የ MICROSOFT የሽያጭስርዓቶችበ የካቲት 2017 ተሻሻለ

እንኳን ወደ Microsoft የመስመር ላይ እና የችርቻሮ ማከማቻዎች በደህና መጡ፡፡ “ማከማቻ” የሚለው ቃል ለመዳሰስ፣ ለማየት፣ ለማግኘት፣ ለመግዛትና ደረጃ ለመስጠት እና መሳሪያዎችን፣ የጨዋታ ኮንሰሎችን፣ ዲጂታላዊ በይዘትን፣ መተግበሪያዎችን፣ ጨዋታዎችን፣ አገልግሎቶችንና ሌሎችን ጨምሮ ምርቶችንና አገልግሎትችን ለማየት የሚስችልዎ የእኛ የመስመር ላይ እና የችርቻሮ መደብሮችን ያመለክታል፡፡ እነዚህ የሽያጭ ስርዓቶች በዚህ ውስጥ (“የሽያጭ ስርዓቶች”) እየተባሉ የሚጠቀሱት የMicrosoft ማከማቻ፣ የOffice ማከማቻ ፣ የXbox ማከማቻ ፣ የWindows ማከማቻ አጠቃቀምን እና ከዚህ የሽያጭ ስርዓቶች (በጥቅሉ “ማከማቻ”) ጋር ተያያዥ) የሆኑ ሌሎች የMicrosoft አገልግሎቶች አጠቃቀምን ይመለከታሉ፡፡ በማከማቻ በኩል፣ Microsoft የማውረድ አካባቢዎች፣ ሶፍትዌር፣ መሳሪያዎችና፤ ስለሶፍትዌር፣ አገልግሎቶች እና ሌሎች ሸቀጦች (በጥቅሉ ስለ “አገልግሎቶች” እና ከማከማቻ ጋር፤ “ማከማቻ”) መረጃ ያካተተ ወደ ተለያዩ ግብዓቶች መዳረሻ ያቀርባል። በማከማቻው የቀረቡ አብዛኛዎቹ ምርቶች፣ አገልግሎቶች እና ይዘቶች ከ Microsoft ውጪ በሆኑ በሌሎች ተቋማት የቀረቡ የሶስተኛ ወገን ምርቶች ናቸው፡፡ ማከማቻውንበመጠቀምምወይምምርቶችናአገልግሎቶችንከማከማቻበመግዛትዎብቻይህንየሽያጭስርዓቶች፣የMicrosoft የግላዊነትመግለጫጥበቃደንብ (ከዚህበታችያለውንየግላዊነትእናየግልመረጃጥበቃክፍልይመልከቱ) እናአግባብነትያላቸውንውሎችናሁኔታዎች፣በማከማቻውስጥያሉወይምበነዚህየሽያጭስርዓቶች (በጥቅሉየ “ማከማቻፖሊሲዎች”) ውስጥየተጠቀሱፖሊሲዎችንወይምኃላፊነትያለመውሰድመግለጫዎችንተቀብለውተስማምተውበታልማለትነው፡፡የማከማቻ ፖሊሲዎችን በጥንቃቄ እንዲያነቡ እናበረታታዎታለን፡፡ በማከማቻ ፖሊሲዎች ካልተስማሙ ማከማቻውን ወይም አገልግሎቶችን ላይጠቀሙ ይችላሉ፡፡

በእናንተ ሀገር ወይም ክልል ውስጥ የሚገኝ አንድ የMicrosoft የችርቻሮ ማከማቻ ቢኖረን ኖሮ፣ ከዚህ የተለዩ ወይም ተጨማሪ ፖሊሲዎች ሊኖሩት ይችል ነበር፡፡ Microsoft በማናቸውም ጊዜ ምንም ዓይነት ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልገው ማናቸውንም ፖሊሲዎችን ሊያሻሻል ወይም ሊለውጥ ይችላል፡፡

ከእርስዎማከማቻአጠቃቀምጋርየተያያዙስምምነቶች

1. የአባል መለያ፡፡ ማከማቻው የራስዎን መለያ እንዲከፍቱ የሚፈለግ ከሆነ፣ አግባብነት ባለው የምዝገባ ቅፅ የሚፈለገውን የእርስዎን ወቅታዊ፣ የተሟላ እና ትክክለኛ መረጃ ለእኛ በመስጠት የምዝገባ ሂደቱን ማጠናቀቅ አለብዎት፡፡ በተጨማሪም መለያውን ለመክፈት እንደ አንድ ቅድመ ሁኔታ የአግልግሎት ስምምነት ወይም የተለዩ የአጠቃቀም ስምምነቶችን መቀበል ሊኖርብዎት ይችላል፡፡ ከማከማቻው ያገኙት ይዘት እና ማከማቻውን ለመጠቀም የእርስዎ የመለያ አጠቃቀም፤ የMicrosoft መለያ አጠቃቀም ላይ ገዢ ለሆኑ ለሁሉም ስምምነቶች ተገዢ ይሆናሉ፡፡ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎንየ Microsoft አገልግሎት ስምምነት ይመልከቱ:: የመለያዎን መረጃና የይለፍ ቃል በሚስጥር የመያዝ እና በእርስዎ መለያ ውስጥ ለሚደረጉ ነገሮች በሙሉ ኃላፊነት አለብዎት፡፡

2. ህገወጥወይምየተከለከለአጠቃቀምአይፈቀድም፡፡ እርስዎ ማከማቻውን እና አገልግሎቶችን ለመጠቀምዎ አንድአንድ ቅድመ ሁኔታ፣ ማከማቻውን ለማናቸውም ህገወጥ ተግባር ወይም በነዚህ የሽያጭ ስርዓቶች፣ በማከማቻ ፖሊሲዎች ወይም በርስዎ የማከማቻ አጠቃቀም ላይ ተፈፃሚ በሆኑ በማናቸውም ሌሎች ስምምነቶች ውስጥ ለተከለከሉ ተግባራት የማይጠቀሙበት መሆኑን ማረጋገጫ ወይም ዋስትና ይሰጡናል፡፡ ማከማቻውን ማናቸውንም የ Microsoft አገልጋይ ወይም ከማናቸውም የ Microsoft አገልጋይ ጋር የተያያዘ ኔትወርክ(ኮች) ቢጎዳ፣ እንዳይሰራ በሚያደርግ፣ በሚያጨናንቅ ወይም በሚያበላሽ ወይም በሌላ ወገን ማከማቻ አጠቃቀም ላይ ጣልቃ በሚገባ ሁኔታ መጠቀም ላይችሉ ይችላሉ፡፡ ሰብሮ በመግባት፣ የይለፍ ቃል በማስገባት ወይም በሌላ በማናቸውም ዘዴ ባልተፈቀደ ሁኔታ ማከማቻውን፣ ሌሎች መለያዎች፣ የኮምፒዩተር ሲስተሞችን ወይም ከማናቸውም የ Microsoft ሰርቨር ወይም ከማከማቻው ጋር የተያየዙ ኔትወርኮችን ለመጠቀን አይሞክሩም፡፡ ሆን ተብሎ በማከማቻው ወይም መደብሩ በኩል ባልተሰጡ ለማናቸውም ዘዴዎች ማናቸውንም ሰነዶች ወይም መረጃዎች አያገኙም ወይም ለማግኘት አይሞክሩም፡፡ Microsoftን ጨምሮ ማናቸውንም ሰው ወይም ተቋም ሆን ብሎ መጉዳትን ጨምሮ ማከማቻውን የሶስተኛ ወገኖችን መብቶች ሊጎዳ በሚችል በማናቸውም መልኩ አይጠቀሙም፡፡ ከማከማቻው የተገኙ ማናቸውንም ምርቶች፣ መረጃዎች ወይም አገልግሎቶች የንግድ ጥቅም በሚያስገኝ መልኩ አያሰራጩም፣ አያትሙም፣ ፈቃድ አይሰጡም ወይም አይሸጡም፡፡

3. ለ Microsoft የሰጡትወይምማከማቻላይየለጠፉዋቸውመረጃዎች፡፡ (ምላሾችን፣ ደረጃዎችን፣ ማሻሻያዎችንና አስተያየቶችን ጨምሮ) ለ Microsoft በሰጧቸው ወይም ለማከማቻ ወይም ተያያዡ ለሆኑ የ Microsoft አገልግሎቶች በሌሎች እንዲታዩ በለጠፏቸው፣ አፕሎድ ባደረጓቸው ወይም ባቀረቧቸው መረጃዎች ላይ Microsoft የባለቤትነት ጥያቄ አያቀርብም (እያንዳንዳቸው በተናጠል “የቀረበ” ሲባል በጥቅሉ “የቀረቡ” ይባላሉ)፡፡ ይሁን እንጂ Microsoft በማናቸውም ማደያ የእርስዎን ስም ጨምሮ እርስዎ ያቀረቡትን ወይም የለጠፉትን መረጃ ከክፍያ ነፃ፣ ቀጣይነት ያለው፣ የማይሽር፣ ዓለም አቀፋዊ፣ አጠቃላይነት ያለው ለሌላ ወገን መተላለፍ የሚችል ፅሑፉን የመጠቀም፣ የማሻሻል የማዘጋጀት፣ የፈጠራ ስራዎችን የመስራት፣ የመተርጎም፣ የማረም፣ የመከወን፣ የማሰራጨት እና የማሳየት ፈቃድ ሰጥተውታል፡፡ ማከማቻ ኦንላይን ያለምንም ገደብ በስፋት በሚታይበት ቦታ ፅሁፍዎን ወይ ያቀረቡትን መረጃ ካተሙት፣ ማከማቻውን እና/ወይም ምርቶቹን፣ አገልግሎቶችን እና በማከማቻ የቀረበ ይዘትን በሚያስተዋውቁ ማሳያዎች ወይም መረጃዎች ውስጥ የእርስዎንም መረጃ አብሮ ሊቀርብ ይችላል፡፡ ላቀረቡት ለማናቸውም መረጃ አስፈላጊ የሆኑ መብቶች ሁሉ ስላሉህ (እና ወደፊትም የሚኖሩ መሆኑን እና እነዚህን መብቶች ለ Microsoft የሚሰጡ መሆኑን በማረጋገጥ ዋስትና ሰጥተዋል፡፡

የእርስዎን ፈቃድ ከመጠቀም ጋር በተያያዘ የሚከፈል ካሳ የለም፡፡ Microsoft ማናቸውንም የቀረበ ፅሁፍ የመለጠፍ ወይም የመጠቀም ግዴታ የሌለበት ሲሆን Microsoft ማናቸውንም የቀረበ ፅሁፍ ወይም መረጃ በማናቸውም ጊዜ በራሱ የመወሰን ስልጣን ሊያነሳ ወይም ሊሰርዝ ይችላል፡፡ ማከማቻውን በመጠቀም እርስዎ ላቀረቧቸው ወይም ሌሎች የሰቀሉዋቸው ወይም ላቀርቧቸው መረጃዎች Microsoft የሚወስደው ኃላፊነት ወይም የሚኖርበት ተጠያቂነት አይኖርም።

ማከማቻ ውስጥ አንድ መተግበሪያ ደረጃ የሚያወጡለት ወይም የሚገመግሙ ከሆነ ከመተግበሪያው አታሚ ይዘቱን የያዘ የኢሜይል መልዕክት ከ Microsoft ሊደርስዎ ይችላል፡፡

4. የሶስተኛወገንድረገፆችአገናኞች። ማከማቻው፤ ከማከማቻ እንዲወጡ የሚደርግዎ የሶስተኛ ወገኖች ድረገፆች ሊንኮችን ጨምሮ ሊያካትት ይችላል፡፡ እነዚህን የተያያዙ ገጾች በ Microsoft ቁጥጥር ስር ያልሆኑ ሲሆን ለማናቸውም የተያያዘ ገፅ ይዘቶች ወይም በተያያዘው ገፅ ላይ ላለ ለማናቸውም ሊንክ ይዘቶች Microsoft ኃላፊነት የለበትም፡፡ Microsoft እነዚህን ሊንኮች ለእርስዎ የሚሰጥዎ ለአጠቃቀም ቅለት እና ምቾት ብቻ ሲሆን የማናቸውም ሊንክ መካተት በገፁ Microsoft የተረጋገጠ መሆኑን አያመለክትም፡፡ የእርስዎ የሶስተኛ ወገን ድረ ገፅ አጠቃቀም በሶስተኛ ወገኑ ውሎችና ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ይሆናል፡፡

ምርቶችንናአገልግሎቶችንለእርስዎከመሸጥጋርየተያያዙስምምነቶች

5. መልከዓ ምድራዊ አቅራቦት፡፡ የሚገኙ ምርቶችና አገልግሎቶች እርስዎ ባሉበት ክልል ወይም በሚጠቀሙት መሳሪያ ላይ በመመስረት ሊለዋወጥ ይችላል፡፡ በተጨማሪም ከዚህ በታች ባሉት በማስጫኛ ፖሊሲዎቻችን ውስጥ በተገለጸው መሰረት ምርቶችን ልንጭን የምንችልበትን ቦታ በተመለከተ ገደቦች ሊኖሩብን ይችላሉ፡፡ ግዢዎን ለማጠናቀቅ፣ ግዢውን በሚፈፅሙበት ማከማቻ በሚገኝበት ሀገር ወይም ክልል ውስጥ ትክክለኛ የክፍያ እና የማስጫኛ አድራሻ ሊኖርዎ ይችላል፡፡

6. የመጨረሻ ተጠቃሚዎች ብቻ፡፡ ምርቶችንና አገልግሎቶችን ከማከማቻ ለመግዛት እርስዎ የመጨረሻ ተጠቃሚ መሆን አለብዎ፡፡ መልሶ ሻጮች ለግዢው ብቁ አይደሉም፡፡

7. የውጪ መላኪያ ገደቦች፡፡ ከማከማቻ የተገዙ ምርቶችና አገልግሎቶች የጉምሩክ እና የውጪ ንግድ ቁጥጥር ህጎችና መመሪያዎች ተፈፃሚ ደረግባቸዋል፡፡ ተፈፃሚ የሆኑ አለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ህጎችና መመሪያዎችን ለማክበር ተስማምተዋል፡፡

8. ክፍያ፡፡ ለ Microsoft የክፍያ ዘዴ በመስጠት፤ (i) የሰጡትን የክፍያ ዘዴ ለመጠቀም የተፈቀደልዎ መሆኑን እና ማናቸውም የሰጡት የክፍያ መረጃ እውነተኛና ትክክለኛ መሆኑን አረጋግጠናል፤ (ii) ያቀረቡትን የክፍያ ዘዴ በመጠቀም ለገዟቸው ለማናቸውም ምርቶች፣ አገልግሎቶች ወይም ሊገኙ ለሚችሉ ይዘቶች Microsoft ክፍያ እንዲያስከፍልዎ የፈቀዱለት መሆኑን እና (iii) ለመመዝገብ እና ለማድረግ ወይም ለመጠቀም ለመረጡት ለማናቸውም የተከፈለበት የማከማቻ ፊቸር ክፍያ እንዲያስከፍልዎ ለ Microsoft የፈቀዱለት መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ ኢሜይል አድራሻዎን እና የክሬዲት ካርድ ቁጥርዎን እና የሚያበቃበትን ቀን ጨምሮ መለያዎን እና ሌሎች መረጃዎችዎን በፍጥነት ወቅታዊ ለማድረግ ተስማምተዋል፣ በዚህም የእርስዎን ግዢ በፍጥነት አጠናቀን ከግዢዎ ጋር በተያያዘ በሚያስፈልገው ሁኔታ እናገኝዎታለን፡፡ ክፍያውን፣ (ሀ) በቅድሚያ፤ (ለ) ግዢው በሚፈፀምበት ወቅት፣ (ሐ) ግዢው ከተፈጸመ በኋላ ወድያው ወይም (መ) ለሰብስክሪብሽኖች ቀጣይነት ወይም ተደጋጋሚ ባለው ሁኔታ ልናስከፍልዎእንችላን፡፡ በተጨማሪም እርስዎ እስከፈቀዱት የገንዘብ መጠን ድረስ ልናስከፍልዎ የምንችል ሲሆን በየጊዜው ለሚደረጉ ሰብስክሪብሽኖች በሚፈፀመው የክፍያ መጠን ላይ ማናቸውም ለውጥ ሲኖር በቅድሚያ እና በግዢ ስምምነትዎ መሰረት አስቀድመን እናሳውቆታለን፡፡ ቀደም ሲል ጉዳያቸው ላልተጠናቀቀላቸው የገንዘብ መጠኖች ከቀድሞ ከአንድ በላይ ክፍያዎችን በአንድ ጊዜ ልናስከፍልዎ እንችላለን፡፡ ከዚህ በታች ያለውን የአውቶማቲክ ሪኒዋል የሚለውን ክፍል ይመልከቱ፡፡

በማናቸውም የሙከራ ጊዜ አቅርቦት ውስጥ የሚሳተፉ ከሆነ፣ ከዚህ የተለየ ካላሳወቅንዎ በስተቀር፣ ተደጋጋሚ የሆኑ አዳዲስ ክፍያዎችን ለማስወገድ አገልግሎቱን በሙከራ ጊዜው ማብቂያ ላይ መሰረዝ አለብዎ፡፡ አገልግሎቱን ከሙከራ ጊዜው ማብቂያ ላይ ካልሰረዙት ለምርቱ ወይም ለአግልሎቱ በመረጡ የክፍያ ዘዴ እንድናስከፍልዎ ፈቅደንልዎታል ማለት ነው፡፡

9. ተደጋጋሚ ክፍያዎች፡፡ ምርቶችን፣ አገልግሎቶችን ወይም አንድን ይዘት በሰብስክሪብሽን መልኩ (ለምሳሌ በሳምንታዊ፣ ወርኃዊ፣ በየ3ወሩ ወይም በየዓመቱ (እንደአግባብነቱ)) የሚገዙ ከሆነ፣ ተደጋጋሚነት ያለውን ክፍያ አውቀው ተስማተውበታል ማለት ሲሆን ሰብስክሪብሽኑ በእርስዎ ወይም በ Microsoft ወይም በስምምነቱ መሰረት እስከሚሰረዝ ድረስ ክፍያዎቹ እርስዎ በመረጡት የክፍያ ዘዴና በየክፍያዎቹ ጊዜ ለ Microsoft ይከፈላሉ፡፡ ተደጋጋሚ ክፍያዎችን በመፍቀድዎ Microsoft እነዚህን ክፍያዎች በኤልክትሮኒክ ዴቢት ወይም በገንዘብ ማስተላለፍ ወይምእርስዎ ከሰጠጡት ሂሳብ በኤሌክትሮኒክ ድራፍት መልኩ (ለአውቶሜትድ ክሊሪንግ ሀውስ ወይም መሰል ክፍያዎች)፣ ወይም የመረጡት ሂሳብ ክፍያ (ለክሬዲት ካርድ ወይም መሰል ክፍያዎችን) (በጥቅሉ“በኤሌክትሮኒስ ክፍያዎች”) ማይክሮሶፍት ክፍያውን ፕሮሰስ እንዲያደርግ ፈቅደዋል ማለት ነው፡፡ ሰብስክሪብሽን ክፍያዎች በአጠቃላይ ተፈፃሚ ከሆነው የሰብስክሪብሽን ጊዜ በፊት በቅድሚያ የሚከፈሉ ናቸው፡፡ ማናቸውም ክፍያዎች ሳይከፈሉ ተመላሽ ከተደረጉ ወይም ማናቸውም ክሬዲት ከተደረጉ ወይም ማናቸውም ክሬዲት ካርዱ ወይም ተመሳሳይ ግዢ ውድቅ ከተደረገ ወይም የተከለከለ ከሆነ፣ Microsoft ወይም አገልግሎት ሰጪዎቹ ማናቸውንም አግባብነት ያለውን ተመላሽ እቃ፣ ውድቅ የተደረገ ነገር ወይም ሌሎች ክፍያዎችን በስራ ላይ ባለው ህግ በተፈቀደው መሰረት የመቀጠል መብት አላቸው፡፡

10. የምርት መገኘት እና ብዛት እና የትዕዛዝ ገደቦች፡፡ የምርት ዋጋዎች እና መገኘት መቻል በማናቸውም ጊዜ ያለምንም ማስጠንቀቂያ በሚፈፀም ክፍያ ላይ የተመሰረቱ ናቸው፡፡ Microsoft በአንድ ማዘዣ፣ በአንድ መለያ፣ በክሬዲት፣ በሰው ወይም በቤተሰብ ሊገዛ የሚችለውን ብዛት በተመለከተ ገደብ ሊያስቀምጥ ይችላል፡፡ ያዘዟቸውን ምርቶች ወይም አገልግሎቶች ሊያገኙ የማይችሉ ከሆነ፣ አማራጭ ምርት ለማቅረብ ለእርስዎ ጋር ግንኙነት ልናደርግ እንችላለን፡፡ አማራጩን ምርት ለመግዛት ካልመረጡ፣ ትዕዛዝዎን እንሰርዘዋለን፡፡

በዚህ ብቻ የተወሰኑ ባይሆኑም ትእዛዙን ባቀረቡበት ጊዜ የተገለፀልዎትን ሁኔታዎች አለሟሟላትዎ፣ ክፍያው ፕሮሰስ አለመደረጉን፣ የታዘዙት ምርቶች ወይም አገልግሎቶች አለመኖራቸውን ወይም የዋጋ ወይም ሌሎች ስህተቶችን ጨምሮ በማናቸውም ምክንያት Microsoft ለእርስዎ ለማዘዣው የከፈሏቸውን ገንዘቦች ተመላሽ በማድረግ በማናቸውም ጊዜ የቀረበለትን የግዢ ማዘዣ ውድቅ ሊያደርግ ወይም ላይቀበል ይችላል፡፡ የዋጋ ወይም ሌላ ስህተት በሚኖርበት ጊዜ፣ በራሳችን የመወሰን ስልጣን ወይም (ሀ) የእርስዎን ማዛዣ ወይም ግዢ ልንሰርዝ ወይም (ለ) ከእርስዎ መመሪያ ለማግኘት ከእርስዎ ጋር ግንኙነት የማድረግ መብት አለን፡፡ ማዘዣውን በሚሰረዝበት ጊዜ፣ ተያያዥ የሆነውን ይዘት ማግኘት የማይችሉ ይሆናል፡፡

በማናቸውም ምክንያት ከእርስዎ አካውንት ጋር ተያያዥ የሆነውን ይዘት ማግኘት እንዳይችል ልናደርግ እንችላለን፡፡ ማከማቻን ወይም ሊጎዱ የሚችሉ ወገኖች ለመጠበቅ ስንል በእርስዎ መሳሪያ ላይ ያሉ ጌሞችን፣ መተግበሪያዎች፣ ይዘቶች ወይም አገልግሎቶች ልናጠፋቸው ወይም እንዳይሰሩ ልናደርጋቸው እንችላለን፡፡ አንዳንድ ይዘቶች እና መተግበሪያዎች በየጊዜው ላይገኙ ወይም ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡ የነገሮች መገኘት መቻልበክልል ምክንያት ችግር ሊገጥመው ይችላል፡፡ በመሆኑም መለያዎን ወይም መሳሪያዎን ወደ ሌላ ክልል የሚለውጡ ከሆነ ይዘቶችን ወይም መተግበሪያዎችን መልሰው ዳውንሎድ ማድረግ ላይችሉ ወይም የገዙትን የተወሰነ ይዘት መልሰው ላይጠቀሙ ወይም ላያዩይችላሉ፣ ቀደም ሲል በነበሩበት ክልል ከፍለውበት የነበረን ይዘት ወይም መተግበሪያ መልሰው መግዛት ሊኖርብዎ ይችላል፡፡ አግባብነት ባለው ህግ ከሚፈለገው ደረጃ ውጭ፤ የማናቸውንም እርስዎ የገዙትን ይዘት ወይም መተግበሪያ ዳግም ዳውንሎድ ወይም ምትክ የመስጠት ግዴታ የለብንም፡፡

11. ወቅታዊ መረጃዎች፡፡ አግባብነት ያለው ከሆነ ወደ ማከማቻ ያልገቡ ቢሆንም፤Microsoft ለእርስዎ መተግበሪያዎችን አጠናቆ ወቅታዊ መረጃዎችን ዳውንሎድ ያደርጋል፡፡ በማከማቻ መተግበሪያዎች አውቶማቲክ አፕዴትስ ላለመቀበል ከመረጡ፤ መቼትዎን መቀየር ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጂ የተወሰኑ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል አገልግሎት ላይ ሆስት ያልተደረጉ የOffice ማከማቻ መተግበሪያዎች በመተግበሪያው ደቨሎፕና በማናቸውም ጊዜ ወቅታዊ ሊደረጉ የሚችሉ ሲሆን እነዚህን ወቅታዊ ለማድረግ የእርስዎ ፈቃድ ላያስፈልግ ይችላል፡፡

12. የሶፍትዌር ፈቃድ እና የመጠቀም መብቶች፡፡ በማከማቻ በኩል የቀረበ ሶፍትዌር እና ሌላ ዲጂታላዊ ይዘት ተፈቅዶልሃል አልተሸጠለህም፡፡ በቀጥታ ከማከማቻ ዳውንሎድ የተደረጉ መተግበሪያዎችን የተለየ የፈቃድ ስምምነት ከመተግበሪያው ጋር ካልቀረበ በስተቀር መደበኛው የመተግበሪያ ፈቃድ ስምምነቶች (“ስልት” https://go.microsoft.com/fwlink/p/?linkid=838610&clcid=0x045e) በሊንክ ላይ ይገኛል ተፈፃሚ ይደረግባቸዋል፡፡ (ከOffice ማከማቻ ዳውንሎድ የተደረጉ መተግበሪያዎች ለሳልት ተገዢ የማይሆኑ ሲሆን የተለየ የፈቃድ ስምምነት አላቸው፡፡) ከማከማቻየተገኙ መተግበሪያዎች፣ ጌሞች እና ሌሎች ዲጂታል ይዘቶች በ https://go.microsoft.com/fwlink/p/?LinkId=723143 በሚገኘው ሕጎች ስር ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል፡፡ ከእነዚህ ዲጂታል ዕቃዎች አኳያ ያልዎት መብቶች በእነዚህ ከላይ በተጠቀሱት የሽያጭ ስርዓቶች፣ የቅጂ መብት ህግ እና የአጠቃቀም ህጎች እንደተወሰኑ ተረድተው ዕውቅና ሰጥተዋል፡፡ ከ Microsoft የችርቻሮ ማከማቻ የተገዙ የሶፍትዌር ፍቃዶች፤ ሶፍትዌሩን ለሚያግዙ የፈቃድ ስምምነቶች ተገዢ ሲሆኑ፤ ሶፍትዌሩን ሲጭኑ ከፍቃድ ስምምነቱ ጋር እንዲስማሙ ይጠየቃሉ፡፡ አግባብነት ካላቸው ከፈቃድ ውሎች፣ የአጠቃቀም ህጎች፣ እና ተግባራዊ ህጎች ውጭ የሆነ የትኛውም የሶፍትዌሩ መልሶ ማማረትና ማሰራጨት ወይም ሽያጭ በጥብቅ የተከለከለ ሲሆን ከባድ የሆነ የሲቪል እና የወንጀለኛ ቅጣቶችን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ህግ ተላላፊዎች የሕጉ እስከ መጨረሻ ቅጣት ድረስ ተጋላጭ ናቸው::

(ከታች በማስታወቂያዎች እና በግንኙነት ክፍል እንደተገለፀው) ፤ ያለ ምንም ወጪ ምንም የሶፍትዌር እሽግ ሳይከፍቱለሳጥን ሶፍተዌር የሚተገበረውን የፍቃድ ስምምነት ቅጂ ከፈለጉ፤እባክዎ የ MICROSOFT የችርቻሮ ማከማቻን ያግኙ፡፡

ሌሎች ውሎችና ሁኔታዎች፡፡ ከሶፍትዌር እና ከሌሎች ዳውንሎድ መደረግ ከሚችሉ ምርቶች በተጨማሪ ማከማቻ ውስጥ ለግዢ ወይም ለሙከራ ሊገኙ የሚችሉ ሌሎች ምርቶችና አገልግሎቶች በተለየ የመጨረሻ ተጠቃሚ የፈቃድ ስምምነቶች የአጠቃቀም ስምምነቶች፣ የአገልግሎት ስምምነቶች ወይም በሌሎች ውሎችና ሁኔታዎች መሰረት ሊቀርብልዎ ይችላሉ፡፡ እነዚህን ምርቶች ከገዙ ወይም የሚጠቀሙ ከሆነ፣ የግዢው፣ የኢንስታሌሽኑ ወይም የአጠቃቀሙ እንደ ቅድመ ሁኔታ ሆኖ እነዚህን ስምምነቶች መቀበልም ሊኖርብዎ ይችላል፡፡

ለእርስዎ ምቾት ስንል MICROSOFT የማከማቻ ወይም የአገልግሎቶቹ አንድ አካል አድርጎ ወይም በሶፍትዌሩ ወይም በሸቀጡ ውስጥ የተሸጠን ምርት ወይም አገልግሎት አባል ያልሆኑ ቱሎችንና ዩቲሊቲዎችን እንድንጠቀሙባቸው እና/ወይም ዳውንሎድ እንድያደርጓቸው ሊያቀርብልዎት ይችላል፡፡ አግባብነት ባለው ህግ እስከሚፈቀደው ደረጃ ድረስ፣ ከነዚህ ከማናቸውም ቱሎች ወይም ዩቲሊቲዎች የሚገኙትን ውጤቶች ትክክለኛነት በተመለከተ MICROSOFT ማናቸውንም ማረጋገጫ ወይም ዋስትና አይሰጥም፡፡

በማከማቻ በኩል የተገኙ ወይም በሶፍትዌር ወይም ሸቀጥ ውስጥ ያሉ ቱሎችንና ዩቲሊቲዎችን በሚጠቀሙ ጊዜ እባክዎ የሌሎችን የአእምሯዊ ንብረት መብት ያክበሩ፡፡

13. የሶፍትዌር እና የይዘት ዳውንሎዶች ደንቦች፡፡ ከግዢዎ ጋር በ Microsoft መለያዎ የዳውንሎድ ሊንክ ለእርስዎ በማቅረብ አንዳንድ ሶፍትዌሮች እና ይዘቶች ተሰጥቶዎታል፡፡ ከታች ባለው አንቀፅ ስር፤ በ Microsoft መለያዎ፤ ከግዢውቀን 3 ዓመታት ውስጥ የእነዚህ ግዢዎች የዳውንሎድ ሊንክ እና ዲጂታል ቁልፉን አብዛኛውን ጊዜ እናከማቻለን፤ ነገር ግን ለየትኛውም የተወሰነ ጊዜ እንደምናከማች ቃል አንገባም፡፡ የዳውንሎድ ሊንክ በመስጠት ሰብስክሪብሽን ምርቶችን ለማግኘት፤ የተለያዩ ስምምነቶች እና የማከማቻ መብቶች ሊፈቀዱ ይችላሉ፤ ይህም በሰብስክሪፕሽን ወቅት የሚያይዋቸው እና የሚስማሙባቸው ናቸው፡፡

በማናቸውም ጊዜ የእኛን የዲጂታል ቁልፍ ልንሰርዝ ወይም ልናሻሽል የምንችል መሆኑን ተስማምተውበታል፡፡ በተጨማሪም፤ ለአንድ ወይም ከዚያ በላይ በየትኛውም ጊዜ እና በየትኛውም ምክንያት፤ ለምሳሌ የዳውንሎድ ሊንክ ወይም የዲጂታ ቁልፉ መጠቀሚያ ፍቃድዎ በማይኖርበት የምርቱ ድጋፍ የአገልሎት ማብቂያ ጊዜን ጨምሮ የምርት ውጤቶች ቁልፎችን የማከማቸት ድጋፍ ልናቆም የምንችል መሆኑን ተስማምተዋል፡፡ በፕሮግራማችን ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ በማድረጋችን ምክንያት አካውንትዎን መጠቀም የማይችሉ ከሆነ፤ አግባብነት ያለውን የ Microsoft አካውንት መረጃ ተጠቅመው የ 90 ቀናት ማስጠንቀቂያ መስጠት ይችላሉ፡፡

14. ዋጋ፡፡ በሀገርዎ ወይም በክልልዎ ውስጥ የ Microsoft የችርቻሮ ማከማቻ ካለን፣ በዚያ የሚሰጡት ዋጋዎች፣ የምርት ምርጫ እና ማስታወቂያዎች ኦንላይን ማከማቻ ላይ ከሚሰጡት የተለዩ ከሆኑ ይችላሉ፡፡ ተፈፃሚነት ባለው ህግ እስከሚፈቅደው ደረጃ ድረስ፤ ኦንላይን የቀረበው ዋጋ፣ ምርት ወይም ማስታወቂያ በ Microsoft የችርቻሮ ማከማቻ እንደሚጠበቅ ወይም እንደሚከበር ወይም ግልባጩ እንደሚሆን Microsoft ዋስትና አይሰጥም፡፡

ማከማቻው የዋጋ ተመሳስሎ ዋስትና የለውም፡፡ ለተመሳሳይ ዕቃ ሌሎች ችርቻሮዎችን ያስተዋውቁንን ዋጋ አናዛምድም፡፡

አንዳንድ ምርቶች ሊገኙ ከሚችሉበት ቀን በፊት በቅድሚያ እንዲታዘዙ አማራጭ ልንሰጥ እንችላለን፡፡ ስለ ቅድመ ትዕዛዝ ፖሊሲዎችን የበለጠ ለማወቅ፣ እባክዎ የእኛን ቅድመ ማዘዣ ገጽ https://go.microsoft.com/fwlink/p/?linkid=834935&clcid=0x045e ተመልከት፡፡

ከዚህ የተለየ ካልተገለፁ በስተቀር፣ በማከማቻ ውስጥ የታዩ ዋጋዎችበእርስዎ ግዢ ላይ ተፈፃሚ ሊደረጉ ከሚችሉ ግብሮችን ወይም ክፍያዎችን (“ግብሮች”) ያካተቱ አይደሉም፡፡ በማከማቻ ውስጥ የታዩ ዋጋዎች የማስረከቢያ ወጪዎችንም ያካተቱ አይደሉም፡፡ ግብሮችና የማስረከቢያ ወጪዎች (እንደ አግባብነታቸው)በእርስዎ የግዢ የገንዘብ መጠን ላይ ተደምረው በማውጫ ገጽ ላይ እንዲታዩ ይደረጋል፡፡ እነዚህን ግብሮችና ወጪዎች መክፈል የእርስዎ የብቻ ኃላፊነትዎ ነው፡፡

ባሉበት ቦታ ላይ በመመስረት፣ አንዳንድ ግዢዎች የውጭ ምንዛሪ ለውጥ ሊፈለጉ ይችላሉ ወይም በሌላ ሀገር ውስጥ ፕሮሰስ ሊደረጉ ይችላሉ፡፡ የክሬዲት ወይም ዴቢት ካርድ በሚጠቀሙበትጊዜ ባንክዎ ለእነዚህ አገልግሎቶች ተጨማሪ ክፍያ ሊያስከፍልዎ ይችላል፡፡ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እባክዎ ከባንክዎ ጋር ግንኙነት ያድርጉ፡፡

15. አውቶማቲክ የእድሳት ምርጫ በሀገርዎ፣ በክልልዎ በአውራጃዎ/ግዛትዎ፣ ወይም በክፍለ-ሃገር ውስጥ አውቶማቲክ እድሳት እንደሚፈቀድ በማሰብ፤ በተወሰነ የአገልግሎት ማብቂያ ጊዜ ላይ በአፋጣኝ ማደስ የሚፈልጉትን ምርት ወይም አገልግሎት ሊመርጡ ይችላሉ፡፡ ምርትዎን ወይም አገልግሎትዎን በአውቶቲክ ለማሳደስ ከመረጡ፤ የአሁኑ የአገልግሎት ክፍለ ጊዜ ማብቂያ ላይ በአውቶማቲክ ስናድስ፤ ከታች እንደተገለፀው ምርቱን ወይም አገልግሎቱን ለመሰረዝ ካልመረጡ በስተቀር፤ በዕድሳቱ ጊዜ የአሁን-ጊዜ ዋጋ እናስከፍልዎታለን፡፡ በእድሳቱ ቀን በማሕደር ውስጥ ቢኖርም ወይም ከዚያ በኋላ ቢቀርብም፤ ለእድሳቱ የመረጡትን የክፍያ መንገድ እንጠቀማለን፡፡ ከእድሳቱ ቀን ቀደም ብሎ ምርትዎን ወይም አገልግሎትዎን መሰረዝ ይችላሉ፡፡ ለእድሳቱ ወጪ ማውጣትን ለማስቀረት፤ ከእድሳቱ ቀን ቀደም ብለው መሰረዝ አለብዎት፡፡

16. የመመለስፖሊሲ:: ላልተሟሉ ምርቶች ተመላሾችን እና ልዋጮችን እንደ አግባብነቱ ከግዢው ወይም ከዳውንሎድ ቀን ጀምሮ ለ 14 ቀናት እንቀበላለን፡፡ በቀላሉ ያተሟሉትን ምርቶች በአዲስ ሁኔታ እና በትክክለኛው ማሸጊያ፣ ከነሙሉ ቅያሪዎች፣ ዕቃዎች፣ የአጠቃቀም መመሪያዎች እና በመጀመሪያ ከተካተቱት መዝገቦችጋር ይመልሱ፡፡ ይህ የመመለስ ፖሊሲ ለግዢዎ የሚተገበረውን የሚከበሩ መብቶች ላይ ተፅዕኖ አያመጣም፡፡

የታሸገ ሶፍትዌር እና ጌሞች እንደታሸጉ መመለስ እና ሁሉንም የሚዲያ እና የምርት ቁልፎች ማካተት አለባቸው፡፡ በተወሰነ ደረጃ የተለየ ሆኖ፣ የተከፈቱ የሶፍትዌር እና የጌም እሽጎች፣ በፈቃዱ ስምምነት ካልተስማሙ እና በማናቸውም መልኩ ያልተጠቀምንበት ወይም ያላባዛነው ከሆነ ብቻ በመመለሻ ጊዜያቸው ውስጥ ተመላሽ ሊደረጉ ይችላሉ፡፡

አንዳንድ ዕቃዎች መመለስ የማይችሉ ናቸው፣ በህጉ ወይም በአንዳንድ የተለየ የምርት አቅርቦት ውስጥ ሽያጭ ካልተፈቀደ ወይም ካልተደነገገ በስተቀር የዚህ ዓይነት ምርቶች ግዢዎች በሙሉ የመጨረሻ እና ገንዘባቸው ሊመለስ የማይችል ነው:

ዲጂታል መተግበሪያዎች፣ ጌሞች መተግበሪያዎችን እና የሰብስክራብሽን ይዘት፣ ሙዚቃ፣ ፊልሞች፣ የቲቪ ትርዒቶች እና ተያያዥ ይዘቶች፤

የስጦታ ካርዶች እና የአገልግሎት/ሰብስክሪብሽን ካርዶች (ለምሳሌ፤ Skype፣ Xbox Live፣ Groove Music Pass)፤

ግላዊ የተደረጉ ወይም እንዲዘምኑ የተደረጉ ምርቶች፤

የልዩ ትዕዛዝ ምርቶች፣ በማከማቻ የሽያጭ ማስታወቂያ ውስጥ ያልተካተቱ ከሆነ፤

ራንደም አክሰስ ማኅደረ ትውስታ (“RAM”) ምርቶች፤

የተሰጡ ወይም ጥቅም ላይ የዋሉ አገልግሎቶች፤ እና

ሊያልቁ የደረሱ ዕቃዎች ወይም “የመጨረሻ ሽያጭ” ወይም “ሊመለስ የማይችል” የመሳሰሉ ምክንያቶች የተደረጉባቸው ናቸው፡፡

ዕቃውን በአግባቡ ተመላሽ ሲያደርጉ፣ ሙሉውን የገንዘብ መጠን ሲቀንስ የመጀመሪያውን የማስጫኛ እና የጥበቃ ወይም የሃንድሊንግ ክፍያ (ካለ) የምንመልስ ሲሆን ገንዘቡ ከ 3-5 የሥራ ቀናት ውስጥ ለእርስዎ ይደርሳል፡፡ ማናቸውም ተመላሽ ገንዘቦች (ተመላሽ ለሚደረገው የገንዘብ መጠን የማከማቻ ክሬዲት ካልመረጡ በስተቀር) ማዘዣውን ለማቅረብ የተጠቀሙትን ያንኑ የአከፋፈል ዘዴ በመጠቀም ወዲያውኑ ሂሳብ ገቢ የሚደረግ ይሆናል፡፡

ብቁ የሆኑ ምርቶች ተመላሽ ማድረግ የሚቻልበትን ሁኔታ የተሟላ መረጃ ለማግኘት የእኛን የተመላሽ ዕቃዎችና ተመላሽ ገንዘቦች ገጽ https://go.microsoft.com/fwlink/p/?linkid=723276&clcid=0x045e ይመልከቱ፡፡

ታይዋን ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ፣ በታይዋን የሸማቾች ጥበቃ ህግና አግባብነት ባላቸው ደንቦቹ መሰረት ግዑዝነት በሌለው ቅርጽ እና/ወይም በኦንላይን አገልግሎቶች በኩል የተፈፀሙ ዲጂታላዊ ይዘት ያላቸው ግዢዎች በሙሉ የመጨረሻ እና እነዚህ ይዘቶች ወይም አገልግሎቶች ኦንላይን የተላኩ ከሆነ ተመላሽ ሊደረጉ የማይችሉ መሆናቸውን እባክዎ ልብ ይበሉ፡፡ ማናቸውም የእፎይታ ጊዜ ወይም ተመላሽ ገንዘብ የማግኘት መብት የለዎትም፡፡

17. ለእርስዎየሚከፈሉክፍያዎች፡፡ለእርስዎ የምንከፍለው ገንዘብ ካለ፣ ክፍያውን ለእርስዎ ለመፈፀም የሚያስፈልገውን ማናቸውንም መረጃ በወቅቱ በትክክል ሊሰጡን ተስማተዋል፡፡ ይህ ክፍያ ለእርስዎ በመከፈሉ ምክንያት መከፈል ያለባቸውን ግብሮች እና ክፍያዎች ካሉ ኃላፊነቱ የእርስዎ ነው፡፡ ተፈፃሚነት ባለው ህግ እስከሚፈቅደው ደረጃ ድረስ በእርስዎ ማናቸውም ክፍያ የማግኘት መብትዎ ላይ እኛ ያስቀመጥናቸውን ማናቸውንም ሌሎች ሁኔታዎች ማሟላት አለብዎት፡፡ በስህተት ክፍያ ከፈፀመን፣ ክፍያውን ወደእኛ ልንመልሰው ወይም እንዲመለስ ልንጠይቅዎ እንችላለን፡፡ ይህን ለማድረግ በምናደርገው ጥረትም እርስዎ ሊተባበሩን ተስማምተዋል፡፡ በተጨማሪም ቀደም ሲል በትርፍ ለተከፈልዎት ገንዘብ ማስተካከያ ለማድረግ ማስጠንቀቂያ ስንሰጥ ከክፍያዎ ላይ ተቀናሽ ማድረግ እንችላለን፡፡

18. የሥጦታ ካርዶች፡፡ Microsoft የችርቻሮ ማከማቻዎች የተገዙ የስጦታ ካርዶች በሚከተለው አድራሻ ከሚገኘው የችርቻሮ የስጦታ ካርድ ስምምነት ላይ ማግኘት ይቻላል https://www.microsoftstore.com/store/msusa/html/pbPage.Help_Retail_Stores#GiftCards::

የስካይፒ የስጦታ ካርድ መረጃ በስካይፒ የአግዘኝ ገጽ ላይ ማግኘት ይቻላል

(https://support.skype.com/en/faq/FA12197/what-is-a-skype-gift-card-and-where-can-i-buy-one)::

የድኅነት ወይም የሌላ የ Microsoft የሥጦታ ካርድ አጠቃቀም በሚከተለው ገጽ ላይ ከሚገኘውMicrosoft የስጦታ ውሎችና ሁኔታዎች መሠረትይታያል

(https://commerce.microsoft.com/PaymentHub/Help/Show/toc_link_no_62)::

19. የደንበኛ አገልግሎት፡፡ ስለ ደምበኞች አገልግሎት አማራጮች የበለጠ መረጃ እባክዎ የእኛን https://go.microsoft.com/fwlink/p/?linkid=824761&clcid=0x045e የሽያጭ እና የድጋፍ ገፅ ይጎብኙ፡፡

አጠቃላይስርዓቶች፡፡

20. የሚለወጡ ስርዓቶች፡፡ Microsoft በየትኛውም ጊዜ፤ ያለ ማስታወቂያ የሽያጭ ስርዓቶችን ሊለውጥ ይችላል፡፡ ትዕዛዝዎን በሰጡበት ጊዜ፤ በስራ ላይ ያሉ የሽያጭ ስርዓቶች፤ ግዢዎን የመምራት እና በእኛ መካከል እንደ ግዢ ውል ያገለግላል፡፡ ከሚቀጥለው ግዢዎ ቀደም ብሎ፤ Microsoft የሽያጭ ስርዓቶችን ያለ ምንም ማስታወዊያ ሊቀይረው ይችላል፡፡ ማከማቻውን ባዩጊዜ ሁሉ እባክዎ እነዚህን የሽያጭ ስርዓቶችይመልከቱ፡፡ ግዢ ሲያደርጉ፤ ለወደፊት ማስታወሻ እንዲያመች የሽያጭ ስርዓቶችን ሕግ እንዲያስቀምጡ ወይም ቅጂውን እንዲያትሙ እንመክራለን፡፡

21. የእድሜ ገደብ፡፡ ግዚዎችን ጨምሮ በእርስዎ የማከማቻ አጠቃቀም ላይ የዕድሜ ገደብ ተፈፃሚ ይደረጋሉ፡፡

22. የግላዊነት ምስጢርና የግል መረጃ ጥበቃ፡፡ የእርስዎ ግላዊነት ለእኛ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ማከማቻውን አፕሬት ለማድረግና ለማከማቻ ለመስጠት ከእርስዎ የተቀበልናቸውን የተወሰኑ መረጃዎች እንጠቀማለን፡፡ እባክዎ ከእርስዎ እና ከዕቃዎችዎ (“መረጃ”) የምንሰበስበውን የመረጃ አይነት እና መረጃእንደሆነ፤ እና መረጃዎን እንዴት እንደምንጠቀም ስለሚያብራራ የ Microsoft የግላዊነት መግለጫውን ያንብቡ፡፡ የግላዊነት መግለጫው፤ በተጨማሪምMicrosoft እርስዎ ከሌሎች ጋር ያልዎትን ግንኙነቶች፣ ተለጣፊዎች ወይም በማከማቻ በኩል ለ Microsoft በእርስዎ የተሰጠውን፤ እናመረጃዎች፣ ፎቶዎች፣ መዝገቦች፣ ድምጾች፣ ዲጂታልስራዎችን፣ እናእርስዎየጫኗቸውን፣ ያከማቿቸውን ወይም በዕቃዎ ወይም በማከማቻ በኩል ያከማቿቸውን ቪዲያዎች (“የእርስዎ ይዘት”) እንዴት እንደሚጠቀም ያብራራል፡፡ በግላዊነት መግለጫ መሰረት እርስዎ ማከማቻውን በመጠቀምዎ ብቻ Microsoft ከእርስዎ መለያ ላይ የእርስዎን ይዘት ተጠቅሞ መረጃ እንዲጠቀም በግልጽ ፈቃድዎን ሰጥተዋል ማለት ነው፡፡

23. የምርት ማሳያ እና ቀለሞች፡፡ Microsoft የምርት ቀለሞችን እና ምስሎችን በትክክል ለማሳየት ይሞክራል፤ ነገርግን በዕቃዎ መስታውት ወይም ማሳያ ላይ የሚያዩት ምስል ከምርቱ ትክክለኛ ቀለም ጋር መዛመዱን ልናረጋጥልዎ አንችልም፡፡

24. የማከማቻ አቀራረብ ስህተት፡፡ መረጃዎችን በትክክል እንድናትም፣ ማከማቻውን በየጊዜው ወቅታዊ እንድናደርግ እና ችግሮች ሲከሰቱ ለማረም ተግተን እንሰራለን፡፡ ሆኖም ግን፤ በማከማቻ ውስጥ ያሉት የትኞቹም ይዘቶች በየትውም ጊዜ ላይ የስሕተት ወይምቀኑ ያለፈበት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በማከማቻው ላይ በየትኛውምጊ ዜ፤ የምርት ዋጋዎችን፣ ልዩባሕሪያትን፣ አቅራቦቶችን እና መገኘትን ጨምሮ ለውጥ የማድረግ መብት አለን፡፡

25. የአጠቃቀም ወይም የመጠቀም ውል ስለማፍረስ፡፡ Microsoft በየትኛውምጊዜ፣ በየትኛውም ምክንያት፣ የሽያጭ ስርዓቶችን ወይም የማከማቻ ፖሊሲዎችን ጥሰት አስመልክቶ ወይም ማከማቻው ከዚህ በኋላ በ Microsoft የማይመራ ከሆነ የገደብ አለመኖርን ጨምሮ መለያዎን ወይም የማከማቻ ጥቅምዎን ሊያቋርጥ ይችላል፡፡ ማከማቻውን በመጠቀም፤ (ከእነዚህ ስርዓቶች አኳያ) ለሚያደርጉት ለየትኛውም ትዕዛዝ ወይም ከመቋረጡ በፊት ለሚያወጡት ለየትኛውም ወጪ ኃላፊነት ለመውሰድ ተስማምተዋል፡፡ Microsoft በየትኛውም ጊዜ በየትኛውም ምክንያት፣ እና ያለ ምንም ቅድመ ማሳወቂያ ማከማቻውን ሊቀይር፣ ሊያቋርጥ ወይም ሊያግድ ይችላል፡፡

26. ዋስትናዎች እና የማስተካከያ ዋስትናዎች፡፡ የከተማዎ ሕግ እስከሚፈቅደው ጥግ ድረስ፤ MICROSOFT እና አቅራቢዎቹ፣ አከፋፋዮቹ፣ መልሶ ሻጮቹ፣ እና የይዘት አቅራቢዎቹ ምንም ዓይነት ገለፃ ወይም የጥቆማ ዋስትናዎች፣ ዋስትናዎች፣ ወይም ሁኔታዎች፣ የነጋዴ ችሎታን ጨምሮ፣ አጥጋቢ ጥራት፣ ለተወሰነ ዓላማ ብቁነት፣ የስራ ጥረት፣ ርዕስ፣ ወይም ሕግን ያለማፍረስ አይሰጡም፡፡ በአጠቃላይ የፍቃድ ስምምነቶች ወይም የሚያጅቧቸው የአምራቾች ዋስትናዎች ካሏቸው፤ በማከማቻ ውስጥ የሚሸጡ ወይም የሚገኙ ምርቶች እና አገልግሎቶች ዋስትናአላቸው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘው የፈቃድ ስምምነት መሰረት ወይም በአምራቹ ዋስትና እና በእርስዎ ሀገር ህግ መሰረት ካልሆነ በስተቀር:

ግዢዎ እናአጠቃቀምዎ በራስዎ ኃላፊነትነው;

ምርቶችን እና አገልግሎቶችን “እንዳሉ አድርገን,” “ከነስሕተታቸው,” እና “እንደ አቅራቦታቸው” እናቀርባለን;

ስለ ጥራታቸው እና ስለ አቋማቸው ያለውን ስጋት እርስዎ ይሸከማሉ፤ እና

የሁሉንም አስፈላጊ የጥገናም ሆነ የእድሳት ወጪዎች እርስዎ ይሸከማሉ፡፡

MICROSOFT በማከማቻ ወይም በአገልግሎቶች ለቀረቡ መረጃዎች ወቅታዊነት ወይም ትክክለኝነት ዋስትና አይሰጥም፡፡ ኮምፒውተር እና የቴሌኮሙኒኬሽን ክስተቶች ከስህተት የፀዱ እና በተለያየ አጋጣሚ የሚወስዱት ጊዜ የተጓተተ መሆኑን ያውቃሉ፡፡ ወደማከማቻ ወይም አገልግሎቶች መግባት የማይቋረጥ፣ ወቅቱን የጠበቀ ደህንነቱ የተጠበቀ ወይም ከስህተት የጸዳ ወይም የይዘቶች መጥፋት አይከሰትም የሚል ዋስትና አንሰጥም፡፡

እነዚህየሽያጭስርዓቶችቢኖሩምከማከማቻ፣አገልግሎትወይምከማናቸውምምርትወይምየተሰጠአገልግሎትጋርየተያያዘየሚደርስብዎትጉዳትሊስተካከልየሚችልበትሁኔታተፈፃሚነትባለውህግእስከሚፈቀደውደረጃድረስየሚስተካከልመሆኑን፣የሚሰጠውካሳከMICROSOFT ወይምከአቅራቢዎቹወይምከሻጮቹወይምአከፋፋዮቹእናየይዘትአቅራቢዎችበቀጥታእስከ (1) ድረስየሚሸፈንመሆኑንለማናቸውምአገልግሎት፣ሰብስክሪፕሽንወይምተመሳሳይለሆኑእቃዎችየሚከፈለውዋጋወይምክፍያ (የግዢየሀርድዌር፣ሶፍትዌርድጋፍወይምየረዥምጊዜዋስትናሳይጨምር) ወይም (2) ዩኤስ $100.00 መሆኑንይህምአገልግሎት፣ሰብስክሪፕሽንወይምተመሳሳይክፍያበሌለጊዜመሆኑንያረጋግጣል፡፡

በእርስዎ ሀገር ህግ መሰረት አንድአንድ የተረጋገጡ መብቶች ሊኖርዎት ይችላሉ፡፡ በዚህ ውል ውስጥ እዚህን መብቶች ለመጉዳት የታሰበ ምንም ነገር የለም፡፡

በኒውዝላንድለሚኖሩሸማቾችበኒውዝላንድየሸማቾችጥበቃህግመሰረትየሚከበሩመብቶችየሚኖሩሲሆንእነዚህንመብቶችየሚነካምንምነገርበዚህየሽያጭስርዓቶችውስጥየለም፡፡

27. የይርጋ ጊዜ፡፡ ተፈፃሚ በሆነው ህግ እስከሚጠረው ደረጃ ድረስ ማናቸውንም ጉዳቶች ወይም ኪሳራዎች አንድን ሁኔታ ተከትለው፣ በልዩነት፣ በተዘዋዋሪ፣ በተያያዥ ወይም ባጋጣሚ የተከሰተ ጉዳት ወይም የትርፍ ማጣትን ጨምሮ ሊያስተካክሉት የሚችሉት ነገር አለመኖሩን ተስማምተውበታል፡፡ በክፍል 26 እና 27 ውስጥ የተቀመጡ ገደቦች እና የማይካተቱ ሁኔታዎች ምንም እንኳ ጉዳት የደረሰብዎት እና ይህ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል እኛ አስቀድመን እናውቀው የነበረ ቢሆንም ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡ አንዳንድ ግዛቶች ወይም ክፍላተ ሀገራት/የድንበር ክልሎች ባጋጣሚ ወይም አንድን ሁኔታ ተከትለው የሚመጡ ጉዳቶች የማይካተቱ ጉዳቶች ወይም ገደቦች እንዲኖሩ አይፈቅዱም፣ በዚህም ከላይ የተገለጸው ገደብ ወይም የማይካተት ሁኔታ በእርስዎ ላይ ተፈፃሚ አይሆንም፡፡

አግባብነት ባለው ህግ እስከሚፈቀደው ከፍተኛ ህግ እነዚህ ገደቦች እና የማይካተቱ ጉዳዮች ከማከማቻ አገልግሎቶች የሽያጭ ስርዓቶች ወይም ማናቸውም ምርት ወይም የተሰጡ አገልግሎቶች በተያያዘ የይዘት መጥፋትን ጨምሮ በእርስዎ የይገባኛል ጥያቄ፣ በማናቸውም ህጋዊ ንድፈ ሀሳብ ላይ ተፈፃሚ ይሆናሉ፣ ማንኛውም ቫይረስ ወይም የሚጠቀሙበት መሳሪያ በአግባቡ እንዳይሰራ እና ለማከማቻአገልግሎቶች ወይም ከማከማቻከሚያገኟቸውን ማናቸውም ምርቶች ወይም አገልግሎቶች በአግባቡ እንዳይጠቀሙ የሚያደርጉ ነገሮች ማንኛውም የስርጭት ወይም የግብይት ስርዓቶች እንዳይጠናቀቁ የሚያደርጉ ወይም የሚያዘገዩ ወይም እንዳይሳኩ የሚያደርጉ ነገሮች በዚሁ ውስጥ አይሸፈኑም፡፡

28. እነዚህንስምምነቶችመተርጎም፡፡የዚህ የሽያጭ ስርዓቶች ሁሉም ክፍሎች አግባብነት ባለው ህግ እስከሚፈቀደው ደረጃ ድረስ ተፈፃሚ ይሆናሉ፤ እርስዎ በሚኖሩበት ህጋዊ ክልል (ወይም የንግድ ስራ፣ ዋና የስራ ቦታ) ውስጥ ካሉት መብቶች የተሻለውን ሊሰጥዎ ይችላል፡፡ እነዚህን የሽያጭ ስርዓቶች ክፍሎች በጽሁፍ በተዘጋጁበት ሁኔታ ተፈፃሚ ልናደርጋቸው የማንችል ከሆነ እነዚህን ስምምነቶች አግባብነት ባለው ውስጥ በሚፈቅደው ደረጃ በተመሳሳይ ስምምነቶች ልንለውጣቸው እንችላለን፡፡ ነገር ግን የተቀሩት የሽያጭ ስርዓቶች አይለወጡም፡፡ ይህ የሽያጭ ስርዓቶች ተፈጻሚ የሚሆነው ለእርስዎ እና ለእኛ ጥቅም ብቻ ነው፣ ከ Microsoft ወራሾች እና ተቀባዮች በስተቀር ለሌላ ለማናቸውም ሰው ጥቅም ተፈፃሚ መሆን አይችሉም፡፡ እርስዎ ምርቶችን ወይም አገልግሎቶችን ከሌላ የ Microsoft ድረገጾች ላይ የገዙ ከሆነ ተፈፃሚ የሚደረጉ ሌሎች ስምምነቶች አሉ፡፡

29. በስጦታማስተላለፍ፡፡አግባብነት ባለው ህግ ውስጥ በሚፈቀደው መሰረት ለእርስዎ ምንም አይነት ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልግ በዚህ የሽያጭ ስርዓቶች ውስጥ ያሉትን መብቶች እና ግዴታዎች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ለሌላ ሰው ልንሰጥ፣ ልናስተላልፍ ወይም ልናስወግድ እንችላለን፡፡ በዚህ የሽያጭ ስርዓቶች ውስጥ ያሉትን ማናቸውንም መብቶች መስጠት ወይም ማስተላለፍ አይችሉም፡፡

30. ማስጠንቀቂያዎችእናግንኙነቶች፡፡ለደንበኛ ድጋፍ ጥያቄዎች እባክዎ በማከማቻ ውስጥ የሽያጭ እና ድጋፍ ገጽ የሚለውን ይመልከቱ፡፡ አለመግባባትን በተመለከተ በዚህ ክፍል ውስጥ ያለውን የማስጠንቀቂያ አሰጣጥ ስርዓት ይከተሉ፡፡

31. ተዋዋይተቋም፣አለመግባባትንለመፍታትየሚደረግየህግእናየቦታምርጫ፡፡

a. ከዩናይትድስቴትስእናካናዳውጭሰሜንወይምደቡብአሜሪካ፡፡እርስዎ የሚኖሩት (ወይም የንግድዎ ወይም ዋና የስራ ቦታዎ) ከዩናይትድ ስቴትስ እና ካናዳ ውጭሰሜን ወይም ደቡብ አሜሪካ ከሆነ፤እርስዎ በቀጥታ ከ Microsoft ኮርፖሬሸን፣ዋን Microsoft ዌብ ሬድ ሞንድ፣ WA 98052፤ ዩኤስኤ ጋር ግንኙነት ማድረግ ይችላሉ፡፡ የዋሽንግተን ግዛት ህግ በእነዚህ የሽያጭ ስርዓቶች አተረጓጎም እና በውል ጥሰት ምክንያት በሚኖሩ የይገባኛል ጥያቄዎች ላይ የተደረገው የህግ መርህ ምርጫ ምንም ይሁን ምን ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ ማከማቻውን ወይም አገልግሎቶችን የምንልክበት ሀገር ህጎች (የሸማች ጥበቃ አግባብነት የጎደለው ውድድር እና ከህግ ውጭ የቀረበ የይገባኛል ጥያቄን ጨምሮ) በሌሎች የይገባኛል ጥያቄዎች ላይ ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡

b. መካከለኛውምስራቅወይምአፍሪካ፡፡እርስዎ የሚኖሩት (ወይም የንግድዎ ወይም ዋና የስራ ቦታዎ) መካከለኛው ምስራቅ ወይም አፍሪካ ከሆነ በቀጥታ ከ Microsoft አይርላንድ ኦፕሬሽንስ ሊሚትድ፣ ዘአታሪየም ቢዩልዲንግ ብሎክ ቢ. ካርማን ሆል ሮድ፣ ሳንዲፎርድ ኢንዱስትሪያል እስቴት ደብሊን18፤ አይርላንድ ጋር ግንኙነት ማድረግ እና ውል መፈራረም ይችላሉ፡፡ የአየርላንድ ህጎች በዚህ የሽያጭ ስርዓቶች አተረጓጎም እና በውል ጥሰት ምክያት የሚኖሩ የይገባኛል ጥያቄ ላይ የተደረገው የህግ መርህ ምርጫ ምንም ይሁን ምን ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ ማከማቻውን ወይም አገልግሎቶችን የምንልክበት ሀገር ህጎች (የሸማች ጥበቃ አግባብነት የጎደለው ውድድር እና ከህግ ውጭ የቀረበ የይገባኛል ጥያቄን ጨምሮ) በሌሎች የይገባኛል ጥያቄዎች ላይ ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡ ከዚህ የሽያጭ ስርዓቶች ወይም ማከማቻ ጋር በተያያዘ ወይም ከዚህ በሚነሱ ማናቸውም አለመግባባት በሚኖሩ ጊዜ፤ ጉዳዩ የሚታየው በአየርላንድ ፍርድቤቶች ብቻ የሚታዩ መሆኑን እርስዎ እና እኛ ተስማምተናል፡፡

c. እስያወይምደቡብፓስፊክ፣ከዚህበታችየተጠቀሱትንሀገራትሳያካትት፡፡እርስዎ የሚኖሩት (ወይም የንግድዎ ወይም ዋና የስራ ቦታዎ) እስያ ውስጥ (ከቻይና፣ ጃፓን፣ ኮሪያ ሪፐብሊክ ወይም ታይዋን በስተቀርከሆነ)፤ እርስዎ በኔቫዳ ዩኤስኤ ህጎች መሰረት ከተቋቋመው ከ Microsoft ክልላዊ የሽያጭ ኮርፖሬሽን ጋር መገናኘት የሚችሉ ሲሆን የዚህ ድርጅት ቅርንጫፎች ሲንጋፖር እና ሆንግ ኮንግ ውስጥ ይገኛሉ፤ ዋና የተመዘገበ አድራሻው 438B አሌክሳንድራ ሮድ፣ #04-09/12፣ ብሎክ ቢ፣ አሌክሳንድራ ቴክኖፓርክ፣ ሲንጋፖር 119968 ነው፡፡ የዋሽንግተን ግዛት ህግ በእነዚህ የሽያጭ ስርዓቶች አተረጓጎም እና በውል ጥሰት ምክንያት በሚኖሩ የይገባኛል ጥያቄዎች ላይ የተደረገው የህግ መርህ ምርጫ ምንም ይሁን ምን ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ ማከማቻን ወይም አገልግሎቶችን የምንልክበት ሀገር ህጎች (የሸማች ጥበቃ አግባብነት የጎደለው ውድድር እና ከህግ ውጭ የቀረበ የይገባኛል ጥያቄን ጨምሮ) በሌሎች የይገባኛል ጥያቄዎች ላይ ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡ ማናቸውንም ህጋዊነት፣ የውል መፍረስ የተመለከቱ ጥያቄዎችን ጨምሮ ከዚህ የሽያጭ ስርዓቶች ወይም ከማከማቻ ጋር በተያያዘ ወይም ከእነዚህ የተነሳ ማናቸውም አለመግባባት ካለ ጉዳዩ ሲንጋፖር ውስጥ በሲንጋፖር አለም አቀፍ የግልግል ማዕከል (ኤስአይኤሲ) ማዕከል አለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ደንቦች መሰረት ታይቶ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጠዋል፡፡ ይህም በእነዚህ አንቀጾች ውስጥ በማመሳከሪያነት እንዲካተት ተደርጓል፡፡ የግልግል ዳኝነት ጉባዔው በኤስአይኤሲ ፕሬዝዳንት በሚሾም አንድ የግልግል ዳኛ የሚቋቋም ይሆናል፡፡ የግልግል ዳኝነት ቋንቋው እንግሊዝኛ ነው፡፡ የግልግል ዳኝነት ውሳኔ የመጨረሻ እና አስገዳጅ፣ ሊለወጥ የማይችል ሲሆን ከዚህ በኋላ በማናቸውም አገር ወይም ክልል ውስጥ ለሚሰጥ ፍርድ መነሻ ወይም ቅድመ ሁኔታ ይሆናል፡፡

d. ጃፓን፡፡እርስዎ የሚኖሩት (ወይም የሚሰሩት ወይም ዋና የስራ ቦታዎ) ጃፓን ውስጥ ከሆነ በቀጥታ ከ Microsoft ጃፓን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ(ኤምኤስኬኬ)፣ ሺናጋዋ ግራንድ ሴንትራል ታወር፣ 2-16-3 ኮናን ሚናቶ-ኩ፤ ቶኪዮ 108-0075 ጋር ግንኙነት ማድረግ ይችላሉ፡፡ የጃፓን ህግ በዚህ የሽያጭ ስርዓቶች ጋር ከእነዚህ ወይም ከማከማቻ ጋር ተያያዥ በሆኑ በማናቸውም ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

e. የኮሪያሪፐብሊክ፡፡እርስዎ የሚኖሩት(ወይም የንግድዎ ወይም ዋና የስራ ቦታዎ) ኮሪያ ሪፐብሊክ ውስጥ ከሆነ በቀጥታ ከ Microsoft ኮሪያ ኢንክ፣ 11ኛ ፎቅ ታወር ኤ-ቲዊን ታወር ጆንግሮ 1 ጊል 50፤ ጆንግሮ-ጉ፣ ሲኦል ኮሪያ ሪፐብሊክ 110-150 ጋር ግንኙነት ማድረግ ይችላሉ፡፡ የኮሪያ ሪፐብሊክ ህግ በዚህ የሽያጭ ስምምነት ጋር ከእነዚህ ወይም ከማከማቻ ጋር ተያያዥ በሆኑ በማናቸውም ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

f. ታይዋን፡፡እርስዎ የሚኖሩት (ወይም የንግድዎ ወይም ዋና የስራ ቦታዎ) ታይዋን ውስጥ ከሆነ በቀጥታ ከ Microsoft ታይዋን ኮርፖሬሽን፣ 18ኤፍ፣ ቁጥር 68 ክፍል 5 ዞንዣዎ ኢ.አርዲ.፣ ሺኒያ ዲስትሪክት ቴፒ 11065 ታይዋን ጋር ግንኙነት ማድረግ ይችላሉ፡፡ የታይዋን ህግ በዚህ የሽያጭ ስርዓቶች ጋር ከእነዚህ ወይም ከማከማቻ ጋር ተያያዥ በሆኑ በማናቸውም ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ Microsoft ታይዋን ኮርፖሬሸን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ እባክዎ በኢኮኖሚ ጉዳዮች ሚኒስቴር አር.ኦ.ሲ. የተሰጠውን (https://gcis.nat.gov.tw/main/index.jsp) ድረ ገጽ ይመልከቱ፡፡ እርስዎ እና እኛ የታይዋን ቴፒ ዲስትሪክት ፍርድ ቤትከዚህ ስርዓቶች ወይም ማከማቻ ጋር በተያያዘ ሊነሳ የሚችል ማናቸውም አለመግባባት፤ በታይዋን ህግ እስከሚፈቀደው እስከከፍተኛው ደረጃ ድረስ ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የሚመለከት ፍርደ ቤት እንዲሆን በማይሻር ሁኔታ ተስማምተናል፡፡

32. ማስጠንቀቂያዎች::

a. የአእምሮአዊንብረትጥሰትንየተመለከቱየይገባኛልጥያቄዎችንለማቅረብየሚሰጡማስጠንቀቂያዎችእናየአሰራርስርዓት፡፡Microsoft የሶስተኛ ወገኖችን የአእምሮአዊ ንብረት መብቶች ያከብራል፡፡ የቅጂ መብት ጥሰትን ጨምሮ የአእምሮአዊ ንብረት መብት ጥሰትን በተመለከተ ማስጠንቀቂያ መላክን የሚፈልጉ ከሆነ እባክዎ የመብት ጥሰት ማስጠንቀቂያዎች አቀራረብ ስነ ስርአት (https://www.microsoft.com/info/cpyrtInfrg.aspx)ይጠቀሙ:: ከዚህ ሥነ ሥርዓት ጋር አግባብነት የሌላቸው ጥያቄዎች ምላሽ አያገኙም፡፡

Microsoft በርዕስ 17፣ የዩናይትድ ስቴትስ ህግ ክፍል 512 ውስጥ በዝርዝር የተቀመጡትን ሂደቶች በመጠቀም ለቅጂ መብት ጥሰት ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣል፡፡ አግባብነት ባላቸውም ሁኔታዎች ውስጥ Microsoft የ Microsoft አገልግሎቶችን በተደጋጋሚ ጥሰው የሚገኙ የተጠቃሚዎችን አካውንት ሊሰርዝ ወይም እንዳይሰራ ሊያደርግ ይችላል፡፡

b. የቅጂመብትእናየንግድምልክትማስጠንቀቂያዎች፡፡

የማከማቻ እና አገልግሎቶች ይዘቶች በሙሉ Copyright ©2016Microsoft ኮርፖሬሽን እና/ወይም አቃቢዎቹ እና ሶስተኛ ወገን አቅራቢዎች፣ ዋን Microsoft ዌይ፣ ሬድሞንድ፣ WA98052፣ ዩኤስኤ ናቸው፡፡ ሁሉም መብቶቹ የተጠበቁ ናቸው፡፡ እኛ ወይም የእኛ አቅራቢዎች እና ሶስተኛ ወገን አቅራቢዎች የራሳቸው መብት፣ የቅጂ መብት እና ሌላ የአእምሮአዊ ንብረት መብት በማከማቻ፣ አገልግሎቶች እና ይዘቶች ላይ አላቸው፡፡ Microsoft እና ስያሜዎቹ አርማዎቹ እና ሁሉም የ Microsoft ምርቶች እና አገልግሎቶች ምልክቶች ወይም የንግድ ምልክት አለዚያም በዩናይትድ ስቴትስ፣ ካናዳ እና/ወይም በሌሎች ሀገራት ውስጥ የተመዘገቡ የ Microsoft የንግድ ምልክቶች ናቸው፡፡

የ Microsoft የንግድ ምልክት ዝርዝሮች ከሚከተለው ድረገጽ ሊገኙ ይችላሉ፡

https://www.microsoft.com/trademarks፡፡ የትክክለኛ ኩባንያዎች ስያሜዎች እና ምርቶች የየባለቤቶቹ የንግድ ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በእነዚህ የሽያጭ ስርዓቶች ውስጥ በግልጽ ያልተሰጡ መብቶች የተጠበቁ ናቸው፡፡

33. የደህንነትማስጠንቀቂያ፡፡ሊደርስ የሚችል የመቁሰል አደጋ፣ የአይን መቆርቆር ወይም ተያያዥ ችግሮችን ለማስወገድ ጌሞችንወይም ሌሎች መተግበሪያዎችን በተለይም እነዚህን አብዝተው በመጠቀም የሚመጣ ማንኛውም ህመም ወይም ከባድ ድካም የሚሰማዎ ከሆነ በየተወሰነ ጊዜው እረፍት ያድርጉ፡፡ ምቾት ማጣት የሚሰማዎ ከሆነ ትንሽ እረፍት ያድርጉ፡፡ ምቾት ማጣት ምናልባት ማቅለሽለሽን፣ የእንቅስቃሴ ህመም መደንዘዝ፣ ራስ ምታት፣ ከባድ ድካም፣ የአይን መቆርቆር ወይም የአይን ድርቀትን ሊያካትት ይችላል፡፡ መተግበሪያዎችን መጠቀም ትኩረትዎን ሊረብሽ እና በዙሪያዎ ያሉት ነገሮች እንዳያስተውሉ ሊያደርጎት ይችላል፡፡ በጉዞ ወቅት የሚከሰቱ ነገሮችን እቃዎችን ይዘው ደረጃ መውጣትን፣ ዝቅ ያለ ኮርኒስ ስር መጓዝንያስወግዱ፡፡ በጣም ጥቂት ሰዎች እንደፍላሽ ብርሀን ወይም መተግበሪያዎች ላይ ያሉ የተለያዩ ፓተርኖች የመሳሰሉ እይታዎች ሲያጋጥማቸው መዛል ወይም መውደቅ ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡ የዚህ አይነት ችግር አጋጥሟቸው የማያውቅ ሰዎችን ጨምር የዚህ አይነት ችግር ሊያስከትል የሚችል ሁኔታ ላይ መሆናቸውን በምርመራ ላይ ሊደርሱበት ይችላል፡፡ የዚህ ምልክቶችን የራስ መቅለል፣ የእይታ መለዋወጥ የአይን ማሳከክ፣ መራድ ወይም የእጅ እና እግር መንቀጥቀጥ፣ ግራ መጋባት ንቃተ ህሊናን ማጣት ወይም ወደላይ የማለት ስሜት ሊያካትት ይችላል፡፡ በፍጥነት ያቁሙ እና እነዚህ የህመም ምልክቶች የሚሰማዎ ከሆነ ዶ/ር ያማክሩ ወይም ከዚህ በፊትየዚህ አይነት ችግር አጋጥሞት ከነበረ መተግበሪያውን ከመጠቀምዎ በፊት ከሀኪም ጋር ይማከሩ፡፡ ወላጆች የልጆቻቸውን የመተግበሪያ አጠቃቀም ወይም የህመም ምልክት ትኩረት ሰጥተው ሊቆጣጠሩት ይገባል፡፡