Windows ማከማቻ የሚል ምልክት የተደረገበት ተሞክሮ ማለት ነው። "Xbox መደብር" ማለት የ Xbox One እና Xbox 360 ኮንሶሎች ወይም Xbox Store ተብሎ የተሰየመ ማንኛውም ተሞክሮ መደብር ነው።
  • i. የፈቃድ ደንቦች። በተገቢው ማከማቻ ውስጥ የሚገኘውን የእያንዳንዱን መተግበሪያ አታሚ ለይተን እናውቃለን። ከመተግበሪያው ጋር ሌሎች የፈቃድ ውሎች ካልቀረቡ በስተቀር፣ ("SALT") ከእነዚህ ውሎች በስተመጨረሻ የቀረቡት መደበኛዎቹ የመተግበሪያ ፈቃድ ውሎች በእርስዎ እና በመተግበሪያው አታሚ መካከል የተደረጉ በWindows መደብር ውእይም Xbox መደብር በኩል የወረዱ መተግበሪያዎች ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ ውሎች ናቸው። ግልጽ ለማድረግ፣ እነዚህ ውሎች በMicrosoft አገልግሎቶች የሚቀርቡ አገልግሎቶችን እና አጠቃቀማቸውን ይሸፍናሉ። የእነዚህ ውሎች ክፍል 5 በማንኛውም በመደብር በኩል የተገኘ የሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎች እና አገልግሎቶች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል። በ Office ማከማቻ በኩል የወረዱ መተግበሪያዎች በ SALT የሚገዙ ሲሆን ተፈጻሚ የሚሆኑ የተለዩ ፈቃዶች አሉት።
  • ii. ማዘመኛዎች። Microsoft ወደተገቢው ማከማቻ በመለያ ባይገቡም እንኳን በራስ ሰር ይፈትሹና ወደ መተግበሪያዎ ማዘመኛዎችን ያወርዳሉ። ወደ ማከማቻ መተግበሪያዎች ማዘመኛዎች እንዳይላኩ የሚፈልጉ ከሆነ የማከማቻ ወይም የስርዓት ቅንብሮችዎን መለወጥ ይችላሉ። ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በመስመር ላይ የሚስተናገዱ የተወሰኑ የOffice Store መተግበሪያዎች በማንኛውም ጊዜ በመተግበሪያው አዘጋጅ ሊዘመኑ የሚችሉ ሲሆን ለመዘመን የእርስዎን ፈቃድ አይጠይቁም።
  • iii. ደረጃዎችና ግምገማዎች። ለአንድ በመደብር ውስጥ ያለ መተግበሪያ ወይም አኃዛዊ ሸቀጥ ደረጃ ወይም አስተያየት ከሰጡ፣ ከመተግበሪያው ወይም አኃዛዊ ሸቀጡ አታሚ የመነጨ ይዘት ያለው ኢሜይል ሊቀበሉ ይችላሉ። እንዲህ አይነቱ ማንኛውም ኢሜይል የሚመጣው ከMicrosoft ነው፣ የኢሜይል አድራሻዎን በመደብሩ በኩል ለሚገዟቸው መተግበሪያዎች ወይም ሌላ አኃዛዊ ቁስ አታሚዎች አናጋራም።
  • iv. የደህንነት ማስጠንቀቂያ። ሊከሰት የሚችል ጉዳትን፣ ምቾት መጓደልን ወይም የአይን ህመምን ለማስቀረት በተለይ ደግሞ ከመጠቀም የተነሳ ማንኛውንም አይነት ህመም ወይም ድካም ከተሰማዎ ጨዋታዎችን ወይም ሌሎች መተግበሪያዎችን ከመጠቀም በየጊዜው እረፍት መውሰድ አለብዎ ። የምቾት መጓደል ከተሰማዎ እረፍት ይውሰዱ። የምቾት መጓደል የሆድ መገላበጥን፣ ከጉዞ ጋር ተዛማጅ የሆድ ህመም፣ መደንዘዝ፣ ማዞር፣ ራስ ምታ፣ ድካም፣ የአይን ህመም ወይም የአይን መድረቅን ያካትታል። መተግሪያዎችን መጠቀም እርስዎንና አካባቢዎን ሊያውክ ይችላል። የመንገድ አደጋ ማስጠንቀቂያዎችን፣ ደረጃዎችን፣ ዝቅ ያሉ ጣሪያዎችን፣ ተሰባሪ ወይም ሊጎዱ የሚችሉ ዋጋ ያላቸውን እቃዎች ይጠንቀቁ። በጣም ጥቂት የሚባሉ ሰዎች እንደ አንጸባራቂ ብርኖችና በመተግበሪያዎች ውስጥ የሚታዩ መስመሮችን የመሳሰሉ ነገሮችን በሚያዩበት ጊዜ በድንገት ሊታመሙ ይችላሉ። ከአሁን በፊት የህመም ታሪክ የሌላቸው ሰዎች እንኳን ይህንን ድንገተኛ ህመም ሊያስከትል የሚችል ያልታወቀ ህመም ሊኖርባቸው ይችላል። ምልክቶቹ የጭንቅላት ቅለት፣ የተዘበራረቀ እይታ፣ ድንገተኛ የጡንቻ መኮማተር፣ የመገጣጠሚያዎች መንቀጥቀጥ፣ ብዥ ማት፣ መምታታት፣ ህሊናን መሳት ወይም የጡንታ መሸምቀቅን ሊያካትቱ ይችላሉ። ከእነዚህ ምልክቶች ውስጥ አንዱም ከተከሰተብዎ መጠቀምዎን ያቁሙና ሃኪም ያማክሩ ወይም ከድንገተኛ ህመም ጋር የተገናኙ ምልክቶች አጋጥመዎት የሚያውቁ ከሆነ መተግበሪያዎቹን ከመጠቀምዎ በፊት ሃኪም ያማክሩ። ወላጆች የልጆቻቸውን የመተግበሪያዎች አጠቃቀምና የህመሙን ምልክቶች መቆጣጠር አለባቸው።
ሙሉ ጽሁፍ
Microsoft የቤተሰብ ባህሪዎችMicrosoft የቤተሰብ ባህሪዎች14c_MicrosoftFamily
ማጠቃለያ
 • ሐ. Microsoft የቤተሰብ ባህሪያት። በቤተሰብ ውስጥ፡እንዴት አይነት ባሕሪዎች፣ የድር ጣቢያዎች፣ መተግበሪያዎች፣ ጨዋታዎች፣ ነባራዊ አካባቢዎች እና ገንዘብ አወጣጥ አግባብነት ያለው እንደሆነ በጋራ መግባባት ላይ መተማመንን ለመፍጠር ወላጆች እና ልጆች የMicrosoft ቤተሰብ ባህሪዎችን መጠቀም ይችላሉ። ወላጆች ወደ https://account.microsoft.com/family በመሄድ (ወይም በWindows መሳሪያቸው ወይም Xbox ኮንሶል ላይ ያሉትን ትዕዛዞች በመከተል) እንዲሁም ልጆችን ወይም ሌሎች ወላጆችን ንዲቀላቀሏቸው በመጋበዝ ቤተሰብ መፍጠር ይችላሉ። ለቤተሰብ አባላት የቀረቡ ብዙ ባህሪዎች አል፣ ስለዚህ እባክዎ ቤተሰብ በሚፈጥሩ ወይም ለመቀላቀል በሚስማሙ ጊዜ እንዲሁም ለቤተሰብ መዳረሻ ያላቸው አኃዛዊ ሸቀጣሸቀጦችን በሚገዙ ጊዜ የቀረበውን መረጃ በጥንቃቄ ያጢኑ። ቤተሰብ በመፍጠር ወይም በመቀላቀል፣ ቤተሰብን ለተዘጋጀበት ዓላማ እንደሚጠቀሙ እንጂ ባልተፈቀደ መንገድ የሌላ ሰው መረጃ ዘንድ ለመድረስ እንደማይጠቀሙ ይስማማሉ።
ሙሉ ጽሁፍ
የቡድን መልዕክትየቡድን መልዕክት14d_GroupMessaging
ማጠቃለያ
 • መ. የቡድን መልዕክት። በርካታ የ Microsoft አገልግሎቶች ለሌሎች በድምጽ ወይም ኤስኤምኤስ ("መልዕክቶች") እንዲልኩ እና/ወይም Microsoft እና በ Microsoft ቁጥጥር ስር ያሉ አጋሮች እነዚህን መልዕክቶች ለእርስዎና እርስዎን በመወከል ለአንድ ወይም ለብዙ ተጠቃሚዎች እንዲልኩ ይፈቅዳሉ። MICROSOFT እና በ MICROSOFT ቁጥጥር ስር ያሉ አጋሮች እነዚህን መልዕክቶች ለእርስዎ ወይም ለሌሎች እንዲልኩ ሲያዙን እርስዎ እና መልዕክት እንድንልክለት ያዘዙን እያንዳንዱ ሰው እነዚህን መልዕክቶች እና ሌሎች ተዛማጅ አስተዳደራዊ መልዕክቶችን ከMICROSOFT እና በ MICROSOFT ቁጥጥር ስር ያሉ አጋሮች ለመቀበል ፈቃደኛ እንደሆነ ያረጋግጣሉ። "አስተዳደራዊ የጽሁፍ መልዕክቶች" ማለት "የእንኳን ደህና መጡ መልዕክትን" ወይም መልዕክቶችን እንዴት መቀበል ማቆም እንደሚቻል የሚያሳዩ መመሪያዎችን እና ሌሎችንም ጨምሮ ከአንድ የተወሰነ የMicrosoft አገልግሎት በየተወሰነ ጊዜው የሚላኩ መልዕክቶቸች ናቸው። እርስዎ ወይም ሌላ ከአሁን በኋላ መልዕክቶችን መቀበል የማይፈልጉ የቡድን አባላት በማንኛውም ጊዜ ከዚህ በታች የተሰጠውን መመሪያ በመከተል ከMicrosoft እና በ Microsoft ቁጥጥር ስር ያሉ አጋሮች ተጨማሪ መልዕክቶችን እንዳይላኩ መርጠው መውጣት ይችላሉ። እነዚህን መልዕክቶች መቀበል ወይም በቡድኑ ውስጥ መሳተፍ የማይፈልጉ ከሆነ ተገቢ በሆነው ፕሮግራም ወይም አገልግሎት በተሰጠው መመሪያ መሰረት መርጠው እነደሚወጡ ይስማማሉ። አንድ የቡድን አባል እነዚህን መልዕክቶች መቀበል ወይም በቡድኑ ውስጥ መሳተፍ እንደማይፈልግ ካወቁ ወይም የሚያሳምን ምክንያት ካለዎት ከቡድኑ ለማስወጣት ይስማማሉ። በተጨማሪም እርስዎ እና መልዕክት እንድንልክለት ያዘዙን ማንኛውም ሰው እያንዳንዱ የቡድን አባል በሞባይል አገልግሎት አቅራቢዎ የሚከፈለውን ማንኛውም የመልዕክት መላኪያ ወጪ፣ መልዕክቶች በዩናይትድ ስቴትስ ካሉ ቁጥሮች ሲላኩ የሚኖሩ ማናቸውንም አለም አቀፍ የመልዕክት መላኪያ ክፍያዎች ጨምሮ መክፈል ሃላፊነታችሁ እንደሆነ እንደሚረዳና እንደሚስማማ ያረጋግጡልናል።
ሙሉ ጽሁፍ
Skype እና GroupMeSkype እና GroupMe14e_Skype
ማጠቃለያ
 • ሠ. Skype እና GroupMe።
  • i. ምንም የድንገተኛ ጥሪ አገልግሎቶች አይገኙም። በመደበኛ የስልክ አገልግሎቶችና Skype መካከል ምንም ልዩነቶች የሉም። በማናቸውም ተፈጻሚነት ያላቸው አካባቢያዊ እና ብሔራዊ ሕጎች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች ወደ አስቸኳይ አገልግሎቶች መዳረሻ ለመስጠት Skype የግድ አያስፈልግም። የ Skype ሶፍትዌርና ምርቶች ወደ ማናቸውም ሆስፒታሎች፣ የህግ አፈጻጸም ኤጀንሲዎች፣ የህክምና እንክብካቤ ክፍሎች ወይም ሌሎች ማናቸውም ሌላ አይነት ወደ የድንገተኛ አገልገሎት ሰጪ ሰራተኞች ወይም የህዝባዊ ደህንነት መመለሻ ነጥቦች ("ድንገተኛ አገልግሎቶች") አገልገሎት ለመስጠት ታቅደው የተሰሩ ወይም ድጋፍ የሚሰጡ አይደሉም። ለሚከተሉት ዕውቅና ይሰጣሉ እንዲሁም ይስማማሉ፦ (I) ወደ የአደጋ ጊዜ አገልግሎቶች መዳረሻ የሚሰጡ መደበኛ ሽቦ አልባ (mobile) ወይም ተቀማጭ የስልክ መስመር የመግዛት ኃላፊነት የእርስዎ ነው እንዲሁም (ii) Skype ለመደበኛው የስልክ አገልግሎትዎን አይተካም።
  • ii. APIs ወይም ማሰራጨት። Skype ከማንኛውም ማሰራጫ አገልግሎት ጋር በተገናኘ መልኩ ለመጠቀም ከፈለጉ በ https://www.skype.com/go/legal.broadcast ከሚገኘው የ "ስርጭት የአገልግሎት ውሎች"ን ማክበር አለብዎ። ማንኛውንም በ Skype የቀረበ ወይም የተሰጠ መተግበሪያ ፕሮግራም ገጽታ ("API") መጠቀም የሚፈልጉ ከሆነ በ www.skype.com/go/legal የሚገኙትን ተፈጻሚ የሆኑትን የፈቃድ አሰጣጥ ውሎች ማክበር አለብዎ።
  • iii. የፍትሃዊ አጠቃቀም ፖሊሲዎች። የፍትሃዊ አጠቃቀም ፖሊሶወች የ Skype አጠቃቀምዎ ላይ ተፈጻሚ ሊሆኑ ይችላሉ። እባክዎ እነዚህን ማታለልንና አለአግባብ መጠቀምን ለመከላከል የተዘጋጁ መመሪያዎች ይገምግሙና ማድረግ የሚፈልጓቸው ጥሪዎች ወይም መልእክቶች አይነት፣ርዝመትና መጠን ላይ ገደብ ማድረግ ይችላሉ። እነዚህ ፖሊሲዎች በማጣቀሻ በውሎቹ ውስጥ ተካተዋል። ፖሊሲዎቹን በ https://www.skype.com/go/terms.fairusage/ ማግኘት ይችላሉ።
  • iv. ካርታ አዘገጃጀት። Skype በካርታ አዘገጃጀት አገልግሎትን በመጠቀም ወደ ካርታ ላይ መረጃ እንዲያስገቡ ወይም ራስዎ ካርታ እንዲሰሩ የሚፈቅዱ ባህሪያትን የያዘ ነው። እነዚህን ባህሪያት በመጠቀም በእነዚህ ውሎችና በ https://www.google.com/intl/en_ALL/help/terms_maps.html በሚገኙት የGoogle ካርታዎች ውሎች ወይም በእርስዎ አገር በሚገኙት የ Google ካርታዎች ተስማምተዋል።
  • v. ተጠቃሚ መንግስታት። የአሜሪካ መንግስትን ወይም ኤጀንሲን ወክለው Skype Manager መጠቀም ከፈለጉ እነዚህ ውሎች ለዚያ አጠቃቀም ተፈጻሚ አይሆኑም። ተፈጻሚነት ላላቸው ውሎች ወይም ለተጨማሪ መረጃ፣ እባክዎ usgovusers@skype.netን ያነጋግሩ።
  • vi. የግል/ለንግድ ያልሆነ አገልግሎት። የ Skype አገልግሎት ለግልዎና ለንግድ ላልሆነ አገልግሎት ብቻ ነው። Skypeን በስራ ቦታ ለራስዎ የስራ ግንኙነቶች መጠቀም ይችላሉ።
  • vii. Skype ቁጥር/Skype To Go. Skype ለእርስዎ የ Skype ቁጥር ወይም Skype To Go ቁጥር ከሰጥዎት የቁጥሩ ባለቤት እንደማይኑና ቁጥሩን ለዘላለም ይዞ የማቆየት መብት እንደሌለዎት ይስማማሉ። በተወሰኑ አገሮች ቁጥሩ የሚሰጠው ከ Skype ይልቅ በ Skype አጋር ሊሆን የሚችል ሲሆን ከዚህ አጋር ጋር ሌላ ውል መግባት ሊያስፈልግዎ ይችላል።
  • viii. የ Skype አስተዳዳሪ። "Skype Manager አስተዳዳሪ መለያ" በእርስዎ የሚፈጠር እና የሚተዳደር ነው፣ ይኽንም የሚያደርጉት የSkype Manager ቡድን አስተዳዳሪ ሆነው እንጂ እንደ ንግድ ተቋም ሆነው አይደለም። የእርስዎን የግል የMicrosoft መለያ ከSkype Manager ቡድን ጋር ማገናኘት ይችላሉ።("የተገናኘ መለያ")። ለእነዚህ ውሎች ተገዥ በሆነ መልክ፣ ለSkype Manager ቡድንዎ ተጨማሪ አስተዳዳሪዎችን ሊሾሙ ይችላሉ። ለተገናኘ መለያ የ Skype ቁጥር ከመደቡ ከተገናኘ መለያ ተጠቃሚዎችዎ መኖሪያ ወይም አካባቢ ጋር ተዛማጅ ለሆኑ ማናቸውም መስፈርቶች ሃላፊነቱ የእርስዎ ነው። የተገናኘ መለያን ከSkype Manager ቡድን፣ ማለያየት ከፈለጉ ማለያየት ከፈለጉ ማንኛውም ምዝገባዎች፣ Skype Credit ወይም Skype ቁጥሮች ዳግም መገኘት አይችሉም እንዲሁም የተለያየውን መለያ ከእንግዲህ ወዲያ ሊያግኙት አይችሉም። ሁሉንም የተገናኙ መለያዎች ተጠቃሚዎች በተመለከተ ተፈጻሚነት ባላቸው የውሂብ ጥበቃ ሕጎች መሰረት ለመጠቀም ተስማምተዋል።
  • ix. የ Skype ክፍያዎች። ተቃራኒው ካልተደነገገ በስተቀር በ Skype ለሚከፈልባቸው ምርቶች ሁሉም ዋጋዎች ተፈጻሚ የሚሆኑትን ግብሮች ያጠቃልላሉ። ከደንበኝነት ምዝገባ ውጪ ያሉ ቁጥሮች ላይ የሚከፈሉ ማናቸውም ክፍያዎች የግንኙነት ክፍያን (በአንድ ጥሪ አንድ ጊዜ የሚከፈል) እና በ www.skype.com/go/allrates ላይ በተጠቀሰው መሰረት የአንድ ደቂቃ ተመንን ያካትታሉ። የጥሪ ክፍያዎች ከ Skype ክሬዲት ቀሪ ሂሳብዎ ላይ ይቀነሳሉ። Skype የጥሪ ተመኖቹን በ www.skype.com/go/allrates ላይ በመለጠፍ በማንኛውም ጊዜ ሊለውጥ ይችላል። አዲሱ ተመን አዲሶቹ ተመኖች ከታሙ በኋላ በሚያደርጉት ቀጣዩ ጥሪ ላይ ተፈጻሚ ይሆናል። እባክዎ ጥሪ ከማድረግዎ በፊት የቅርብ ጊዜዎቹን ተመኖች ይመልከቱ። የክፍልፋይ ደቂቃ ጥሪዎችና ክፍልፋይ ሂሳቦች ወደ ቀጣዩ ሙሉ አሃድ ይጠጋገሉ። በአንዳንድ አገሮች በ Skype የሚከፈልባቸው ምርቶች በ Skype አካባቢያዊ አጋር የሚቀርቡ ሲሆን የአጋሩ የአገልግሎት ውሎች ተፈጻሚ ይሆናሉ።
  • x. Skype ክሬዲት። Skype ሁሉንም የእርስዎን የ Skype የሚከፈልባቸው ምርቶች ለመግዛት የ Skype ክሬዲት ቀሪ ሂሳብዎን መጠቀም እንደሚችሉ ዋስትና አይሰጥም። ካልሆነ በስተቀር የ Skype ክሬዲትዎን ለ 180-ቀናት ያልተጠቀሙበት ከሆነ Skype የ Skype ክሬዲትዎን ንቁ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ ያቆየዋል። በ https://www.skype.com/go/store.reactivate.credit የተሰጠውን የዳግም ማንቂያ አገናኝ በመጠቀም የ Skype ክሬዲቱን ዳግም ማንቃት ይችላሉ። ጃፓን ውስጥ የሚኖሩ ከሆነና Skype Creditን ከSkype ድር ጣቢያ የሚግዙ ከሆነ ከዚህ በላይ ያሉት ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ለእርስዎ Skype Credit ተፈጻሚ የማይሆኑ ሲሆን፣ የእርስዎ Skype Credit ከተገዛበት ከ180 ቀናት በኋላ የአገልግሎት ጊዜው ያበቃል። አንድ ጊዜ ክሬዲትዎ ጊዜው ካበቃ በኋላ፣ ዳግም ሊያነቁት እና ሊጠቀሙበት አይችሉም። የ Skype ክሬዲት ሲገዙ ተገቢው ሳጥን ላይ ምልክት በማድረግ የራስ ሰር ዳግም መሙያውን ማንቃት ይችላሉ። ከነቃ፣ የእርስዎ Skype Credit ሂሳብ፣ በSkype ከጊዜ ወደ ጊዜ ከሚወሰነው ዝቅተኛ የሂሳብ መጠን በታች ሲወርድ በተመሳሳይ የገንዘብ መጠንና በመረጡት የክፍያ ዘዴ ይሞላል። ከክሬዲት ካርድ፣ PayPal ወይም Moneybookers (Skrill) በተለየ የክፍያ መንገድ የደንበኝነት ምዝገባ ከገዙና በራስ ሰር ሂሳብ መሙያን ካነቁ የ Skype ክሬዲት ቀሪ ሂሳብዎ ቀጣዩን ተደጋግሞ የሚመጣ የደንበኝነት ምዝገባዎን ለመግዛት በሚበቃዎት መጠን ዳግም ይሞላል። በማንኛውም ጊዜ በSkype ውስጥ የመለያ ኆህትዎ ዘንድ በመድረስና ቅንብሮችን በመለወጥ በራስ-መሙላትን ማሰናከል ይችላሉ።
  • xi. የአለም አቀፍ መልዕክት ክፍያዎች GroupMe በአሁኑ ወቅት ለእያንዳንዱ የሚፈጠር ቡድን በዩናይትድ ስቴትስ ያሉ ቁጥሮችን ይጠቀማል። ከ ወይም ወደ GroupMe ቁጥር የተላከ ማንኛውም ቁጥር ከ ወይም ወደ ዩናይትድ ስቴትስ አንደተላከ አለም አቀፍ የጽሁፍ መልዕክት ይቆጠራል። እባክዎ ለተዛማጅ አለም አቀፍ ክፍያዎች አቅራቢዎ ጋር ይፈትሹ።
  • xii. ገንዘብ መላክ እና መቀበል። (የሚገኝ ከሆነ) የገንዘብ ላክ እና ተቀበል ባህሪን በመጠቀም፣ ክፍያን ለማከናወን ወይም ገንዘብ ለማስተላለፍ Skype ሶስተኛ-ወገን የክፍያ አገልግሎት አቅራቢዎችን አገልግሎት እንደሚጠቀም እውቅና ይሰጣሉ። Skype የክፍያ አገልግሎቶችን አይሰጥም ወይም ገንዘብ አያስተላልፍም፣ እንዲሁም የገንዘብ አገልግሎቶች ሥራ ላይ የትሰማራ አይደለም። በSkype ገንዘብ መላክ እና መቀበል የሚፈቀደው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ (ወይም አልያም በሶስተኛ- ወገን አቅራቢዎቹ ደንብ መሰረት) እና በሶስተኛ ወገን አቅራቢው የተመዘገቡ እና የተፈቀደላቸው ተጠቃሚዎች ነው። የገንዘብ መላክ ባህሪን ለመጠቀም፣ ለሶስተኛው ወገን አቅራቢ ውሎች እና ሁኔታዎ መመዝገብ እንዲሁም ይህንኑ አገልግሎት ለማቅረብ ሲባል ከእነዚህ ሶስተኛ-ወገኖች ጋር ውሂብ ለማጋራት ፈቃድ መስጠት ሊጠበቅብዎ ይችላል። Skype የገንዘብ መላክ ባህሪን አጠቃቀምዎ የሶስተኛ ወገን ውሎች እና ሁኔታዎችን እንደማያከብር ለSkype ማሳወቂያ ከደረሰው፣ Skype በመለያዎ ላይ እርምጃ መውሰድ ሊኖርበት ይችላል፣ ለምሳሌ መለያዎን መሰረዝ ወይም ለጊዜው ማገድ። Skype ወይም Microsoft ፣ በሶስተኛ-ወገን ለሚቀርቡ የክፍያ አገልግሎቶች ወይም በሶሰተና ወገን ውሎች እና ሁኔታዎች መሰረት ለሚወሰዱ ማናቸውም እርምጃዎች ተጠያቂ አይሆንም። የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎቱ የሚገኝ ወይም የሚቀጥል ስለመሆኑ Skype ምንም አይነት ማረጋገጫ፣ ውክልና ወይም ዋስትና አይሰጥም።
ሙሉ ጽሁፍ
Bing እና MSNBing እና MSN14f_BingandMSN
ማጠቃለያ
 • ረ. Bing እና MSN።
  • i. Bing እና MSN ማቴሪያሎች። በBing እና MSN ላይ የሚገኙ መጣጥፎች፣ ጽሁፎች፣ ካርታዎች፣ ቪዲዮዎች፣ የቪዲዮ ማጫወቻዎች እና የሶስተኛ ወገን መረጃዎች፣ በMicrosoft ቦቶች በኩል የሚቀርቡትን ጨምሮ፣ መተግበሪያዎች እና ፕሮግራሞች፣ ለእርስዎ ለንግድ ያልሆነ እና ለግላዊ አጠቃቀም ብቻ የተፈቀዱ ናቸው። ሌሎች አጠቃቀሞች፣ እነዚህን ይዘቶችን ማውረድ፣ መቅዳት ወይም ማሰራጨትን ጨምሮ ወይም እነዚህን ይዘቶች የራስዎን ምርቶች ለመገንባት መጠቀም የሚፈቀደው በተለይ በMicrosoft ባለመብቶች በተፈቀደው ልክ ወይም ተፈጻሚነት ባለው የቅጅ መብት ሕግ መሰረት ነው። በ Microsoft በተዘዋዋሪ በማመልከት፣ ወይም በሌላ መንገድ ይሁን በፈቃድ ውሎቹ በግልጽ ባልተሰጡ ነገሮች ላይ ያለው መብት በ Microsoft ወይም በሌሎች ፈቃድ ሰጪዎች የተጠበቀ ይሆናል።
  • ii. Bing ካርታዎች። የዩናይትድ ስቴትስን፣ የካናዳን፣ የሜክሲኮን፣ የኒው ዚላንድን፣ የአውስትራሊያን ወይም የጃፓንን ከላይ ወደታች የወፍ አይን እይታ ለመንግስት አገልግሎት ያለ እኛ የተለየ የጽሁፍ ፈቃድ መመልከት ይችላሉ።
  • iii. Bing አካባቢዎች እና Bing የአምራች ማዕከል ውሂብዎን ወይም ይዘትዎን ለBing አካባቢዎች እና ለBing የአምራች ማዕከል በሚያቀርቡ ጊዜ፣ ለMicrosoft የመጠቀም፣ ዳግም የመፍጠር፣ የማስቀመጥ፣ የማሻሻል፣ የማዋሃድ፣ የማስተዋወቅ፣ የማስተላለፍ፣ የማሳየት ወይም እንደ አገልግሎት አካል የማሰራጨት፣ እንዲሁም ለሶስተኛ ወገኑች ንዑስ ፈቃድ የመስጠት፣ ከመብት ክፍያ ነጻ የሆነ የአዕምሮ ንብረትነት ፈቃድ ይሰጣሉ።
ሙሉ ጽሁፍ
CortanaCortana14g_Cortana
ማጠቃለያ
 • ሰ. Cortana።
  • i. የግል ንግድ ያልሆነ አገልግሎት። Cortana የ Microsoft የግል አጋዥ አገልግሎት ነው። በCortana የሚቀርቡ ባህሪዎች፣ አገልግሎቶች፣ ይዘት እና የሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎች (በአንድ ላይ "Cortana አገልግሎቶች") ለእርስዎ ለንግድ ላልሆነ ግላዊ መጠቀሚያ የተፈቀዱ ናቸው።
  • ii. ተግባራት እና ይዘት። Cortana በርካታ ባህሪዎችን ያቀርባል፣ አንዳንዶቹ ለግል የተበጁ ናቸው። Cortana አገልግሎቶች በሌሎች የMicrosoft አገልግሎቶች ወይም የሶስተኛ ወገን አገልግሎቶች እና መተግበሪያዎች የሚቀርቡ አገልግሎቶችን፣ መረጃ ወይም ተግባር እንዲያገኙ ሊያስችልዎት ይችላል። ለአገልግሎት የተወሰኑ የክፍል 13 ውሎች በተጨማሪም በCortana አማካኝነት ለሚጠቀሙባቸው የMicrosoft አገልግሎቶች ላይም ተፈጻሚ ይሆናሉ። Cortana መረጃ የሚያቀርበው ለእርስዎ የእቅድ አገልግሎት እንዲውል ብቻ ሲሆን ይህንን መረጃ ሲገመግሙም ይሁን እሱ ላይ ሲተማመኑ የራስዎን ግምት መውሰድ አለብዎ። Microsoft በCortana አማካኝነት ለሚቀርቡ ግላዊነትን ለተላበሱ አገልግሎቶች የአስተማማኝነት፣ የተገኝነት፣ ወይም ጊዜያቸውን የጠበቁ ስለመሆናቸው ዋስትና አይሰጥም። የCortana የግንኙነት አስተዳደር ባህሪ ቢዘገይ ወይም አንድን መልዕክት ወይም ማሳወቂያ እንዳያገኙ፣ እንዳይገመግሙ ወይም እንዳይልኩ ቢከለክልዎ Mirosoft ኃላፊነት አይኖርበትም።
  • iii. ሶስተኛ-ወገን መተግበሪያዎች እና አገልግሎቶች። Cortana አገልግሎቶችን የማቅረብ አንዱ አካል፣ Cortana ጥያቄዎን ለማሟላት እንደ ዚፕ ኮድ እና በሶስተኛው ወገን የሚመለሱ መጠይቆች እና ምላሾች ያሉ የሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎ ወይም አገልግሎቶች ጋር መረጃ ሊሊዋወጥ ይችላል። መለያዎችን በማገናኘት፣ Cortana ተጠቃሚዎች በሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎች እና አገልግሎቶች አማካኝነት ከእነዚያ ሶስተኛ-ወገኖች ጋር ተጠቃሚው በወሰናቸው ምርጫዎች እና ዝግጅቶች መሰረት ግዥ እንዲፈጽሙ ሊያስችል ይችላል። ተጠቃሚዎች መለያ ማገናኘትን በማንኛውም ጊዜ ማቋረጥ ይችላሉ። የእርስዎ የሶስተኛ-ወገን መተግበሪያዎች እና አገልግሎቶች በእነዚህ ውሎች ክፍል 5 ይሸፈናል። የሦስተኛ ወገን መተግበሪያዎች እና አገልግሎቶች አታሚዎች የእነርሱን የሦስተኛ ወገን የመተግበሪያዎችና አገልግሎቶች ተግባር ወይም ባህሪ ወይም ከCortana አገልግሎቶች ጋር ያላቸውን ጥምረት ሊቀይሩ ወይም ሊያቋርጡ ይችላሉ። Microsoft በአምራች ለቀረበ ሶፍትዌር ወይም ፈርምዌር ኃላፊነት አይወስድም።
  • iv. Cortana-ተጠቃሚ መሳሪያዎች። ለCortana-የነቁ መሳሪያዎች ለCortana አገልግሎቶች መዳረሻ ያላቸው ምርቶች ወይም መሳሪያዎች፣ ወይም ከCortana አገልግሎቶች ጋር ተኳኋኝ የሆኑ ምርቶች ወይም መሳሪያዎች ናቸው። Cortana-ተጠቃሚ መሳሪያዎች በMicrosoft ይዞታ ስር ያልሆኑ፣ ያልተመረቱ ወይም ያልለሙ የሶስተኛ-ወገን መሳሪያዎች ወይም ምርቶችን ያካትታሉ። Microsoft ለእነዚህ የሶስተኛ-ወገን መሳሪያዎች እና ምርቶች ኃላፊነት የለበትም።
  • v. የሶፍትዌር ዝማኔዎች። ከCortana አገልግሎቶች ጋር መገናኘት ለሚችል ማንኛውም መሳሪያ፣ የእርስዎን የCortana አገልግሎቶች ሶፍትዌር ስሪት ልንፈትሽ እንዲሁም የሶፍትዌር ዝማኔ ወይም የአወቃቀር ለውጦችን ልናወርድ ወይም ማናቸውም የCortana-ተጠቃሚ መሳሪያ አምራቾች የCortana አገልግሎት ሶፍትዌርን እንዲያዘምኑ ልናስገድድ እንችላለን።
ሙሉ ጽሁፍ
Outlook.comOutlook.com14h_Outlook_com
ማጠቃለያ
 • ሸ. Outlook.com። የ Microsoft መለያዎን ለመፍጠር የተጠቀሙት የ Outlook.com (ወይም @msn፣ @hotmail ወይም @live) ኢሜይል አድራሻ የ your Outlook.com ገቢ መልእክት ሳጥንዎ ወይም የ Microsoft መለያዎ ንቁ ሆነው እስከቆዩ ድረስ ለእርስዎ ልዩ ሆነው ይቆያሉ። የ Outlook.com የገቢ መልእክት ሳጥንዎ ወይም የ Microsoft መለያዎ በእርስዎ ወይም በ Microsoft በእነዚህ ውሎች መሰረት ከተዘጋ የኢሜይል አድራሻው ወይም የተጠቃሚ ስሙ ወደ ስርዓታችን ተመልሰው ጥቅም ላይ ውለው ለሌላ ተጠቃሚ ሊመደቡ ይችላሉ።
ሙሉ ጽሁፍ
የOffice አገልግሎቶችየOffice አገልግሎቶች14i_officeBasedServices
ማጠቃለያ
 • ቀ. የOffice አገልግሎቶች። Office 365 Home፣ Office 365 Personal፣ Office 365 University፣ Office Online፣ Sway፣ OneNote.com  እና ማንኛውም ሌላ የOffice 365 ምዝገባ ወይም የOffice ብራንድ ያላቸው አገልግሎቶች፣ ከዚህ በተለየ ከMicrosoft ጋር የተደረገ የንግድ መብት ከሌለዎት በስተቀር ለእርስዎ ለንግድ ዓላማ ለማይውል የግል ግልጋሎት የተፈቀዱ ናቸው።
ሙሉ ጽሁፍ
Microsoft የጤና አገልግሎቶችMicrosoft የጤና አገልግሎቶች14j_MicrosoftHealthServices
ማጠቃለያ
 • በ. Microsoft የጤና አገልግሎቶች።
  • i. HealthVault። HealthVault የተዘጋጀው እርስዎ የግል ጤና ነክ መረጃዎንና የሌሎች ሰዎችን መረጃ (እንደ ቤተሰብዎ የመሳሰሉ) በፈቃዳቸው እንዲያከማቹበት የታቀደ ነው። HealthVault መለያዎች በጤና አገልግሎት አቅራቢዎች ወይም ለማንኛውም ሌላ የንግድ ወይም የግል ያልሆነ አገልግሎት ጥቅም ላይ ሊውሉ አይችሉም። በመለያዎ ውስጥ ያለው መረጃ ሁልጊዜ ትክክል ወይም በቀኑ የታደሰ ላይሆን ስለሚችል በጤና አገልግሎት አቅራቢው መታየት ያለበት ለመረጃ ያህል ብቻ ነው። የ HealthVault አገልግሎት ለጤና አገልግሎት አቅራቢዎች ወይም ሌሎች የህክምና ወይም የኬዝ አስተዳደር አላማዎች መረጃዎችን መዝግቦ አይዝም። ለምሳሌ የ HealthVault መረጃዎች በዩናይትድ ስቴትስ ህጎች ላይ እንደተገለጸው የተወሰኑ የምዝገባ ስብስቦች አይደሉም። የጤና አገልግሎት አቅራቢው ማንኛውንም ከ HealthVault የተገኘ መረጃ በራሱ መዝገብ ውስጥ ለማካተት ከወሰነ አንድ ቅጂ በራሱ ስርዓት ውስጥ ማካተት አለበት። በመለያዎ ውስጥ የአንድ የተመዘገበ መረጃ የጋራ ጠባቂ ካለ (ምክንያቱም አንዳችሁ ሌላኛውን ስለጋበዛችሁ)፣ የጋራ ጠባቂው በምዝግቡ ላይ ሙሉ ቁጥጥር እንዳለውና በመዝገቡ ላይ ያልዎትን የመዳረሻ ስልጣን ሊያግደው፣ ሌሎች ሰዎችን የመዝግብ መዳረሻ እንደሚያስተዳድር እንዲሁም መዝገቡ መቼና እንዴት ጥቅም ላይ እንደዋ ጨምሮ የመዝገቡን ውሂብ የመመልከት መብት እንዳለው ያረጋግጣሉ። Microsoft የ Microsoft ያልሆኑ ዝርዝር መረጃዎችን (እንደ Facebook እና OpenID) ስለማይደግፍ የ HealthVault የደንበኞች ድጋፍ ለእነሱ በመለያ የመግባት ችግሮች ሊያግዝዎ አይችልም። በመለያ የመግቢያ ዝርዝር መረጃዎ ከጠፋብዎት ወይም ዝርዝር መረጃዎን ያገኙበት መለያ ከተዘጋ ያከማቹትን ውሂብ መልሰው ሊያገኙት በፍጹም አይችሉም። ቀጣይነት ያለውን መዳረሻ እንደተጠበቀ ለማቆየት በ HealthVault መለያዎ ከአንድ በላይ በመለያ የመግቢያ ዝርዝር መረጃን እንዲጠቀሙ እንመክርዎታለን። Microsoft እርስዎ ሊጠቀሟቸው ለሚችሉ የ Microsoft ያልሆኑ ዝርዝር መረጃዎች መስራትን፣ ድጋፍን ወይም ደህንነትን በተመለከተ ማረጋገጫ አይሰጥም ወይም አይቆጣጠርም እንዲሁም ሃላፊነቱን አይወስድም።
  • ii. Microsoft Band። Microsoft Band መሳሪያ እና መተግበሪያ የሕክምና መሳሪያዎች አይደሉም፣ ለአካል ብቃት እና ደህንነት አላማ ብቻ የታሰቡ ናቸው። በሽታዎችን ለመመርመር፣ ወይም በሽታን ወይም ሌላ የጤና ሁኔታን ለማዳን፣ ለማስታገስ፣ ለማከም፣ ወይም ለመከላከል ወይም ሌሎች ሁኔታዎች ታስበው የተነደፉ አይደሉም። ከMicrosoft Band በሚያገኟቸው መረጃዎች ላይ ተመስርተው ለሚወስኗቸው ውሳኔዎች በሙሉ Microsoft ኃላፊነቱን አይወስድም።
ሙሉ ጽሁፍ
ዲጂታል እቃዎችዲጂታል እቃዎች14k_DigitalGoods
ማጠቃለያ
 • ቨ. ዲጂታል እቃዎች። በ Microsoft Groove፣ Microsoft Movies & TV፣ Store እና ሌሎች ተዛማጅና ወደፊት ሊመጡ በሚችሉ አገልግሎቶች በኩል Microsoft በዲጂታል መልክ የሚያገኟቸውን ሙዚቃን፣ ምስሎችን፣ ቪዲዮ፣ ጽሁፍ፣ መጽሃፍትን፣ ጨዋታዎችን ወይም ሌሎች ነገሮችን ("ዲጂታል እቃዎችን") (እንደ ነገሩ ሁኔታ) እንዲያገኙ፣ እንዲያዳምጡ፣ እንዲመለከቱ፣ እንዲያጫውቱ ወይም እንዲያነቡ ያስችልዎታል። ዲጂታል እቃዎቹ የሚሆኑት ለግል፣ ንግድ ላልሆኑ መዝናኛ አገልግሎት ብቻ ነው። ማናቸውንም የዲጂታል እቃዎቹን ቅጂዎች ላለማሰራጨት፣ ላለማስተላለፍ፣ በይፋ ላለመጫወት ወይም በይፋ ላለማሳየት ይስማማሉ። ዲጂታል እቃዎቹ የ Microsoft ወይም የሶስተኛ ወገን ንብረት ሊሆኑ ይችላሉ። በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ የዲጂታል እቃዎቹን የሚመለከቱ መብቶችዎ በእነዚህ ውሎች፣ በቅጂ መብት ህግ እና በ https://go.microsoft.com/fwlink/p/?LinkId=723143 በሚገኘው የአጠቃቀም ደንቦች ተገዢ እንደሚሆን ተስማምተዋል። ከአገልግሎቶቹ ውስጥ በማንኛውም መንገድ ያገኟቸውን ማናቸውም ዲጂታል እቃዎች ለማስመሰል፣ ወይም ባለቤትነት ወይም ምንጫቸውን ለመቀየር ጨምሮ ለማንኛውም ምክንያት ለማስተካከል እንደማይሞክሩ ተስማምተዋል። Microsoft ወይም የዲጂታል እቃዎቹ ባለቤቶች ከጊዜ ወደጊዜ ዲጂታል እቃዎቹን ያለ ምንም ማስጠንቀቂያ ሊያስወግዷቸው ይችላሉ።
ሙሉ ጽሁፍ
OneDriveOneDrive14l_OneDrive
ማጠቃለያ
 • ተ. OneDrive.
  • i. የማከማቻ ምደባ። በ OneDrive መለያዎ ውስጥ በነጻ የደንበኝነት ምዝገባዎ ወይም ለOneDrive ከፍለው በተመዘገቡት የደንበኝነት ምዝገባ ከሚፈቀደው የውሂብ መጠን በላይ የሆነ ውሂብ ካለዎትና ትርፉን ይዘት እንዲያስወግዱ ወይም ተጨማሪ ማከማቻ ቦታ ያለው አዲስ ምዝገባ እንዲመዘገቡ በ Microsoft ለተላከልዎ መልዕክት ምላሽ ካልሰጡ መለያዎን የመሰረዝና በ OneDrive ያለዎትን ይዘት የመሰረዝ ወይም የማሰናከል መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ii. የአገልግሎት አፈጻጸም ብቃት። መሳሪያዎ፣ የበይነ መረብ ግንኙነቱ እንዲሁም Microsoft የሚሰጠውን አገልግሎት ብቃትና አስተማማኝነት ለማሻሻል በሚያደርገው ጥረት ላይ በመመስረት ይዘትን ወደ OneDrive በመስቀል ወይም በማመሳሰል ላይ መጓተት ሊያጋጥም ይችላል።
ሙሉ ጽሁፍ
Microsoft RewardsMicrosoft Rewards14m_MicrosoftRewards
ማጠቃለያ
 • ቸ. Microsoft Rewards.
  • i. ፕሮግራም Microsoft Rewards ("ፕሮግራሙ") ተዋጅ የእንቅስቃሴ ነጥቦችን፣ ለምሳሌ መስፈርቱን የሚያሟሉ ፍለጋዎች፣ ግዥዎች፣ በMicrsoft Edge በማሰስ የሚያሳልፉትን ጊዜዎች እንዲሁም በMicrosoft የሚቀርቡ ሌሎች ግብዣዎች፣ እንዲያገኙ ያስችልዎታል። አቅርቦቶች እንደየገበያው ሊለያዩ ይችላሉ። ፍለጋ ማለት አንድ ሰው ለግለሰቡ የምርምር ዓላማ ከBing የፍለጋ ውጤቶችን ለማግኘት ሲል የሚያደርገው ጽሁፍን በእጅ በመተየብ የማስገባት ድርጊት ሲሆን፣ በሮቦት፣ ማክሮ ወይም ሌላ የተቀላጠፈ ሰው ሰራሽ ወይም የማታለል ዘዴን አያካትትም። ("ፍለጋ")። ግዥ ማለት በነጻም ሆነ በክፍያ ሸቀጦችን የመግዛት ወይም ከMicrosoft ዲጂታል ይዘት የማውረድ ወይም ፈቃድ የማግኘት ሂደት ነው። ("ግዥ"). የሽልማት ነጥቦች ለሁሉም ከMicrosoft የሚደረጉ ግዥዎች አይሰጡም። በ Microsoft Edge በንቃት ማሰስ ማለት አሳሹን በመሳሪያዎ ማያ ገጽ ላይ እንዲታይ ማድረግ (ለምሳሌ፦ ተክፍቶ በጥቅም ላይ መሆንና፣ በዚህም ምክንያት Microsoft Edge አሁን በሥራ ላይ ያለው መተግበሪያ እንደሆነ ለማመልከት አዶው በተግባር አሞሌ ላይ የነቃ ሲሆ)፣ እና ድር ጣቢያዎችን ለመመልከት አሳሹን መጠቀም፣ ቪዲዮዎችን በአሳሹ ውስጥ መመልከት፣ ኢሜይል መፈተሽ፣ እንዲሁም አሳሾች የሚሰጧቸውን ሌሎች ግልጋሎቶች በአሳሹ መጠቀም። Microsoft Edgeን በመጠቀም ነጥብ ለማግኘት፣ Bing የአሳሹ ነባሪ የፍለጋ ፕሮግራም መሆን ያለበት ሲሆን፣ በሩቅ መለኪያ በእርስዎ የWindows ቅንብሮች ውስጥ መንቃት አለበት። Microsoft በተጨማሪም ነጥቦችን ለማግኘት ከጊዜ ወደ ጊዜ ተጨማሪ ዕድሎችን ሊያቀርብ ይችላል፣ እናም እያንዳንዱ ነጥብ አስገኝ ግብዣ በቀጣይነት አይገኝም። የተገኙ ነጥቦችዎ በዋጅ ገጽ ውስጥ በ ("ሽልማቶች") ንጥሎች ሊዋጁ ይችላሉ። ለበለጠ መረጃ support.microsoft.com ("FAQ") ይመልከቱ።
   • 1. የፕሮግራም መስፈርቶች። ልክ የሆነ የMicrosoft መለያ ያስፈልግዎታል እንዲሁም መሳሪያዎችዎ ዝቅተኛውን የስርዓት መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው። ፕሮግራሙ በበዛት የሚጠየቁ ውስጥ በተዘረዘሩት ገበያዎች ውስጥ ላሉ ተጠቃሚዎች ክፍት ነው። አንድ ግለሰብ ከአንድ በላይ የኢሜይል አድራሻ ቢኖረውም እንኳን ግለሰቦች ከአንድ በላይ የፕርግራም መለያ ሊኖራቸው አይችልም፤ ቤተሰቦች ሊኖራቸው የሚችለው በስድስት መለያዎች የተገደበ ነው። ፕሮግራሙ የሚያገለግለው ለእርስዎ ግላዊ እና ለንግድ ያልሆነ ጥቅም ብቻ ነው።
   • 2. ነጥቦች። ነጥቦችዎን በመዋጃ ማዕከል ውስጥ ከተካተተ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ካልሆነ በቀር፣ ነጥቦችን ማስተላለፍ አይችሉም። ነጥቦች የእርስዎ ግላዊ ሃብት አይደሉም፣ በመሆኑም እነርሱን በመሸጥና በመለወጥ የብር ኖቶች ወይም ገንዘብ መቀበል አይችሉም። ነጥቦች ለእርስዎ የሚሰጡት በማስተዋወቂያ መሰረት ነው። ነጥቦችን መግዛት አይችሉም። Microsoft ለአንድ ሰው፣ ለአንድ ቤተሰብ፣ ወይም በተቀመጠ የጊዜ መጠን ውስጥ (ለምሳሌ በቀን) የሚሰጠውን የነጥቦች ወይም ሽልማቶች መጠን ሊገድብ ይችላል። በፕሮግራሙ ውስጥ በአንድ የቀን መቁጠሪያ ዓመት ከ 550,000 ነጥቦች በላይ መዋጀት አይችሉም። በፕሮግራሙ ውስጥ የተገኙ ነጥቦች፣ በMicrosoft ወይም ሶስተኛ ወገኖች በሚሰጡ ሌሎች ፕሮግራሞች ውስጥ ዋጋ የሌላቸው ሲሆን ከእነዚያ ጋር በመጣመር ጥቅም ላይ መዋል አይችሉም። ለ18 ወራት ምንም ነጥቦችን ካላገኙ ወይም ካልዋጁ፣ ያልተዋጁ ነጥቦች ጊዜያቸው ያበቃል።
   • 3. ሽልማቶች ነጥቦችዎን መዋጃ ማዕከልን በመጎብኘት መዋጀት ወይም ለተዘረሰረ የትርፍ ያልሆነ ድርጅት መለገስ ይችላሉ። ለአንድ ሽልማት የተገደበ አቅርቦት ብቻ ሊኖር ይችላል፣ እነዚያም ሽልማቶች መጀመሪያ የመጣ ቀድሞ ያገኛል በሚለው መርኅ መሰረት ይታደላሉ። እንደ የመልዕክት አድራሻ እና ስልክ ቁጥር (VOIP ወይም ከክፍያ ነጻ ያልሆነ) ያሉ ተጨማሪ መረጃዎችን ሊጠየቁ ይችላሉ ፣ እንዲሁም ለሽልማቶቹ የማታለል-መከላከያ ኮድ እንዲያስገቡ ወይም ተጨማሪ ሕጋዊ ሰነዶችን እንዲፈርሙ ሊጠየቁ ይችላሉ። አንድ ጊዜ ሽልማት ካዘዙ፣ ተፈጻሚነት ባለው ሕግ መሰረት ግድፈት ያለበት ምርት ቢሆን መሰረዝ ወይም ነጥብዎን ተመላሽ በማድረግ መመለስ አይችሉም፣ በመደብር ውስጥ የሌለ ወይም በሌላ ምክንያት የማይገኝ ሽልማት ቢያዙ Microsoft በራሱ ምርጫ ይወስናል፣ ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው ሽልማት ልንሸልምዎ ወይም ነጥቦችዎን ተመላሽ ልናደርግ እንችላለን። Microsoft በመዋጃ ማዕከል ውስጥ የሚሰጡ ሽልማቶችን ሊለውጥ ወይም የተወሰኑ ሽልማቶችን መስጠትን ሊያቋርጥ ይችላል። አንዳንድ ሽልማቶች የዕድሜ ብቁነት መስፈርት ሊኖራቸው ይችላል። እንዲህ አይነት መስፈርቶች አግባብነት ባለው ግብዣ ውስጥ ይካተታሉ። ሽልማቱን ለመቀበል አስፈላጊ ለሆኑ የፌዴራል፣ የግዛት፣ እና አካባቢያዎ ቀረጦችና ሌሎች ወጪዎች ኃላፊነቱን ይወስዳሉ። ሽልማቶች፣ ሽልማትዎን በሚያዙ ጊዜ ወዳቀረቡት የኢሜይል አድራሻ ይላካሉ፣ ስለዚህ የኢሜይል አድራሻዎን ወቅታዊ ያድርጉ። መረከብ ያልቻሉ ሽልማቶች ዳግም አይሰጡም እናም በፈቃድ እንደተተዉ ይቆጠራሉ። ሽልማቶች ለዳግም-ሽያጭ መቅረብ አይችሉም።
   • 4. በፕሮግራሙ ውስጥ ያለዎትን ተሳትፎ መሰረዝ። ቢያንስ በ 18-ወር ጊዜ ውስጥ በመለያ ካልገቡ የፕሮግራም መለያዎ ይሰረዛል። በተጨማሪም፣ Microsoft፣ አላግባብ በመነካካት፣ ፕሮግራሙን ያላግባብ በመጠቀም ወይም በማጭበርበር፣ ወይም ይህን ውል በማፍረስ ምክንያት የፕሮግራም መለያውን የመሰረዝ መብቱን ያስጠብቃል። ፕሮግራሙ ሲሰረዝ (በእርስዎ ወይም በእኛ) ወይም ፕሮግራሙ በእገዳ ከቆየ፣ ነጥቦችዎን ለመዋጀት 90 ቀናት ይኖሩዎታል፤ ያ ካልሆነ ግን እነዚያ ነጥቦች በፈቃድ እንደተተዉ ይቆጠራሉ። በሚሰረዝበት ጊዜ፣ ፕሮግራሙን የመጠቀም መብትዎና ለወደፊቱ ነጥብ የማጠራቀም ሂደትዎ ያበቃል።
   • 5. ሌሎች ሁኔታዎች። Microsoft ፕሮግራሙን ያላግባብ የነካኩ እንደሆነ ወይም ማንኛውንም የፕሮግራሙን አካል ያላግባብ እንደተጠቀሙ ወይም ይህን ውል በሚጥሱ እንቅስቃሴዎች ላይ እንደተሳተፉ ካመነ፣ Microsoft እርስዎን ከፕሮግራም ውጭ የማድረግ መብቱን፤ ወደ ፕሮግራሙ ወይም ሽልማቶችዎ ያለዎትን መዳረሻ የማሰናከል፤ እና/ወይም ነጥቦችን፣ ሽልማቶችን እና ልገሳዎችን የማገድ፣ መብቱን፣ ይጠብቃል።
ሙሉ ጽሁፍ
አጠቃላይ ድንጋጌዎችአጠቃላይ ድንጋጌዎች16_17_18_miscellaneous
ማጠቃለያ

14. አጠቃላይ ድንጋጌዎች። ይህ ክፍል እና ክፍሎች 1፣ 9 (ከእነዚህ ውሎች ማብቂያ ጊዜ በፊት ለተከፈሉ መጠኖች)፣ 10፣ 11፣ 12፣ 15፣ 17 እና ሌሎች በውላቸው መሰረት እነዚህ ውሎች ካበቁ በኋላ ተፈጻሚ የሚሆኑ፣ የእነዚህ ውሎች ጊዜ ካበቃም በኋላ ቢሆን ተፈጻሚ ይሆናሉ። ተፈጻሚ በሆነው ህግ እስከሚፈቀደው መጠን ድረስ በሙሉም ሆነ በከፊል፣ በማንኛውም ጊዜ ለእርስዎ ማሳወቅ ሳይጠበቅብን እነዚህን ውሎች ለሌላ ሰው ልናስተላልፍ፣ በእነዚህ ውሎች ስር ያሉብንን ግዴታዎች ለሌላ ሰው በንዑስ ውል ልናስተላልፍ፣ ወይም በእነዚህ ውሎች ውስጥ ያሉንን መብቶች ለሌላ አካል ንዑስ ፈቃድ ልንሰጥባቸው እንችላለን። እነዚህን ውሎች አሳልፈው ሊሰጡ ወይም አገልግሎቶቹን ለመጠቀም ማናቸውንም አገልግሎቶች ሊያስተላልፉ አይችሉም። ይህ እርስዎ አገልግሎቱን እንዲጠቀሙ በእርስዎና በ Microsoft መካከል የተደረገው አጠቃላይ ውል ነው። ይህ ውል የአገልግሎቱን አጠቃቀምዎን በተመለከተ በእርስዎና በ Microsoft መካከል ከአሁን በፊት የተደረገ ማንኛውም ውል በመሻር ተፈጻሚ ይሆናል። ወደነዚህ ውሎች በሚገቡበት ወቅት በዚህ ውል ላይ በግልጽ ከተቀመጡት በስተቀር በሌላ በማንኛውም መግለጫ፣ ውክልና፣ ዋስትና፣ መረዳት፣ ቃል ኪዳን ወይም ማስተማመኛ ላይ ተማምነው አይደለም። ሁሉም የእነዚህ ደንቦች ክፍሎች በተገቢው ህግ በሚፈቀደው ከፍተኛው መጠን ተፈጻሚ ይሆናሉ። አንደ ፍርድ ቤት ወይም የግልግል ዳኛ የነእዚህን ውሎች አንድ ክፍል እንደተጻፈው መተግበር እንደማንችል ከወሰነ እነዚህን ድንጋጌዎች በተገቢው ህግ ስር መፈጸም እስከከሚችለው ድረስ በሌሎች ተመሳሳይ ድንጋጌዎች እንተካቸዋለን። ነገር ግን የውሉ ቀሪ ድንጋጌዎች አይለወጡም። እነዚህ ደንቦች ሙሉ በሙሉ ለእርስዎና ለእኛ ጥቅም ናቸው። እነዚህ ደንቦች ከ Microsoft ወራሾችና ተሹዋሚዎች በስተቀር ለማንም ሌላ ሰው ጥቅም አይደሉም። የክፍል ርእሶች ለማጣቀሻ ብቻ ሲሆኑ ምንም የህግ ውጤት የላቸውም።

15. የይገባኛል ጥቄዎች በአንድ አመት ውስጥ መሞላት አለባቸው። ከእነዚህ ውሎች ወይም ከአገልግሎቶቹ ጋር የተዛመዱ ማናቸውም ክሶች የአካባቢዎ ህግ ክስ ለማቅረብ ረጅም ጊዜ እስካልጠየቀ ድረስ በፍርድ ቤት (ወይም ክፍል 10 (መ) ተፈጻሚ የሚሆን ከሆነ በግልግል ዳኛ) ክሱን ለመጀመሪያ ጊዜ ማቅረብ ከሚችሉበት ጊዜ ጀምሮ በአንድ አመት ውስጥ መቅረብ አለበት። በዚያ ጊዜ ውስጥ ካልተሞላ በቋሚነት ይታገዳል።

16. ወደ ውጪ የመላክ ህጎች። ሁሉንም ሶፍትዌሩ እና/ወይም አገልግሎቶቹ ላይ ተፈጻሚ ሊሆኑ የሚችሉ በመዳረሻዎች፣ በመጨረሻ ተተቃሚዎችና በመጨረሻ አገልግሎቶች ላይ ገደብን የሚካትቱ የአገር ውስጥና አለም አቀፍ ወደ ውጪ የመላክ ህጎችና መመሪያዎች ማክበር አለብዎ። በጂኦግራፊያዊና ሌሎች ገደቦች ላይ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት https://go.microsoft.com/fwlink/?linkid=868968 እና https://www.microsoft.com/exporting ይጎብኙ።

17. መብትን መጠበቅ እና ስለ ግብረመልስ። በእነዚህ ውሎች ስር በግልጽ ከተቀመጠው በስተቀር፣ በማንኛውም የአዕምሮ ንብረት ማስከበሪያ፣ ዕውቀት፣ የቅጅ መብት፣ የንግድ ምስጤሮች፣ የንግድ ምልክቶች ወይም ሌላ በMicrosoft ወይም በማንኛውም ተዛማጅ አካል የተያዙ ወይም ቁጥጥር ስር ያሉ የአ ዕምሯዊ ንብረቶች፣ ማንኛውንም ስም፣ የንግድ ምስል፣ አርማ ወይም እኩያዎችን ጨምሮ ነገርን ግን በዚያ ሳይወሰን በእነዝህ ሁሉ Microsoft ለእርስዎ የፈቃድም ሆነ ሌላ ማንኛውም መብት አይሰጥም። ለMicrosoft ማንኛውንም ሃሳብ፣ ምክረ ሃሳብ፣ ጥቆማ፣ ወይም አስተያየት ለአዲስ ምርቶች፣ ቴክኖሎጂዎች፣ ማስተዋወቂያዎች፣ የምርት ስሞች፣ የምርት ግብረመልስ እና የምርት ማሻሻያዎችን ያለገድብ በማካተት ("ግብረመልስ")፣ ለMicrosoft ያለ ክፍያ፣ የመብት ክፍያ ወይም ሌሎች ግዴታዎች፣ እንዲሰራበት፣ ሰርቶበት እንዲሆን፣ ሁለተኛ ደረጃ ሥራዎችን እንዲሰራ፣ እንዲጠቀም፣ እንዲያጋራ፣ እንዲሁም በማንኛውም መንገድ እና ለማንኛውም ዓላማ ለንግድ ሥራ እንዲያውል መብት ይሰጣሉ። Microsoft የእርስዎን ግብረመልስ በማካተቱ ሶፍትዌሮቹን፣ ቴክኖሎጂዎችን ወይም ሰነዶቹን ለሌላ ሶስተኛ አካል ፈቃድ እንዲሰጥ ለሚያስገድድ ፈቃድ ተገዥ የሆነ ግብረመልስ አይሰጡም።

ሙሉ ጽሁፍ
ማስታወቂያዎችማስታወቂያዎችNOTICES
ማጠቃለያ

የአእምሮአዊ ንብረት መብት ጥሰት ክሶችን ለማቅረብ ማሳወቂያዎችና ስነ ስርዓቶች። Microsoft የሶስተኛ ወገኖች የአአምሮአዊ ንብረት መብቶችን ያከብራል። የቅጂ መብት ጥሰትን የሚመለከት ክስን ጨምሮ የአእምሮአዊ ንብረት መብት ጥሰት ማሳወቂያን መላክ የሚፈልጉ ከሆነ እባክዎ የጥሰት ማሳወቂያዎችን ለማቅረብ የምንጠቀምባቸውን ስነ ስርዓቶች ይጠቀሙ። ከእዚህ የአሰራር ሂደት ጋር ተዛማጅ የሆኑ መጠይቆች ብቻ ምላሽ ያገኛሉ።

Microsoft በ ርእስ 17፣ የዩናይትድ ስቴትስ ኮድ፣ ክፍል 512 ውስጥ የተጠቀሰውን የቅጂ መብት ጥሰቶችን የተመለከቱ ማሳወቂዎች ሲሰጡ ምላሽ የሚሰጥበትን ሂደት ይጠቀማል። አስፈላጊ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ Microsoft በተደጋጋሚ ጥሰቶችን የሚፍጽሙ የ Microsoft አገልግሎቶች ተጠቃሚዎች መለያዎችን ሊያሰናክል ወይም ሊያቋርጥ ይችላል።

በማስታወቂያ ውስጥ የአእምሮአዊ ንብረት ስጋቶችን የተመለከቱ ማሳወቂያዎችና ስነ ስርዓቶች። እባክዎ በማስታወቂያ አውታረ መረባችን ላይ ስላሉ የአእምሮአዊ ንብረት ስጋቶችን በተመለከተ የአእምሮአዊ ንብረት መመሪያዎችን ይመልከቱ።

የቅጂ መብትና የንግድ ምልክት ማስታወቂያዎች። አገልግሎቶቹ © 2018 Microsoft Corporation እና ወይም አቅራቢዎቹ One Microsoft Way, Redmond, WA 98052, U.S.A. የቅጂ መብት ጥበቃ የሚደረግላቸው ናቸው። ሁሉም መብቶች በህግ የተጠበቁ ናቸው። Microsoft እና የሁሉም የ Microsoft ምርቶች፣ ሶፍትዌር እና አገልግሎቶች ስሞች፣ አርማዎችና አዶዎች በዩናይትድ ስቴትስ እና/ወይም ሌሎች አገሮች የ Microsoft የንግድ ምልክቶች ወይም የተመዘገቡ የንግድ ምልክቶች ናቸው። የእውነተኛ ኩባንኛዎች ስሞች እና ምርቶች የባለቤቶቻቸው የንግድ ምልክቶች ሊሆኑ ይችላል። ሁሉም በዚህ ደንቦች ላይ በግልጽ ያልተሰጡ መብቶች እንደተጠበቁ ናቸው። በተወሰነ የ Microsoft የድር ጣቢያ አገልጋይ ላይ ጥቅም ላይ የሚውል የተወሰነ ሶፍትዌር በከፊል የኢንዲፔንደንት JPEG ግሩፕ የስራ ውጤት ነው። Copyright © 1991-1996 Thomas G. Lane. ሁሉም መብቶች በህግ የተጠበቁ ናቸው። በተወሰነ የ Microsoft የድር ጣቢያ አገልጋይ ላይ ጥቅም ላይ የሚውለው "gnuplot" ሶፍትዌር በ © 1986‑1993 Thomas Williams, Colin Kelley የቅጂ መብት ጥበቃ የሚደረግለት ነው። ሁሉም መብቶች በህግ የተጠበቁ ናቸው።

የህክምና ማስታወቂያ። Microsoft የህክምና ወይም ሌላ ምንም አይነት የጤና ጥበቃ ምክር፣ ምርመራ ወይም ህክምና አይሰጥም። ማንኛውንም አይነት የህክምና ችግር፣ አመጋገብ፣ የአካል ብቃት ወይም የደህንነት ፕሮግራም በተመለከተ ሁልጊዜም የሃኪምዎን ወይም ሌላ ብቃት ያለው የጤና እንክብካቤ ሰጪ ባለሞያን ምክር ያግኙ። በአገልግሎቶቹ ላይ ወይም በእነሱ ውስጥ ባገኙት መረጃ ምክንያት በፍጹም የባለሞያን የህክምና ምክር ችላ አይበሉ ወይም ምክር መጠየቅዎን አያዘግዩ።

የአክሲዮን ጥቅሶችና የማውጫ ውሂብ (የማውጫ ዋጋዎችን ጨምሮ)። © 2013 Morningstar, Inc. ሁሉም መብቶች በህግ የተጠበቁ ናቸው። እዚህ ውስጥ የተካተተው መረጃ: (1) የሞርኒንግስታር እና/ወይም የይዘት አቅራቢዎቹ ንብረት ነው፤ (2) ሊቃዳና ሊሰራጭ አይችልም፤ እንዲሁም (3) ትክክለኛ፣ የተሟላና ወቅቱን የጠበቀ እንደሆነ ዋስትና የለውም። ሞርኒንግስታርም ሆነ የይዘት አቅራቢዎቹ ይህንን መረጃ በማንኛውም መንገድ ከመጠቀም ለሚመጣው ጉዳት ሃላፊነትን አይወስዱም። ከአሁን በፊት ያለ የአፈጻጸም ብቃት የወደፊት ውጤቶች ዋስትና አይሆንም።

ማናቸውንም ገንዘብ ነክ ሰነዶች ወይም የኢንቨስትመንት ምርቶች (ለምሳሌ የመሳሪያው ወይም የኢንቨስትመንት ምርት ዋጋ፣ ትርፍ እና/ወይም አፈጻጸም የሚመሰረትበት፣ የሚዛመድበት ወይም ከማውጫዎቹ አንዱን የሚከታተል ወይም ለማውጫዎቹ ወኪል የሚኮንባቸው ተሳቢዎች፣ የተዋቀሩ ምርቶች፣ የኢንቨስትመንት ፈንዶች፣ በኤክስቼንጅ-የሚሸጡ ፈንዶችየኢንቨስትመንት ፖርትፎሊዮ ወዘተ) ማውጣት፣ መፍጠር፣ ስፖንሰር ማድረግ፣ መሸጥ፣ ገበያ መፈለግ ወይም ማስተዋወቅ ጋር በተያያዘ ማናቸውንም የ Dow Jones IndexesSM፣ የማውጫ ውሂብ ወይም የDow Jones ምልክቶችን ያለ Dow Jones ፈቃድ አየቻልም።

ገንዘብ ነክ ማሳወቂያ። Microsoft በፌዴራል የሴኪዩሪቲስ ህግ ወይም በሌሎች አገሮች የሴኪዩሪቲስ ህጎች የተመዘገበ ደላላ ወይም የመዋእለ ነዋይ ፈሰት አማካሪ ስላልሆነ ሴኪዩሪቲዎችን ወይም ሌሎች ገንዘብ ነክ ምርቶችን ወይም አገልግሎቶች ላይ ኢንቨስት የማድረግን፣ የምግዛትን ወይም የመሸጥን ተመካሪነት በተመለከተ ለግለሰቦች ምክር መስጠት አይችልም። በአገልግሎቶቹ ውስጥ የተካተተ ማንኛውም ነገር ማናቸውንም ሴኪዩሪቲ የመግዛት ወይም የመሸጥ ጥያቄ ወይም ማግባባት አይደለም። Microsoft እና የአክሲዮን ጥቅስ ፈቃድ ሰጪዎቹ ወይም የማውጫ ውሂብ አቅራቢዎቹ ማንኛውምን አይነት የተወሰነ ገንዘብ ነክ ምርቶች ወይም አገልግሎቶች አይደግፉም ወይም አይመክሩም። በአገልግሎቶቹ ውስጥ ካሉት ነገሮች አንዳቸውም እንደ የባለሙያ ምክር እንዲያገለግሉ የታሰቡ አይደሉም፣ በዚያ ሳይገደብ ፣ የኢንቨስትመንት እና የግብር ምክሮችን ጨምሮ፡፡

ስለ H.264/AVC፣ MPEG-4 Visual እና VC-1 የቪዲዮ ደረጃዎች+ የተሰጠ ማሳወቂያ ሶፍትዌሩ በMPEG LA, L.L.C ፈቃድ ሊሰጣቸው የሚችሉ H.264/AVC፣ MPEG-4 Visual እና/ወይም VC-1 ኮዴክ ቴክኖሎጂን ሊያካትት ይችላል። ይህ ቴክኖሎጂ የውሂብ ማጨቂያ ቪዲዮ መረጃ ቅርጸጽ ነው። MPEG LA, L.L.C. ይህንን ማሳወቂያ ይጠይቃል:

ይህ ምርት በ H.264/AVC፣ MPEG-4 VISUAL እና VC-1 የፓተንት ፖርትፎሊዮ ፈቃዶች ስር ለግልና ለንግድ ላልሆኑ አገልግሎቶች (ሀ) ቪዲዮን ከደረጃው ጋር በሚጣጣም መልኩ ኢንኮድ ለማድረግ ("የቪዲዮ ደረጃዎች") እና/ወይም (ለ) በግልና ንግድ ባልሆነ እንቅስቃሴ ውስጥ የተሰማራ ተጠቃሚ ኢንኮድ ያደረጋቸውን እና/ወይም እንደዚህ አይነት ቪዲዮዎችን የማቅረብ ፈቃድ ካለው ቪዲዮ አቅራቢ የተገኙ የ H.264/AVC፣ MPEG-4 VISUAL እና VC-1 ቪዲዮዎች ኮዲንግ መፍታት። ይህ ምርት ከዚህ ሶፍትዌር ጋር በነጠላ አንቀጽ ውስጥ ተካተተም ወይም አልተካተተም ማናቸውም ፈቃዶች ወደ ሌላ ምርት አይስፋፉም። ምንም ፈቃድ ለሌላ ለማንኛውም አገልግሎት አልተሰጠም እንደተሰጠም መቆጠር የለበትም። ተጨማሪ መረጃ ከ MPEG LA, L.L.C. ማግኘት ይቻላል። የ MPEG LA ድር ጣቢያን ይመልከቱ።

ለማስረጂያ አላማዎች ብቻ ይህ ማሳወቂያ በእነዚህ ውሎች ስር የሚከተሉትን የማያካትቱ ለዚያ ንግድ የግል ለሆኑ ለመደበኛ የንግድ አገልግሎቶችን አይገድብም (i) ሶፍትዌሩን ለሶስተኛ ወገኖች ዳግም ማሰራጨት ወይም (ii) ለሶስተኛ ወገኖች ለማሰራጨት ደረጃቸውን የጠበቁ ቪዲዮዎችን በሚጠብቁ ቴክኖሎጂዎች ነገሮችን መፍጠር።

ሙሉ ጽሁፍ
መደበኛ የመተግበሪያ ፈቃድ ውሎችመደበኛ የመተግበሪያ ፈቃድ ውሎችSTANDARDAPPLICATIONLICENSETERMS
ማጠቃለያ

መደበኛ የመተግበሪያ ፈቃድ ውሎች

MICROSOFT STORE፣ WINDOWS STORE፣ AND XBOX STORE

እነዚህ የፈቃድ ደንቦች በእርስዎና በመተግበሪያ አዘጋጁ መካከል የሚደረጉ ስምምነቶች ናቸው። እባክዎ ያንብቧቸው። ማናቸውንም ዝማኔዎች እና የመተግበሪያ ደጋፊዎችን ጨምሮ፣ መተግበሪያው ከተለየ ውል ጋር የሚመጣና፣ ይህ ከሆነም እነዚያ ውሎች ተፈጻሚ የሚሆኑ ካልሆነ በስተቀር፣ከMicrosoft Store፣ Windows Store፣ ወይም Xbox Store (እያንዳንዱም በፈቃድ ውሎች ውስጥ እንደ “Store” የተጠቀሰ) በሚያወርዷቸው መተግበሪያዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ።

መተግበሪያውን በማውረድዎ ወይም በመጠቀምዎ ወይም ከእነዚህ ውስጥ አንዱን ለማድረግ በመሞከርዎ እነዚህን ውሎች ይቀበላሉ። የማይቀበሏቸው ከሆነ ምንም መብት የሌለዎት ሲሆን መተግሪያውን ማውረድ ወይም መጠቀም የለብዎትም።

የመተግበሪያ አታሚ ማለት Store ውስጥ በተገለጸው መሰረት በመተግበሪያው ላይ ለእርስዎ ፈቃድ የሰጠው አካል ማለት ነው።

በእነዚህ የፈቃድ ውሎች ከተስማ ከዚህ በታች ያሉት መብቶች አሉዎት።

 • 1. የመጫንና የመጠቀም መብቶች፤ የሚያልፍባቸው ጊዜ። መተግበሪያውን በእኛ የአጠቃቀም ደንቦች ላይ በተቀመጠው መሰረት በWindows መሣሪያዎች ወይም XBOX ኮንሶሎች ላይ መጫን እና መጠቀም ይችላሉ። Microsoft የእኛን የአጠቃቀም ደንቦች በማንኛውም ጊዜ የመለወጥ መብቱን ያስጠብቃል።
 • 2. በይነመረብ ላይ የተመሰረቱ አገልግሎቶች።
  • ሀ. በይነመረብ ላይ የተመሰረቱ አገልግሎቶች ወይም ገመድ አልባ አገልግሎቶች ፈቃደኝነት። መተግበሪያው በበይነመረብ፣ ገመድ አልባ አውታረ መረብን ጨምሮ፣ ከኮምፒውተር ስርዓቶች ጋር ከተገናኘ መተግበሪያዎን መጠቀምዎ መደበኛ የመሳሪያ መረጃ (ስለመሳሪያዎ፣ ስርዓትዊ እና የመተግበሪያ ሲፍትዌሩ ቴክኒካዎ መረጃና የመሳሰሉት) በበይነመረብ ላይ ለተመሰረቱ ወይም ለገመድ አልባ አገልግሎቶች እንዲተላለፍ ፈቃድዎን እንደሰጡ ቆጠራል። መተግበሪያውን ተጠቅመው በሚደርሱዋቸው አገልግቶችን በመተመለከተ ሌሎች ውሎች ከቀረቡ እነዚያ ውሎች ተፋጸሚ ይሆናሉ።
  • ለ. በይነመረብ ላይ የተመሰረቱ አገልግሎቶችን ያለአግባብ መጠቀም። ማንኛውንም በይነ መረብ ላይ የተመሰረተ አገልግሎትን የሌሎች ሰዎች የመጠቀም ነጻነትን በሚነካ መልኩ ወይም ገመድ አልባ አውታረ መረቡን በሚጎዳ መልኩ መጠቀም የለብዎትም። አገልግሎቱን በማንኛውም መንገድ ወደ ማንኛውም አገልግሎት፣ ውሂብ፣ መለያ ወይም አውታረ መረብ መዳረሻ ለማግኘት መጠቀም አይችሉም።
 • 3. ፈቃዱ የሚሸፍናቸው ነገሮች። መተግበሪያው ፈቃድ ተሰጠበት እንጂ አልተሸጠም። ይህ ስምምነት መተግበሪያውን ለመጠቀም የተወሰኑ መብቶች ይሰጥዎታል። ከ Microsoft ጋር ባለዎት ስምምነት መሰረት በስልክዎ ላይ ያሉ መተግበሪያዎችን የመጠቀም መብትዎን Microsoft ካሰናከለው ማናቸውም ተዛማጅ መብቶች ይቋረጣሉ። የመተግበሪያው አታሚ የተቀሩትን መብቶች ሁሉ ያስጠብቃል። ተፈጻሚ የሆነው ህግ ይህ ገደብ እንዳለ ሆኖም ተጨማሪ መብቶች ካልሰጥዎ በስተቀር መተግበሪያውን መጠቀም የሚችሉት በዚህ ስምምነት ላይ በግልጽ በተፈቀደው መሰረት ብቻ ነው። ይህንን በማድረግ መተግበሪያውን በተወሰነ መንገዶች ብቻ እንዲጠቀሙት የሚፈቅዱልዎን ቴክኒካዊ ገደቦች በጠቅላላ ማክበር ለብዎ። የሚከተሉትን ማድረግ አይችሉም:
  • ሀ. የመተግበሪያውን ማንኛውም ቴክኒካዎ ገደብ ለማለፍ መሞከር።
  • ለ. ይህ ገደብ ቢኖርም ተፈጻሚ የሆነው ህግ በግልጽ እስከሚፈቅደው ድረስ ብቻ ካልሆነ በስተቀር መተግበሪያውን ገልብጦ መስራት፣ መልሶ መገጣጠም ወይም መበታተን።
  • ሐ.ይህ ገደብ ቢኖርም በዚህ ስምምነት ላይ ከተገለጸው ወይም ተፈጻሚ በሆነው ህግ ከተፈቀደው ቅጂ በላይ ማባዛት።
  • መ. መተግበሪያውን ማተም ወይም በሌላ መንገድ ሌሎች እንዲቀዱት የሚገኝ ማድረግ።
  • ሠ. መተግበሪያውን ማከራየት፣ ሊዝ መስጠት ወይም ማበደር።
  • f. መተግበሪያውን ወይም ይህን ስምምነት ለሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ።
 • 4. ሰነድ። ከመተግበሪያው ጋር የቀረበ ሰነድ ካለ ሰነዱን ለግል ማጣቀሻ አገልግሎቶች ሊያባዙትና ሊጠቀሙት ይችላሉ።
 • 5. የቴክኖሎጂና ወደ ውጪ የመላክ ገደቦች። መተግበሪያው የዩናይትድ ስቴትስ ወይም የአለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ቁጥጥር ወይም ወደ ውጪ የመላክ ህጎችና መመሪያዎች ተገዢ ሊሆን ይችላል። በመተግበሪያው ጥቅም ላይ የዋሉ ወይም የሚደገፉ ቴክኖሎጂዎች ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑትን ሁሉንም የአገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ወደ ውጪ የመላክ ህጎች ማክበር አለብዎ። እነዚህ ህጎች በመዳረሸዎች፣ በመጨረሻ ተጠቃሚዎችና በመጨረሻ አገልግሎቶች ላይ ገደቦችን ያካተቱ ናቸው። የ Microsoft የንግድ ምልክት ለተደረገባቸው ምርቶች ወደ Microsoft ወደ ውጪ የመላክ ድር ጣቢያ ይሂዱ።
 • 6. የድጋፍ አገልግሎቶች። የትኛዎቹን የድጋፍ አገልግሎቶች ማግኘት እንደሚችሉ ለመወሰን የመተግበሪያ አታሚውን ያግኙ። Microsoft፣ የሃርድዌርዎ አምራች እና የገመድ አልባ አገልግሎት አቅራቢዎ (ከነሱ መካከል አንዱ የመተግበሪያ አታሚ ካልሆነ በስተቀር) ለመተግበሪያው የድጋፍ አገልግሎቶችን የማቅረብ ሃላፊነት የለባቸውም።
 • 7. አጠቃማይ ስምምነቱ። ይህ ስምምነት፣ ማንኛውም የግላዊነት መመሪያ፣ ከመተግበሪያው ጋር አብሮ የሚመጣ ማንኛውም መተግበሪያ እንዲሁም የአጋዦች ውሎች እንዲሁም ማዘመኛዎች ለመተግበሪያው በእርስዎና በመተግበሪያው አዘጋጅ መካከል እንደተደረገ አጠቃላይ ስምምነት ይቆጠራሉ።
 • 8. ተፈጻሚ የሚሆነው ህግ።
  • ሀ. ዩናይትድ ስቴትስና ካናዳ። መተግበሪያውን በዩናይትድ ስቴትስ ወይም ካናዳ ውስጥ ከተቀበሉ፣ እርስዎ በሚኖሩበት ክልል ወይም አውራጃ (ወይም፣ የንግድ ሥራ ከሆኑ፣ የንግድ ሥራዎ ዋና አድራሻ በሚገኝበት) ውስጥ ያሉ ሕጎች የሕግ መርኆች መጣረስ ቢኖርም እንኳን የእነዚህን ውሎች ትርጓሜዎች፣ ስለ መጣሳቸው የሚቀርቡ አቤቱታዎችን እና ሌሎች አቤቱታዎችን (የሸማች ጥበቃ፣ ፍትሐዊ ያልሆነ ውድድር፣ እና የጉዳት አቤቱታዎችን ጨምሮ) ይገዛሉ።
  • ለ. ከዩናይትድ ስቴትስና ከካናዳ ውጪ። መተግበሪያውን የራስዎ ያደረጉት በሌላ አገር ከሆነ የዚያ አገር ህጎች ተፈጻሚ ይሆናሉ።
 • 9. የህግ ውጤት። ይህ ስምምነት የተወሰኑ በህግ የተሰጡ መብቶችን ይገልጻል። በእርስዎ ግዛት ወይመ አገር ህጎች ስር ሌሎ መብቶች ሊኖሩዎት ይችላሉ። ይህ ስምምነት የግዛትዎ ወይም የአገርዎ ህግ የማይፈቅዱ ከሆነ በግዛትዎ ወይም በአገርዎ ህግ ስር የተሰጠዎትን መብቶች አይለውጥም።
 • 10. የዋስትና ሃላፊነትን ማንሳት። የዚህ መተግበሪያ ፈቃድ የሚሰጠው "እንዳለ"፣ "ከነ አንከኖቹ" እና "እንደቀረበው" ነው። እሱን በመጠቀም የሚመጡ ስጋቶች ሁሉ የእርስዎ ናቸው። የመተግበሪያ አታሚው እራሱን፣ Microsoft ን (Microsoft የመተግበሪያው አታሚ ባልሆነ ጊዜ)፣ መተግበሪያው በአውታረ መረባቸው የሚቀርብባቸው ገመድ አልባ አገልግሎት ሰጪዎችን፣ እያንዳንዳቸው አጋሮቻችንን፣ ቸርቻሪዎቻችንን፣ ወኪሎቻችንንና አቅራቢዎቻችንን ("የሚሸፈኑ አካላትን") በመወከል መተግበሪያውን በተመለከተ ምንም አይነት ግልጽ ዋስትናዎችን፣ ማስተማመኛዎችን ወይም ሁኔታዎችን አይሰጥም። የመተግበሪያው ጥራት፣ ደህንነት፣ ምቾትና የአፈጻጸም ብቃትን የሚመለከት አጠቃላይ ሃላፊነት የእርስዎ ነው። መተግበሪያው ችግር ያለበት ሆኖ የተገኘ እንደሆነ የሁሉም እድሳት ወይም ጥገና ወጪ ኃላፊነት የሚወሰዱት እርስዎ ነዎት። በአካባቢዎ ህግ ስር ይህ ስምመነት ሊለውጣቸው የማይችል ተጨማሪ የደንበኛ መብቶች ሊኖሩዎት ይችላሉ። በአካባቢዎ ህጎች እስከሚፈቀደው መጠን ድረስ የሚሸፈኑ ወገኖች የሚለው ለመሸጥ መቻልን፣ ለአንድ የተወሰነ አላማ ብቁ መሆንን፣ ደህንነትን፣ ምቾትን እና ህግ አለመጣስን ጨምሮ ማንኛውንም በተዘዋዋሪ የተጠቆሙ ዋስትናዎችን ወይም ሁኔታዎችን አያጠቃልሉም።
 • 11. በካሳዎችና በጉዳት ካሳዎች ላይ ያሉ ገደቦችና አለማካተቶች። በህግ እስከተከለከለው ድረስ የጉዳት ካሳዎችን ለመጠየቅ ማንኛውም አይነት መሰረት ካለዎት ከመተግበሪያ አታሚው ሊጠይቁ የሚችሉት ለመተግበሪያው ከከፈሉትን የገንዘብ መጠን ወይም USD$1.00 መካከል ከፍተኛ የሆነውን ብቻ ነው። ሌሎች ማናቸውንም አይነት ጉዳቶች ተከታይነት ላላቸው ጉዳቶች፣ የትርፍ ማጣቶችን፣ ልዩ፣ ቀጥተኛ ያልሆኑ ወይም ድንገተኛ ጉዳቶችን ጨምሮ ማንኛውንም አይነት የጉዳት ካሳ ከመተግበሪያው አታሚ የመጠየቅ መብትዎን አሳልፈው ስለሰጡ መጠየቅ አይችሉም። የአካባቢዎ ህጎች እነዚህ ውሎች የማይሰጡ ቢሆንም ዋስትናዎችን፣ ማስተማመኛዎችን ወይም ሁኔታዎችን የሚደነግጉ ከሆነ ተፈጻሚነቱ የሚቆየው መተግበሪያውን ባወረዱ በ 90-ቀናት ውስጥ ብቻ ነው።

ይህ ገደብ ለሚከተሉት ተፈጻሚ ይሆናል:

 • በመተግበሪያው በኩል የቀረበ ማንኛውም መተግበሪያ ወይም አገልግሎት ጋር የተገናኘ ማንኛውም ነገር ላይ፤ እንዲሁም
 • የውል፣ ዋስትና፣ ማስተማመኛ ወይም ሁኔታዎች መጣስ፤ ከባድ ሃላፊነት፣ ቸልተኝነት ወይም ሌላ ከውል ውጪ የሚደርስ ሃላፊነት፤ የተጻፈ ህግ ወይም መመሪያ መጣስ፤ አለአግባብ መበልጸግ፤ ወይም በማንኛውም ሌላ ንድፈ ሃሳብ ስር ሁሉም ተፈጻሚ በሚሆነው ህግ እስከሚፈቀዱበት መጠን ድረስ።

በተጨማሪም የሚከተሉት ቢኖሩም ተፈጻሚ ይሆናል:

 • ይህ ካሳ ለደረሰብዎት ጉዳት ሙሉ በሙሉ ባይክስዎትም፤ ወይም
 • የመተግበሪያ አታሚው ጉዳቱ ሊከሰት እንደሚችል ሲያውቅ ወይም ማወቅ ሲኖበት።
ሙሉ ጽሁፍ
የሚሸፈኑ አገልግሎቶችየሚሸፈኑ አገልግሎቶችserviceslist
ማጠቃለያ

የሚከተሉት ምርቶች፣ መተግበሪያዎችና አገልግሎቶች በ Microsoft የአገልግሎቶች ስምነት የሚሸፈኑ ሲሆን በእርስዎ ገበያ ውስጥ ላይገኙ ይችላሉ።

 • Account.microsoft.com
 • Advertising.microsoft.com
 • Bing
 • Bing App for Android
 • Bing Apps
 • Bing Bots
 • Bing Business Bot
 • Bing Desktop
 • Bing Dictionary
 • Bing for Business
 • Bing Image and News (iOS)
 • Bing in the Classroom
 • Bing Maps
 • Bing Search APIs/SDKs
 • Bing Search app
 • Bing Sportscaster
 • Bing Toolbar
 • Bing Translator
 • Bing Webmaster
 • Bing Wikipedia Browser
 • Bing.com
 • Bingplaces.com
 • Citizen Next
 • Cortana
 • Cortana skills by Microsoft
 • Default Homepage and New Tab Page on Microsoft Edge
 • Dev Center App
 • Device Health App
 • Dictate
 • Docs.com
 • education.minecraft.net
 • Face Swap
 • Feedback Intake Tool for Azure Maps (aka “Azure Maps Feedback”)
 • Forms.microsoft.com
 • forzamotorsport.net
 • Groove
 • Groove Music Pass
 • GroupMe
 • HealthVault
 • LineBack
 • Maps App
 • Microsoft Academic
 • Microsoft account
 • Microsoft Add-Ins for Skype
 • Microsoft Bots
 • Microsoft Educator Community
 • Microsoft Family
 • Microsoft Health
 • Microsoft Pay
 • Microsoft Research Interactive Science
 • Microsoft Research Open Data
 • Microsoft Soundscape
 • Microsoft Translator
 • Microsoft Wallpaper
 • Microsoft XiaoIce
 • Microsoft ፊልሞችና ቲቪ
 • Mixer
 • MSN Dial Up
 • MSN Explorer
 • MSN Food & Drink
 • MSN Health & Fitness
 • MSN Money
 • MSN News
 • MSN Premium
 • MSN Sports
 • MSN Travel
 • MSN Weather
 • MSN.com
 • Next Lock Screen
 • Office 365 Consumer
 • Office 365 Home
 • Office 365 Personal
 • Office 365 University
 • Office Online
 • Office Store
 • Office Sway
 • Office.com
 • OneDrive
 • OneDrive.com
 • OneNote.com
 • Outlook.com
 • Paint 3D
 • Picturesque Lock Screen
 • Presentation Translator
 • Remix 3D
 • Rinna
 • rise4fun
 • Ruuh
 • Seeing AI
 • Send
 • Skype
 • Skype in the Classroom
 • Skype Interviews
 • Skype Manager
 • Skype Qik
 • Skype.com
 • Smart Search
 • Snip Insights
 • Spreadsheet Keyboard
 • Sprinkles
 • Sway.com
 • to-do.microsoft.com
 • Translator for Microsoft Edge
 • Translator Live
 • UrWeather
 • Video Breakdown
 • Visio Online
 • Web Translator
 • Who’s In
 • Windows Live Mail
 • Windows Live Writer
 • Windows Movie Maker
 • Windows Photo Gallery
 • Windows ማከማቻ
 • Xbox Game Pass
 • Xbox Game Studios ማጫወቻዎች መተግበሪዎችና ድረ-ገጾች
 • Xbox Live
 • Xbox Live Gold
 • Xbox Music
 • Xbox Store
 • ማከማቻ
 • በ Microsoft የታተሙ Windows ማጫወቻዎች፣ መተግበሪያዎች እና ድረ-ገጾች
 • የMicrosoft ድጋፍ እና የመልሶ ማግኘት ረዳት ለOffice 365
ሙሉ ጽሁፍ
ማርች 1፣ 20180